የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ የሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ግምገማ አካሄደ።
0E2A5073ባህርዳር ጥቅምት 9 ፣ 2017 ( እ/ዓ/ሃ/ል/ጽ/ቤት) የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ የሩብ አመት የስራ አፈጻጸም ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች በተገኙበት የ3 ወር የዋና ዋና ስራዎች አፈፃፀምን ገመገመ ፡፡
በግምገማ መድረኩ የዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የማኔጅመንት አካላት እንዲሁም የዞንና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራርሮች ተገኝተዋል፡፡
መድረኩን በንግግር የከፈቱት የጽ/ቤቱ ኃላፊ ዶ/ር ጋሻው ሙጨ ሲሆኑ ሀላፊው በመልክታቸው የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው ካለው ፋይዳ በተጨማሪ ለወጣቶችና ሴቶች በውስን ካፒታል እና መሬት ሰፊ የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው ብለዋል ።

 

ኃላፊው አክለውም በ2017 በጀት ዓመትም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብና የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ የተቋሙን የልማት ግቦች ለማሳካት በየደረጃው ያለው አመራር እና ሙያተኛ ክልላችን ያለበትን ሁኔታ በተገቢው መልኩ ተገንዝቦ በችግር ውስጥም ሆኖ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ ክላስተርን መሰረት ያደረጉ ስራዎችን በትኩረት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ፡፡
በመድረኩ የሦስት ወር የዋና ዋና ስራዎች አፈፃፀም የሚያሳይ ሪፖርት የእቅድ ዝግጅት ክትትል ባለሙያ በአቶ ጀማል ሙሐመድ በኩል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡
በውይይቱ ማጠቃለያም በቀጣይ በአፈፃፀም ረገድ የታዩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ ማስቀጠል እንዲሁም እጥረቶችን ለይቶ በቀጣይ ጊዜያት የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንዳለበት ተገልጻል ።
በመጨረሻም የዕለቱን ግምገማዊ መድረኩን በመሩት የጽ/ቤቱ ሃላፊዎች በኩል የማጠቃለያ ሃሳብና የቀጣይ አቅጣጫ ተሰጥቶ የእለቱ መድረክ ተጠናቋል፡፡
0E2A5063
LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |