የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት አመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ::
0E2A2613ኮምቦልቻ ነሐሴ 19፣ 2016 ( እ/ዓ/ሃ/ል/ጽ/ቤት) የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በምስራቅ አማራ ለሚገኙ ዞኖች የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ ።
በመድረኩ የዞን ሃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ፣የከተማ አስተዳደር ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው ዩንቨርስቲዎችና የፕሮጀክት አስተባባሪዊች እንዲሁም የክልል ሃላፊዎችና ዳይሬክተሮች ተሳታፊ ሆነዋል ፡፡
በመድረኩ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የቁልፍና የአበይት ተግባራት አፈፃፀም እንዲሁም የ2017 በጀት ዓመት እቅድ በጽ/ቤቱ የእቅድ ዝግጅት ክትትል ባለሙያ በአቶ ጀማል ሙሀመድ ቀርቧል፡፡
በተጨማሪም የመንግስት የትኩረት ማዕከል የሆነው የሌማት ቱርፋት እቅድ አፈጻጸም እና የ2017 ዓ.ም የሌማት ቱርፋት እቅድ በአቶ መኳንንት ዳምጤ የእንስሳት እርባታ ፣ተዋጽኦ እና መኖ ልማት ዳይሬክተር በኩል ቀርቧል ።

 

የቀረቡ ፕረዘንቴሽኖች መሰረት አድርጎ ወደ ውይይት የተገባ ሲሆን የዕለቱን ውይይት የመሩት የጽ/ቤቱ ሃላፊዎች ሲሆኑ ክልሉ በፀጥታ ችግር ውስጥ ሆኖ በየደረጃው ያለው መዋቅራችን ከነችግሩም ቢሆን የሰራቸው ስራዎች የሚበረታተ መሆኑን በመጥቀስ ግን ደግሞ በተመሳሳይ የፀጥታ ችግር ውስጥ ሆነው የተሻለ የፈፀሙ ዞኖችና ከተሞች ሊመሰገኑና ተሞክሮም ሊወሰድባቸው ይገበባል ብለዋል።
ከዚህ በመነሳት በቀረበው ሪፖርትና እቅድ ላይ ቤቱ በስፋት በመወያየት ለቀጣይ ስራችን የተሻለ መነሳሳትና መግባባት በሚፈጥር ሁኔታ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል።
0E2A2673
LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |