Amhara Livestock and Fisheries Resources Development Office
Niga Yesmaw

full name

Nega Yismaw

Working Jobs

Deputy Head

Office phone

058 320

Fax

058 320

Email

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it

Office number

 

  

የምክትል ኃላፊ መልዕክት

ሀገራችን ኢትዮጵያ በእንስሳት ሃብቷ ከዓለም ዓቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ድርሻ ያላት ሲሆን ዘርፉ ለግብርናው ጂዲፒ (GDP) 47 በመቶ እንዲሁም ለአጠቃላይ ጂዲፒ (GDP) 22 በመቶ እና ለውጭ ንግዱ 19 በመቶ አስተዋጽኦ እንዳለው የተለያዩ ጥናቶች መለክታሉ፡፡ በመሆኑም የግብርና ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ፣ ድህነትን ለመቀነስና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ዘርፉ የጎላ አስተዋጽኦ እንዳለው ይታመናል፡፡ (IGAD and FAO sat)

የክልሉ እንስሳት ሀብት ከአገር አቀፍ ድርሻው 28.6% ሲሆን በማዕከላዊ ስታስቲክ የ 2017/18 መረጃ መሰረት በክልሉ 16.14 ሚሊዮን የዳልጋ ክብቶች (26.7% ) 11.1ሚሊዮን በጎች     (35.4%) 7.7 ሚሊዮን ፍየሎች (23.7%) 3.99 ሚሊዮን የጋማ ከብቶች (35.3%) 0.15 ሚሊዮን ግመሎች (10.7%) እና 19.8 ሚሊዮን ዶሮዎች (33%) እና 1.15 ሚሊዮን ህብረ-ንብ (17.7%) እንዲሁም በክልሉ በሚገኙ ወንዞችና ሀይቆች በአመት ከ 30.000 እስከ 40.000 ቶን በላይ የዓሣ ምርት ማምረት የሚቻልበት ክልል መሆኑን የመረጃ ምንጮች ያመላክታሉ (CSA 2017/18)

ኤጀንሲዉ በደንብ ቁጥር81\2003ዓ.ም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የእንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊ ኤጀንሲ የክልል መስተዳድር ምክርቤት ደንብ ተቋቁሟል፡፡

በአማራ ብሄራዊ ክልል ዉስጥ የተለያዩ ፖሊሲዎችና ሰትራቴጅችን ተግባራዊ በማድረግ      ፈጣንና ቀጣይነት ባለዉ የኢኮኖሚ እድገት ዉስጥ የእንስሳት ሃብትን በመጠበቅ በመንከባከብና በማልማት ከፍተኛ ዉጤት ማስገኘት እንዲቻል ለማድረግና የእንስሳት ሃብት ልማትና ጤና ጥበቃ ስራዎችን በባለቤትነት የሚመራ አካል ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፡

 በክልሉ ዉስጥ የሚገኘዉን የእንስሳት ሃብት በተሻለ ሁኔታ ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲቻል ለዘርፉ ልማት ማነቆ የሆኑትን የዝርያ ምርታማነት አነስተኛ መሆን የመኖ አቅርቦት ጥራት መጓደል  የበሽታ መስፋፋትና የገበያ እጥረት ለመግታትና ለመቅረፍ  የእንስሳት ሃብት ጤና አጠባበቁ ለእድገታችን ወሳኝ ሚና ያለዉ መሆኑ ስለታመነበት፤

የክልሉን የእንስሳት ሃብት ልማትና ጥበቃዉ ዘላቂነት ባለዉ መልኩ እንዲጓዝ የሚደረገዉን የልማት ጥረት ከማገዝ ጎን ለጎን በየጊዜዉ ከዘርፉ ከወጡና የሚወጡ ፖሊሲዎች ፤ ስትራቴጅዎች፤ ደንቦች፤ መመርያዎችና ፕሮግራሞች ከገጠር ልማት ፖሊሲና ሰትራቴጅ ጋር ማጣጣምና ዉጤት ማስመዝገብ በማስፈለጉ፤

የእንስሳት ዉጤቶችንና ግብአቶችን ንግድ ዝዉዉር ማስፈጸሚያ መመሪያዎችን በመቅረፅ በማሻሻልና በመተግበር ህጋዊ አሰራር እንዲሰፍን የሚያደርግና የሚከታተል ተቋም ማደራጀት ተገቢሆኖ በመገኘቱ ክልላችን በእንስሳት ሃብት በሃገርና በዉጭ ንግድ ተወዳዳሪ ሆኖ እንዲገኝ ለማድረግ ተከታታይ የእንስሳት በሽታዎች ቅኝት ጥናት ቁጥጥር በማካሄድ ደረጃ በደረጃ ነጻ የበሽታ ቀጠና አካባቢዎችን ለመፍጠርና እንዲሁም የእንስሳት ኳራንቲን  አገልግሎት መስጫ ጣቢያና የቁጥጥር ኬላዎችን በማቋቋም የበሽታ ቁጥጥር ስራዎችን  ማጠናከር በማስፈለጉ፤

የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር ምክርቤት በተሸሻለዉ ብሄራዊ ክልሉ ህገመንግስት አንቀጽ58 ንዑስ አንቀጽ7 ድንጋጌ ስር በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት የእንስሳት ኤጀንሲን ደንብ አዉጥቷል፡፡

ኤጀንሲዉ የሴቶችና የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በአመታዊ እቅዱ በማካተት በጣም በርካታ ስራወችን አየተገበረ መሆኑ የሚታወቅ ነዉ ይህ ሲባል የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር ትልቁን ድርሻ ወስዶ መስራት የሚጠበቅበት መሆኑን

በመረዳት በተለያዩ ፕሮጀክቶች እንዲሁም በመደበኛ በጀት በመታገዝ የሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ፡፡ በርካታ ለዉጥም አምጥቷል ፡፡

በክልሉ ዉስጥ ኤጀንሲዉ እራሱን የቻለ መዋቅራዊ አደረጃጀት ያለዉ በመሆኑ ከቀበሌ እስከ ክልል የኤክስቴንሽን አደረጃጀቶችን በመጠቀም አርሶ አደሩን በማነቃነቅ ወደ ተጨባጭ ለወጥ ማስገባት ስለተቻለ አበረታች ለዉጦች በመታየት ላይ ናቸዉ፡፡ ይሁን እንጅ ይህን ያህል ሃብትና ፀጋ ያለዉ ክልል  ባግባቡ ያለዉን እምቅ አቅም አሟጦ በመጠቀም ህዝባችን ከድህነት በማዉጣት በኩል የተሰራዉ ስራ አባይን በጭልፋ እንደመቅዳት የሚቆጠር ነዉ፡፡

ስለሆነም በቀጣይ የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ  ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ ተቀራርቦ እና ተመካክሮ በመስራት በተጨባጭ መረጃ ላይ በመመስረት የክልሉን ህዝብ በእንስሳት ሃብት ልማቱ ዘርፍ ቀዳሚ ለማድረግ የሚጠበቅበትን ማበርከት ይሆናል፡፡ እንስሳት እርባታ ሲታሰብ ቀዳሚዉ ከላይ እንደተገለጸዉ  የመኖ ልማት፤ዝርያ ማሻሻል እና የእንስሳት ጤና መከላከልና መጠበቅ የማይታለፉ ተግባሮች ናቸዉ፡፡ ስለሆነም የክልሉን ማህበረሰብ በተገቢዉ መንገድ ሰለመኖ ማሻሻልና በተለያዩ አማራጮች መኖ ማልማት ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ ከዘልማዳዊ የመኖ አመራረትና ልቅግጦሽን በማስቀረት  አርሶ አደሩ በመኖ አያያዝ እራሱን እንዲያዘምን በማድረግ መኖን እንዲያሻሻሽል መስራት ለነገ የማይባል ተግባር ነዉ፡፡

 ከእንስሳት ጤና አኳያም አርሶ አደራችን እንስሳቱን ከማሳከም ይልቅ ከመታመማቸዉ በፊት የመከላከልስራ በመስራት ጤንነታቸዉ የሚጠበቅበትን ሁኔታ ማሰብ መቻል አለበት ይህን ስራ ዉጤታማ ለማድረግ በየደረጃዉ ያለዉ ባለሙያና አመራር ሌት ተቀን ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በትጋት በመስራት ሳይማር ያስተማረዉን ማህበረሰብ ማገልገል ይጠበቅበታል፡፡

ይህ ሲሆን ብቻ የክልላችን ማህበረሰብ በእንስሳት ሃብት ልማቱ የተሸለ እርቀት እንዲጓዝ ማድረግ ስለሚቻል ቅድሚያ ለሚሰጣቸዉ ተግባራት ቅድሚያ በመስጠት ለጋራ ተጠቃሚነት ልንረባረብ ይገባል፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |