Debrebirhan Sheep multiplication and Breed Improvement Center
የደብረ ብርሃን በግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል በ1960 ዓ.ም በፌደራል ግብርና ሚንስቴር የተቋቋመ ማዕከል ነው፡፡ ማዕከሉ ከ1985 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በመዛወር በግብርና ቢሮ ስር ከ1994 ዓ.ም ጀምሮ በክልሉ ግብርና ምርምር ተቋምና በቅርቡ ደግሞ በአብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ሥር በመሆን የብዜትና ዝርያ ማሻሻል ስራውን ላለፉት 49 አመታት ሲያከናውን የቆየና እያከናወነ ያለ ማዕከል ነው፡፡ ማዕከሉ ወደ ክልሉ ከተዛወረ ወዲህ በአብዛኛው የሚያባዛቸውን የአዋሲ ዲቃላ ወጠጤ በጎችን ለሰሜንና ደቡብ ወሎ እንዲሁም ለሰሜን ሸዋ ዞኖች በማሰራጨት የተጣለበትን ሀላፊነት እየተወጣ ያለ ማዕከል ነው፡፡
ማዕከሉ በደጋማው አካባቢ ያለውን ሰፊ የበግ ሀብት ዝርያ በማሻሻል በወቅቱ በደብረ ብርሃን ከተማ ለተከፈተው የብርድ ልብስ ፋብሪካ ጥሬዕቃነት የሚያገለግል በቂ የበግ ጸጉር ለማቅረብ ታሳቢ ተደርጎ የተቋቋመ ቢሆንም ይህ ነው የሚባል የፀጉር ምርት በሚፈለገው ብዛትና ጥራት ማቅረብ ሳይችል ይልቁንም በወቅቱ በጎቹን ከማዕከል በሚሰጥ አቅጣጫ ለተለያዩ የንጉሱ የዘውድ ክበረ በዓላት ለሥጋ ወደ አዲስአበባ ይላኩ እንደ ነበረ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
ማዕከሉ ለረጅም አመታት ወጠጤዎችን ሲያሰራጭ የቆየ ቢሆንም በአርሶ አደሩ ዘንድ ከዓላማው እንጻር በተገቢው ጥቅም ላይባለመዋላቸው የተፈለገውን ያክል ውጤት ማምጣት ባለመቻሉ እነዚህ የተሸሻሉ በጎች በስፋት ረብተው አይታዩም፡፡ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ በ1990ዎቹ መጨረሻ አመታት በበሽታ ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ተዘግቶ የነበረ ቢሆንም ከ2000 ዓ.ም በኋላ እንደገና በአዲስ መልክ ወደ ብዜትና ዝርያ ማሻሻል ሥራው በመመለስ የበጎች አያያዝ ፤ የበጎች ድቀላ ፤የግልገል ውልደት እና የወጠጤ ሥርጭትሥራውን ከአመት አመት እያሳደገ ነው፡፡
ከዚን ጊዜ ጀምሮም ሙሉ ጊዜውንና በጀቱን በበግ ዝርያ ማሻሻል ስራ ላይ ትኩረት አደርጎ እየሰራ ያለ ማዕከል ሲሆን የሀገረሰብ በጎችንከአዋሲ አውራዎች ጋር በማዳቀልና የዲቃላዎችንም የደም መጠን እያሳደገና ምርትና ምርታማነትን ከመጨመሩም በላይ በአርሶ አደሩአካባቢ ከ4-6 ወር ባለ ጊዜ ውሥጥ ፈጥነው ለሥጋ እየደረሱ መሆኑ እና ከዓመት አመት የሥርጭት መጠኑም ሆነ አድማሱን እያሰፋ ያለማዕከል ነው፡፡
ማዕከሉ ቀደም ሲል የሀገረሰብና የውጪ በጎችን እርስ በርስና አንዱን ከሌላው ጋር የማዳቀል ሥራ ሲሰራ ቢቆይም በአሁኑ ሰዓት የአገረሰብበግ እርስበርስ የማዳቀል ሥራውን በመተው ሀገረሰብን ከውጪ አውራዎችና እንዲሁም የውጪዎቹን ከውጪ በጎች ጋር በማዳቀል የዝርያማሻሻል ሥራውን እየተወጣ ይገኛል፡፡
የእርባታ ስራው ወቅቱን የጠበቀ እና በተቻለ መጠን በጎች ሲጠቁም ሆነ ሲወለዱ በቂ የመኖ አቅርቦት በሚኖርበት ጊዜ እንዲሆን ለማድረግ እና በክረምት ወቅት ሲወለዱ የሚሞቱ የግልገል በጎችን ቁጥር ለመቀነስ ግልገሎች በክረምት እንዳይወለዱ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡፡
በጎች የድቀላ ጊዜያቸውን እንደጨረሱም እንደየዝርያና የሰውነት አቁዋማቸው እየታዩ መንጋ ይመሠረትና እስኪወልዱ ተገቢው እንክብካቤእየተደረገላቸው እንዲቆዩ እና ለመውለድ ሲደርሱም እየታዩ ወደ መውለጃ በረት ተዛውረው እንዲወልዱ ይደረጋል፡፡ እንደተወለዱም በየቀኑተገቢ የውልደት ታሪክ/መረጃ እየተያዘ ግልገሎች እየተመዘኑ ተፈላጊውን ክብደትና ጤንነት ሁኔታቸው ሲረጋገጥ የጆሮ መለያ ቁጥርእየተሰጣቸው ከ3-4 ወር እናቶቻቸውን እየጠቡና እንደየእድሜያቸው እና አቋማቸው እየታየ ተጨማሪ የተመጣጠነ መኖ እንዲመገቡከተደረገ በሁዋላ ጡት ሲጥሉም እንዳይደነግጡ አስፈላጊው እንክብካቤ ይደረግላቸዋል፡፡ይህም ሲደረግ ጡት ከጣሉበት ቀን ጀምሮ ወጠጤእና ቄብ በጥብቅ ክትትል እንዳይገናኙ ይደረጋል፡፡ ይህ የሚደረገው የእርባታ ሥራውን ከዘመደ ርቢ የጸዳ እንዲሆንና አርሶ አደሩ ዘንድውጤታማ ዝርያን ለማድረስ ስለሚያስችል ነው፡፡ የድቀላ አሰጣጡ አንድ አውራ ከ30 እስከ 40 ለሚሆኑ ሴት በጎች ሲሆን ከ34 -51 ቀናት መረጃ እየተያዘ አብረው እንዲቆዩ ይደረጋል፡፡
ማዕከሉ ለመኖ ስብሰባ በየአመቱ ከፍ ያለ በጀት እየመደበ ሠፊ ሊባል የሚችል የሰው ኃይል/ጉልበት/ ይጠቀማል፡፡ በተጨማሪምየተመጣጠነ እና የፋብሪካ ውጤት የሆነ መኖም እንዲሁ ሰፊ ሊባል የሚችል በጀት ወጪ በማድረግ እየቀረበ የሚገኝበት ሁኔታ መኖሩየጨውና ሌሎች የማዕድን መኖዎችን በጎች በተገቢው መጠንና ወቅት እንዲያገኙ እየተደረገ ይገኛል:: የሚመረተውን የመኖ ድርቆሽ ምርትከፍ ለማድረግና ጥራቱን ለማሻሻል የፍግና የዩሪያ ቶፕ ድሬ ማድረግ፤ ወቀቱን የጠበቀ የአረም ሥራ እየሰራ የድርቆሽ ምርታማነትንከአመት አመት እያሻሻለ መምጣቱ የሚበረታታ እና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑ ማዕከሉ ዓላማውነን ለማሳካት እያደረገ ያለውጥረት አካል ነው፡፡በማዕከሉ የተሻለ የበጎች አያያዝ በመደረጉ በጎች መንታ የመውለድ፤ እንዲሁም ንጹህ አዋሲ በጎች በአንድ ውልደት ከ3 - 4 ግልገሎችን መውለድ የቻሉበት ሁኔታ መኖርና ይህ መልካም ጅምር አርሶአደሩ ድረስ መውረድ እንዳለበት ጽኑ እምነት ተይዞ እየተሰራ ይገኛል፡፡
ማዕከሉ ከ2007 በጀት አመት መጨረሻ ጀምሮ ደግሞ ከአዋሲ በግ ዝርያ በተጨማሪ የዶርፐር በግ የማባዛትና እስካሁን ተደራሽባልሆነባቸው ቆላማና ወይናደጋማ ወረዳዎች ለሚኖሩ አርሶ አደሮች ለማሰራጨት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል:: የሀገረሰብ በጎች አድገውለእርድ ወይም ለሽያጭ የሚደርሱት በረጅም ወራትና የስጋ ምርታቸውም በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ በአመት 2 ጊዜ ወጠጤ በጎችየተሰራጩባቸው ዞኖችና ወረዳዎችን፤ ቀበሌዎችን መሰረት በማድረግ እስከ አርሶ አደሩ ቤት ድረስ በመሄድ ስለአያያዛቸው እናአመጋገባቸው በጎቹ በተጨባጭ ያሉበትን ሁኔታ የማረጋገጥ ሥራም እየተሰራ ይገኛል:: በዚህም አርሶ አደሩ ዘንድ በኑሮው በቤተሰቡ ላይየሚታይ ውጤት እያመጣ እና ለውጥ ያስመዘገበበትና ተጠቃሚ መሆን የጀመረበት ሁኔታም ተፈጥሯል፡፡
ይሁን እንጅ እነዚህ ለውጦች ቢኖሩም የመረጃ አያያዝና ቅብብሎሹ ክፍተት ያለበት መሆን፣ በአርሶ አደሩ ዘንድ ተፈላጊውን ክህሎትና ግንዛቤ በመፍጠርና ተገቢውን የኤክስቴንሽን አገልግሎት በመስጠት በኩል ውስንነት መኖር፣ ከቀበሌ እስከ ዞን ድረስ ያለው ቅንጅታዊ አሰራር የተጠናከረ አለመሆንና የመሳሰሉት ክፍተቶች ስላሉ ማዕከሉ እነዚህን ክፍተቶች ለመሙላት በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራ ይገባል፡፡
የማዕከል ስራ አስኪያጅ
ስም አቶ
ስልክ ቁጥር:(058…)
ፋክስ:(058…)
ፖ.ሳ.ቁ፡
ኢ-ሜይል፡