ዜና

የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ከእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በደረጃ ሶስት ተጠቃሚ ከሆኑ 5 ስፒሻላይዝድ ኮፕሬቲቭ እና ዩኔኖች ጋር ፕሮጀክቱ በሚያደርግላቸው ድጋፍ እና ከፕሮጀክቱ ድጋፍ በፊት በቅድመ ዝግጅት መሰራት በሚገባቸው ስራዎች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሄደ ፡፡

በመድረኩ የክልል፣የዞን እና የወረዳ እንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ተ/ጽ/ቤት ፣ የህብረት ስራ ማስፋፊያ ተ/ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች እንዲሁም የ5 ስፒሻላይዝድ ኮፕሬቲቭ እና ዩኔኖች የሰራ ኃላፊዎች እና ከንግድና ገበያ ልማት ተቋም የመጡ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል ፡፡

በመድረኩ ለመነሻ የሚሆን የመወያያ ጹሁፍ በፕሮጀክቱ በኩል ቀርቦል ፡፡ በቀረበው የመነሻ ጹሁፍ መነሻ በማድረግ ከማህበራት እና ከዩኔኖች የመጡ ተወካዮች ሀሳብ ሰጥተዋል ፡፡

በተጨማሪም በየደረጀው ያሉ ከእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ተ/ጽ/ቤት ፣ ከህብረት ስራ ማስፋፊያ ተ/ጽ/ቤት እና ከንግድና ገበያ ልማት የመጡ የስራ ኃላፊዎች እና ሙያተኞች

በቀጣይ የህብረት ስራ ማህበራትና ዩኔኖች የተጠናከረ ስራ ሰርተው ከፕሮጀክቱ ለሚደረገው ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከየተቋሞቻቸው ስራዎች አንጻር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል ፡፡

በመጨረሻም መድረኩ የመሩት ዶ/ር ጋሻው ሙጨ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ፣ አቶ ወልደተንሳይ የክልሉ ከህብረት ስራ ማስፋፊያ ኮሚሽን ኮሚሽነር እና አቶ አበጀ አየሁ የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ም/ኃላፊ በቀጣይ 5ቱ ስፔሻላይዝድ ኮፕሬቲቭና ዩኔኖች በቀጣይ ከፕሮጀክቱ ለእያንዳዳቸው የሚገኘው 11.6 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ የሚገባቸውን ስራዎችና በየተቋማቱ ሊደረጉ የሚደገፉ ድጋፎችን በተመለከተ የማጠቃለያ አቅጣጫ በመስጠት የዕለቱ ውይይት ለቀጣይ ስራ መነሳሳትን በመፍጠር ውይይቱ ተጠናቋል ፡፡

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |