ባሕርዳርየእንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርመራ ላቦራቶሪ
መግቢያ
በኢትዮ-ቻይና የጋራ ፕሮጀክት አማካኝነት በ1972 ተቋቋመ በእንስሳት ዘርፍ በተለያዬ ደረጃ እና የእርባታ ዓይነት የሚንቀሳቀሱትን ለማገልገልየመስክ የእንስሳት ጤና አገልግሎቱን እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ለመደገፍ ፡፡
ተልዕኮ
የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገውን ጥረት በማገዝ፤ በእንስሳት አርቢው ጥያቄ ላይ የተመሠረተ የበሽታ ቅኝት እና ምርመራ በማካሄድተላላፊ እና ተላላፊ ባልሆኑ የእንስሳት በሽታዎች ላይ የቁጥጥር መርሀ-ግብር በመንደፍ፤የክልሉን ከፍተኛ የዕድገት ደረጃ ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት አስተዋጽኦ ማድረግ፡፡
ራዕይ
የእንስሳትን ጤንነት በመጠበቅ፡-
ለዘላቂ ልማት አስተዋጽኦ ማድረግና የሕብረተሰቡ ኑሮ በተሻሻለ ሁኔታ ተለውጦ ከድህነት ነጻ የሆነ ክልል እና አገር ማየት፤
የትኩረት አቅጣጫዎች
- የላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት
- የመስክ እንስሳት ጤና ባለሙያዎችን አቅም መገንባት
- ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው የእንስሳት ጤና አጀንዳዎች ላይ ቅኝት ማካሄድ
- የጥራት አስተዳደር ሥርዓትን ማጎልበት
- የበጀት ምንጮችን ማፈላለግ
- አገልግሎት አሰጣጥን ማስፋት
- የደንበኞችን ስኬት ማጎልበት እና
- የደንበኞችን እርካታ ማረጋገ
- የስራሽፋንወይንምክልል
ምዕራብ አማራ ክፍል ያሉትን ዞኖች ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ጎንደር፣ ምዕራብ ጎንደር ማዕከላዊ ጎንደር፣ ምዕ/ጎጃም፣ ምስ/ጎጃም፣ ሰሜን ጎጃምች አዊ፣ ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ እና ሪጅዮፖሊታንከተሞች ባህርዳር ፣ጎንደር አካቶ ይዟል፡፡
የማዕከሉ ዋና ዋና ተግባራትና ኃላፊነት
የበሽታ ፍንዳታን መመርመርና መንሥዔዎቹን መለየት፣የምርመራ አገልግሎት መስጠት ፣ ወርሃዊ ለዓለም እንስሳት ጤና ድርጅት የሚላኩ የወረዳ ሪፖርቶችን ማጠናቀርና ወደ ሰርቨር ማስገባት ፣ ቅኝትና ጥናት ማካሄድ፣የላቦራቶሪ ቴክኒክ ሥልጠና መስጠት፣ለእርባታ ጣቢያዎችና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከላት ድጋፍ መስጠት፡፡
የላቦራቶሪ ቴክኒክ ሥልጠና / Off-campus Training
ለወረዳ የእን/ጤና ክሊኒክ የላቦራቶሪ ቴክኒሽያኖች፣ለዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እና ለ TVET ኮሌጅ ተማሪዎች
የበሽታ ፍንዳታን በመመርመርና በመለየት ምላሽ መስጠት /Outbreak Investigation /
በሽታው ከተነሳበት ቦታ መረጃ በስልክ ወይም ቴሌግራም መቀበል፣ወደ ቦታው የሚሄዱ ባለሙያዎችን ቡድን ማዋቀርቡድኑ ወደ ቦታው ከመሄዱ በፊት ዝርዝር መረጃ በተዘጋጀ ፎርማት ከወረዳው በስልክ መቀበ ወደ ቦታው በመሄድ መረጃና ናሙናዎችን መሰብሰብ ፣ለእንስሳቱ ባለቤቶችና በቦታው ለሚገኙ ባለሙያዎች ወቅታዊ ምክረ-ሀሳብ መስጠት፣ወደ ላቦራቶሪ በመመለስ ምርመራ ማካሄድ ፣ከላቦራቶሪው አቅም በላይ የሆኑት ናሙናዎች ወደ ማዕከላዊ ላቦራቶሪ መላክ፣ለመፍትሔ የሚሆን በመረጃና የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤት ላይ የተመሠረተ የተጠናቀረ ሪፖርት ወደ ወረዳው መላክ
የላቦራቶሪ ምርመራ አገልግሎት መስጠት
ቫይረሶች መንሥዔ ይሆናሉ ተብለው ለተጠረጠሩ በሽታዎች፡- የሴሮሎጂ ምርመራ/Serological Diagnosis ወደ እንስሳት ጤና ኢንስቲትዩት መላክ (Referral to AHI)
ባክቴሪያዎች መንሥዔ ይሆናሉ ተብለው ለተጠረጠሩ በሽታዎች፡-ናሙናዎችን መዝራትና ማሳደግ/Bacterial Culture/፣በባዮኬሚካል ሙከራ ማካሄድ/Biochemical test/፣ በሚዲያዎች ላይ ያደጉ ባክቴሪያዎች ፣ ለፀረ-ተዋህስያን ያላቸውን ብግርነትና ፣ተጋላጭነት በቤተ ሙከራ መለየት /Antimicrobial Sensitivity Test
ቅኝትና ጥናት ማካሄድ
በእንስሳት ጤና በችግርነት በተለዩ በሽታዎች ላይ ቅኝት ማካሄድ Surveillance on regionally identified diseases/problemsየውርጃ በሽታ (Brucellosis), የጡት በሽታ (Mastitis), ገንዲ (Trypanosomosis), …ወዘተወቅታዊ ቅኝት ሰውን እና እንስሳትን የሚያጠቁ ድንበር ዘለል በሽታዎች ላይ (Active Surveillance on Trans-boundary Zoonotic Diseases)Highly Pathogenic Avian Influenza / HPAI (አደገኛ የወፍ ጉንፋን
ለዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት የሚላኩ ወርሃዊ የበሽታ ክስተትና ክትባት አፈጻጸም ሪፖርቶችን ማጠናቀር)
ከየዞኖች የሚላኩ የየወረዳዎቻቸውን ወርሃዊ የበሽታ ክስተትና ክትባት አፈጻጸም ሪፖርቶች ማሰባሰብ መረጃዎቹን ወደ ፌደራል ግብርና ሚ/ር ሰርቨር ማስገባት የየሩብ ዓመቱን መረጃ ማጠናቀርና ግብረ-መልስ መስጠት የዓመቱን መረጃ ማጠቃለል፣ ማጠናቀርና ግብረ-መልስ መስጠት
የበሽታ ቁጥጥርና ማጥፋት ፕሮግራምን ማስተባበር
ክልላዊ ማስተባበሪያ (Regional Coordination፣ ደስታ መሰል በሽታ (Rinderpest) - ከ13 ዓመታት በፊት ከአገራችን የጠፋ)ደስታ የበጎችና ፍየሎች በሽታ (Peste des petits ruminants/PPR) (በላቦራቶሪው በተከፈተ ቅ/ማስተባበሪያ ከ2012ዓ.ም ጀምሮ በመካሄድ ላይ የሚገኝ) Universities and Colleges ፣የግቢዉጭስልጠና/Off-campus Training ፣የምርምርአጀንዳዎችላይበጋራመሥራት ፣ /Jointly working on Researchable issues/ ፣የምርመራግብዓቶችንማቅረብ /Supply of consumables
FAO ለቅኝትሥራዎችየበጀትድጋፍናትብብር (Budget support on surveillance issues) ፣HPAI (አደገኛየወፍጉንፋን) AMR (ምልክትበማያሳየውየጡትበሽታላይባክቴሪያዎችለፀረ-ተዋህስያንያላቸውንብግርነትናተጋላጭነትበወተትላሞችእርባታጣቢያዎችለማጥናት)
USAID-IDDS Budget/Technical support on: AMR (ምልክትበማያሳየውየጡትበሽታላይባክቴሪያዎችለፀረ-ተዋህስያንያላቸውንብግርነትናተጋላጭነትበወተትላሞችእርባታጣቢያዎችለማጥናት) Quality Management System/QMS (ለላቦራቶሪጥራትአስተዳደርሥርዓትየባለሙያእናየቁሳቁስድጋፍ) ያደርጋል እኔህና መሰል ስራዎችልን ይሰራል