Amhara Livestock and Fisheries Resources Development Office

Gashaw Muche01

full name

Dr. Gashaw Muche

Working Jobs

Head Office

Office phone

058 220

Fax

058 320

Email

This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it

Office number

 

 

የዋና ኃላፊ መልዕክት

የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በደንብ ቁጥር 81/2003 ዓ.ም በክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ውሳኔ መሰረት የተቋቋመ ሲሆን ክልላችን ለእንስሳት ሃብት ልማት ምቹ የሆነ የአየር ንብረት ያለው ከመሆኑም በተጨማሪ እንደ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ 2015/2016 ጥናት በክልላችን 15454923 ዳልጋ ከብት 9797248 በግ 6085912 ፍየል 19958894 ደሮ 3478747 የጋማ ከብት 1328235 የንብ መንጋ 63500 የግመል ሀብት ያለ ቢሆንም በህ/ሰቡ ኋላቀር የሆነ የአረባብ ዘዴ ጋር ተያይዞ በሚስተዋሉ ምርታማ ያልሆኑ ዝርያዎች ቁጥር ላይ ብቻ አተኩሮ የመስራት፣ መኖን በተገቢው መልኩ አልምቶ በአግባቡ ያለመመገብ እንዲሁም የእንስሳትን ጤና በተገቢው መልኩ ከመጠበቅ አንጻር በሚስተዋሉ ችግሮች ምክንያት ህ/ሰቡም ሆነ ሀገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት ያለባትን ጥቅም እንዳታገኝ አድርጓት ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ኤጀንሲው እነዚህን መሰረታዊ የሆኑ የዘርፉ ልማት ማነቆዎችን በመፍታት ሃገሪቱም ሆነ በዘርፉ የተሰማራው የህ/ሰብ ክፍል በተለይም ወጣቶችና ሴቶችን በዚህ ዘርፍ ተሰማርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ በየደረጃው በዘርፉ ልማት ጋር ተያይዞ በሚታዩ የአመለካከት፣ የክህሎት፣ የአሰራርና ግብአት አቅርቦት ችግሮችን ለመፍታት እንዲቻል በተቀመጠው የሲቪል ሰርቫንቱ እና የአርሶ አደሩ የልማት ሰራዊት አደረጃጀቶች በሚፈለገው ደረጃም ባይሆን ስራዎችን ለመስራት ጥረት ተደርጓል፡፡ ወደ ፊትም እነዚህን አደረጃጀቶች የማጠናከር ስራ ይሰራል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከአመራሩ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የአመለካከት ችግሮችን ለመፍታት ባለፉት አመታትና በያዝነውም በጀት አመት መድረኮችን ፈጥሮ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ የተሰራ ሲሆን በተመሳሳይ በየደረጃው ካሉ የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ተያይዞ የሚታዩ የክህሎት ችግሮችን ለመፍታት በተደረጉ ጥረቶች በሚፈለገው ደረጃም ባይሆን አንጻራዊ የሆኑ ለውጦችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ ወደ ፊትም ይህ ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ ኤጀንሲው የዘርፉን ልማት በማዘመን ህ/ሰቡን እና ሃገሪቱን ከዘርፉ ልማት ይበልጥ ተጠቃሚ  ለማድረግ ከሚሰራቸው የአቅም ግንባታ ስራዎች በተጨማሪ በግብዓት አቅርቦትም የተሻለ ምርት መስጠት የሚችሉ እንስሳትን ለተጠቃሚው የህ/ሰብ ክፍል እንዲቀርቡ በማድረግ እንዲሁም የተለያዩ የዝርያ ማሻሻል ቴክኖሎጅዎችን ስራ ላይ በማዋል ህ/ሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡ ወደ ፊትም በዚህ ዙሪያ የሚስተዋሉ የአመለካከት የክህሎትና የግብአት አቅርቦት ችግሮችን በመፍታት የዝርያ ማሻሻል ስራዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ስራው በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡

ሌላኛው የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ኤጀንሲው ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ የእንስሳት መኖ ልማትና ስነ አመጋገቡን የማሻሻል ስራ ነው፡፡ በዚህ ረገድም አርሶ አደሩ ከተለመደው የልቅ ግጦሽ አመጋገብ ወጥቶ የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርት እንዲመግብ፣ አግሮ ኢኮሎጅውን መሰረት ያደረገ የእንስሳት መኖዎችን እንዲያለማ ከሰብል ተረፈ ምርት የሚያገኘውን የእንስሳት መኖ በተለያዩ ቴክኖሎጅዎች ተበይነቱን አሻሽሎ እንስሳቶችን መግቦ የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማድረግ የማስፈጸሚያ እስትራቴጅዎችን አስቀምጦ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በተሰሩ ስራዎችም እንደ ሜጫ ያሉ ወረዳዎች አበረታች ውጤቶችን በማስመዝገብ ህ/ሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ ይህን ስራ በሁሉም የክልሉ  አካባቢዎች እንዲሰፉ ለማድረግ የተሰሩ ስራዎች ቢኖሩም በባለሙያና በአርሶ አደሩ በሚታዩ የክህሎትና የአመለካከት ችግሮች ምክንያት የመኖ ልማት ስራችን በሚፈለገው መጠን ውጤታማ አይደለም፡፡ ይህን ለመቀየርም በቀጣይ የተጠናከረ ስራ ይሰራል፡፡

ሌላኛውና ዋነኛው የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ኤጀንሲው ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው ስራዎች ውስጥ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ስራዎች ናቸው፡፡  በዚህም ኤጀንሲው እንደ ስትራቴጅ መከላከልን መሰረት ያደረገ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ስራ እየሰራ ሲሆን በዚህም ካላንደርን መሰረት ያደረገ የእንስሳት ክትባት አገልግሎት ለህ/ሰቡ ተደራሽ የማድረግ ስራዎች እየተሰሩ ከመሆኑም በተጨማሪ በክልሉ ባሉ ሁሉም ቀበሌዎች የእንስሳት ጤና ኬላዎች በመንግስትና በህ/ሰቡ ተሳትፎ እንዲገነቡና ባለሙያና የህክምና ቁሳቁስ እንዲሟላላቸው አቅጣጫ ተቀምጦ በክልላችን ከሚገኝ 3380 ቀበሌዋች ውስጥ 2454 የእንስሳት ጤና ክሊኒኮች ተገንብተዋል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ 2049 ያክሉ ባለሙያና ቁሳቁስ ተሟልቶላቸው የእንስሳት ህክምና አገልግሎት ለህ/ሰቡ በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ኤጀንሲው ከእንስሳት መድሃኒት አቅርቦት ጋር ተያይዞ በየደረጃው ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ችግሩን ለክልሉ መንግስት አቅርቦ የክልሉ ምክር ቤት በወሰነው ውሳኔ መሰረት በክልል ደረጃ ከ110 ሚሊዮን ብር በጀት ከሪቮልቪንግ ፈንድ ተመድቦ በየአመቱ ለመድሃኒት መግዣ እንዲውል ተደርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች ለእንስሳት መድሃኒት መግዣ   1 ሚሊዮን ብር ከሪቮልቪንግ ፈንድ መድበው የእንስሳት መድሃኒት እንዲገዛ በወሰነው መሰረት በክልሉ የሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች በክልሉ መንግስት የተወሰነውን 1 ሚሊዮን ብር በተሟላ ሁኔታም ባይወስኑም ካላቸው በጀት በማንሳት ለእንስሳት መድሃኒት መግዣ መድበው ስራ ላይ እንዲውል አድርገዋል፡፡ ኤጀንሲዉ በበጀት አመቱ በልዩ ትኩረት ይዞ ከሚሰራቸዉ ስራዎች አንዱና ዋነኛዉ የዘርፉን ልማት በጥራትና በብዛት ምርታማነቱን ለማሳደግና የወጣቶችና ሴቶችን የስራ አጥነት ችግር ፈትቶ ወጣቶችና ሴቶችን በዘርፉ ልማት በስፋት ወደስራ ለማስገባት በበጀት አመቱ የአካባቢን ፖቴንሻል መሰረት ያደረገ የእንስሳት ክላስተር ኮሞዲቲ እቅድ አቅዶ ወደ ስራ የገባ ሲሆን በዚህም ለአቅዱ ተፈጻሚነት ድርሻ ያላቸዉ በየደረጃዉ ያሉ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጠንክረዉ በሰሩባቸዉ አካባቢዎች አበረታች ጅምር ለዉጦች የተስተዋሉ ሲሆን እንዚህን ለዉጦች በእቅድ በተያዙ ሁሉም አካባቢዎች ለማስፋት ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡

 

በአጠቃላይ ኤጀንሲው የዘርፉን ልማት ለማዘመን እና አገሪቱም ሆነ ህ/ሰቡ ከዘርፉ ልማት በሚፈለገው መጠን ተጠቃሚ እንዳይሆን የሚያደርጉ ከዝርያ ማሻሻል፣ ከተሻሻለ መኖ ልማትና አመጋገብ እንዲሁም ከእንስሳት ጤና አጠባበቅ ጋር ተያይዞ የሚታዩ ማነቆዎችን ለመፍታት እና ህ/ሰቡ ሳይንሳዊ የሆነ የአረባብ ዘዴ ተጠቅሞ ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል በሚሰሩ ስራዎች የክልላችን ህዝብና መንግስት እንዲሁም ባለድርሻ እና አጋር አካላት የተለመደ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ በዚህ አጋጣሚ ጥሪየን አስተላልፋለሁ፡፡

 

 

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |