ዜና
የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የ2013 በጀት ዓመት የዝርያ ማሻሻል አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል እቅድን ገመገመ፡፡
ኤጀንሲው ከ 12-13/1/2014 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ባካሄደው መድረክ የደ/ጐንደር፣ ምስ/ ጐጃም እና የአዊ ዞን ተ/ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች ፤ የወረዳ ተ/ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ፤ ቡድን መሪዎች እንዲሁም የእርባታ ባለሙያዎችና የአዳቃይ ቴክኒሻኖች በተገኙበት የ2013 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል እቅድ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበው ሰፊ ወይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በውይይቱም በአፈፃፀም ረገድ ክፍተት የሆኑ ችግሮች በተሳታፊዎች በኩል የቀረቡ ሲሆን በኤጀንሲው የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በኩል ይህን ሊፈታ የሚችል ማብራሪያዎችና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በመስራት እና ለቀጣይ ስራ መነቃቃትን በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል፡፡በድራት ሆርሞን የታገዘ የዳ/ከብቶች ድቀላ.ppt
ዜና
የተሻሻለ የቤተሰብ ደሮ እርባታ የሙከራ ትግበራ የሚተገበርባቸዉ ሞዴል መንደሮች በተመለከተ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ
የፌደራል ግብርና ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ የተሻሻለ የቤተሰብ ደሮ እርባታ የሙከራ ትግበራ ለሚካሄድባቸዉ ወረዳዎች እና የተመረጡ ሞዴል መንደሮች በተመለከተ የሚመለከታቸዉ አጋር አካላት በተገኙነበት ግንቦት 25/2013 በባህርዳር ከተማ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ አካሄደ፡፡
በመድረኩ በግብርና ሚኒስቴር የደሮ እርባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኑት ወ/ሮ ጽጌረዳ ፍሬዉ የሙከራ ፕሮጀክቱን አስመልክቶ መነሻ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡
ዜና
የቻግኒ የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያና ጥበቃ ማዕከል የ10 ሚሊዮን ብራ ድጋፍ ተደረገለት፡፡
የኢፊድሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ፣ ፣የብሄራዊ ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስራት ቴራ እንዲሁም ከምርምር ፣ ከATA ፣ከLFSDP ፕሮጀክት የመጡ የስራ ሃላፊዎች በ24/09/2013 ዓ.ም ቻግኒ የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያና ጥበቃ ማዕከል የስራ እንቅስቃሴ በመስክ እና በቢሮ ደረጃ ጎበኙ፡፡
ጎብኝዎች በመስክና በቢሮ ደረጃ ከቀረበው ሪፖርት ተነስተው ማዕከሉ ወደ ተሻለ የስራ ደረጃ ሊያሳድጉት በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ወይይት ተደርጓል ፡፡
ዜና
የአለም የወተት ቀን በደማቅ ሁኔታ በአገር አቀፍ ደረጃ በአማራ ክልል ተከበረ፡፡
በአለም ለ21ኛ ጊዜና በኢትዮጵያ ለ5ኛ ጊዜ በፈረንጆች አቆጣጠር በየአመቱ June 1 በሃገራችን ግንቦት 24 የሚከበረው አለም አቀፍ የወተት ቀን “ቀንዎን በአንድ ብርጭቆ ወተት ይጀምሩ” በሚል መሪ ቃል በአማራ ክልል በዳንግላ እና በባህር ዳር ከተማ በመስክ ጉብኝትና በፓናል ውይይት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡
በበአሉ የኢፊድሪ ግብርና ሚኒስቴር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ፣የብሄራዊ ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስራት ቴራ እና ጥሪ የተደረገለቸው ከክልሎች ፣ ከዩንቨርስቲዎች እና ከምርምር ተቋማት የተገኙ የስራ ሃላፊዎች ፣ ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል፡፡
ዜና
የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የ3ኛው ሩብ ዓመት የዋና ዋና ስራዎች አፈፃፀም ገመገመ፡፡
በመድሩኩ የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም በሪፖርት ከመቅረቡ በተጨማሪ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የሆኑ ሴክተር መ/ቤቶች በሩብ አመት ያከናወናቸውን ስራዎች በሪፖርቱ አቅርበዋል ፡፡ በቀረበው ሪፖርት ቤቱ በስፋት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን የቀጣይ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡
- በሌቭል 1 ደረጃ ያሉ ተጠቃሚዎች ውጤታማ ከማድረግ አንፃር የእንስሳት ሃት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ተቋም ከእርባታ እና ከጤና አንፃር የሚሰሩ ስራዎችን በመለከተ ችግር ፈች ድጋፍ እንዲያደርግ፡፡
ዜና
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሃብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክትና ማህበራት በዶሮ እርባታ፣ በቀይ ስጋ ፣ በወተትና በዓሣ ሃብት ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ማህበራት ውጤታማነትን አስመልክቶ ምክክር አካሂደዋል፡፡
የምክክሩ ዓላማ በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት ስራቸውን በእቅድ እንዲመሩ ማስቻል፤ ከሸማቹ የገበያ ትስስር መፍጠር ፣ የተሻለ ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ማስቻልና መደገፍ እንደሆነ የአማራ ክልል የኀብረት ስራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ኃላፊ ኃይለልዑል ተስፋ ተናግረዋል፡፡
“አምራችና ሸማች ጥብቅ ትስስር መፍጠራቸው ለሀገር እድገት መሰረት ነው” ያሉት ኃላፊው ሁለቱ አካላት ትስስር የማይፈጥሩ ከሆነ ተጠቃሚ የሚሆነው ሕገ ወጥ ደላላው ብቻ ነው ብለዋል፡፡
ሸማቹ የሚፈልገው የምርት ጥራት ፣አይነት፣ብዛትና ጊዜን በአግባቡ መረዳት አምራቹን ስኬታማ ያደርጋል፤ ለዚህም በየወቅቱ መነጋገር እንደሚያስፈልግ አቶ ኃይለልዑል አስገንዝበዋል፡፡
ዜና
ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች (ፒፒአር) በሽታ ምንነት ፤ መተላለፊያና መከላከያ መንገዶች እንዲሁም በሽታውን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ የምዕራብ አማራ ክፍል ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ ቁጥጥር አሰተባባሪ ከአቶ ኤሌያስ ደምሴ ጋር የተደረገ ቆይታ
ዜና
የባ/ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እስመልክቶ ከላብራቶሪ ስራ አስኪያጅ ከአቶ ወንደሰን ቁምላቸው ጋር ያደረግነው ቆይታ
- በሰሜን ጎንደር ዞን አዲ-አርቃ ወረዳ በሳንቅ ብስኒት ቀበሌ ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ (ፒፒአር) የክትባት አገልግሎት ሲሰጥ
- በአማራ ክልል የተሻለ የእንስሳት ማድለብ ስራ እንቅስቃሴ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን እና ባለሃብቶችን ምርጥ ተሞክሮዎች
- በአማራ ክልል የተሻለ የዶሮ ሃብት ልማት ስራ እንቅስቃሴ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን እና ባለሃብቶችን ምርጥ ተሞክሮዎች
- በአማራ ክልል የተሻለ የወተት ሃብት ልማት ስራ እንቅስቃሴ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን፤ባለሃብቶችንና አርሶ አደሮችን ምርጥ ተሞክሮዎች