ወ/ሮ ጽላተማርያም ተመስገን ይባላሉ በጎንደር ከተማ በንብ እርባታ ስራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ ::
ዮናታን አስቴርና ጓደኞቻቸው የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ
የኮምቦልቻ ከተማ ለዶሮ ሃብት ልማት ተስማሚ የሆነ የአየር ንብረት ያላት ከተማ ናት ። በከተማዋ በርካታ የህብረተሰብ ክፍሎች በግልና በኢንተርፕራይዝ በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው ተጠቃሚ ሆነዋል ።
ከነዚህም መካከል ዮናታን አስቴርና ጓደኞቻቸው የእንቁላል ጣይ ዶሮ እርባታ ኢንተርፕራይዝ ተጠቃሽ ነው ። የኢንተርፕራይዙ ሰብሳቢ ዶ/ር ዮናታን ብርሃኑ ይባላል ። ዶ/ር ዮናታን በእንስሳት ህክምና ሳይንስ የመጀመሪያ ድግሪውን የተመረቀ ሲሆን ወጣቱ የመንግስትን የስራ ቅጥር ሳይጠብቅ ከጓደኞቹ ጋር በመሆን በኢንተርፕራይዝ በመደራጀት በዶሮ ሃብት ልማት ስራ 1300 የአንድ ቀን ጫጩት በመያዝ ከተማ አስተዳደሩ ባመቻቸው ሸድ ወደ ስራ የገባ ታታሪ ወጣት ነው ። ዶ/ር ዮናታን እና ጓደኞቹ የዶሮ ሃብት ልማት ኢንተርፕራይዝ ባላቸው ሙያዊ እውቀትና የከተማ አስተዳደሩ ሙያተኞች በሚያደርጉላቸው ያላሰለሰ ሙያዊ ድጋፍ በመታገዝ አሁን ላይ ከ5000 በላይ የእንቁላል ጣይ ዶሮዎችን ተጨማሪ ሳይቶችን በመከራየት እየሰሩ ይገኛል ።
በሌማት ቱርፋት በጎንደር ፤ በኮምቦልቻ እና በደሴ ከተማ የተከናወኑ ስራዎች በአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በተለያዩ ዘርፎች የተሰሩ ሰራዎች
ነዋሪነታቸው በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ የሆኑትና በወተት ላም እርባታ የተሰማሩት ወ/ሮ ፀሀይንሽ ግዛው ስራውን በአንድ ላም እና ከአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ባገኙት 20 ሽህ ብር ብድር ነው። እኒህ ታታሪ ግለሰብ አሁን ላይ ከ 30 በላይ የወተት ላሞች ያሏቸው ሲሆን በቀን ከ 400 ሊትር ወተት በላይ በደሴ ከተማ ባሉ 7 ቅርንጫፎች ለገበያ ያቀርባሉ። ከአካባቢው አርቢዎችም ወተት በመሰብሰብ በገዙት ዘመናዊ የወተት ማጓጓዣ መኪና እስከ አፋር ክልል ድረስ ወተት ለገበያ የሚያቀርቡት እኒህ ታታሪ ግለሰብ አሁን ላይ በጥቅሉ ከ12 ሚሊዮን ብር ያላነሰ ካፒታል አላቸው። የእንሰሳት ሃብት ዘርፍ አዋጭ የስራ ዘርፍ በመሆኑ ወጣቶች፣ ባለሀብቶች እና ሌሎች አካላት በዘርፉ በመሰማራት ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ የእኒህ ታታሪ ሴት ተሞክሮ ትልቅ ትምህርት ይሰጣል ፡፡
ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎችን በሽታ በሚመለከት ከኮምቦልቻና ባህርዳር እንስሳት ቅኝት ጥናትና ምርመራ ላብራቶሪ ዳይሬክተሮች ጋር የተደረገ ቆይታ
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የ1ኛው ሩብ ዓመት የዋና ዋና ስራዎች አፈጻጸም በሚመለከት ለሚዲያ ተቋማት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ
- የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ግብርናዉን ከመደገፍ ባለፈ የስርአተ ምግብ ለዉጥ በማምጣት የክልላችንና የሀገራችን የገቢ ምንጭ ሆኗል።
- የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የ2016 ዓ.ም የእቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት አመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ::
- በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ በይካቲት ወር የሚዲያ ሽፋን ያገኙ ስራዎች
- የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ከእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በደረጃ ሶስት ተጠቃሚ ከሆኑ 5 ስፒሻላይዝድ ኮፕሬቲቭ እና ዩኔኖች ጋር ፕሮጀክቱ በሚያደርግላቸው ድጋፍ እና ከፕሮጀክቱ ድጋፍ በፊት በቅድመ ዝግጅት መሰራት በሚገባቸው ስራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ ፡፡