ዜና

በምስራቅ አማራ በእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ በጋራ ፍላጎት ቡድን የተደራጅ ተጠቃሚዎችን ወደ ህብረት ስራ ማህበር ለማሳደግ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ ፡፡

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በምስራቅ አማራ ድጋፍ በሚያድረግባቸው ስድስት ወረዳዎች ደሴ ዙሪያ ወረዳ ፣ ቃሉ ወረዳ ፣ ጉባላፍቶ ወረዳ ፣ ዳዋጨፋ ወረዳ ፣ ሞረትና ጅሩ ወረዳ እና ባሶናወረና ወረዳ በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች ተደራጁ ለሚገኙ 40 (አርባ) የህብረት ስራ ማህበር አባላትና አመራሮች ፣ የህብረት ስራ ማህበራት ገዥዎች ፣ የወረዳ ፕሮጅክት አሰተባባሪዎች ፣ የወረዳ እና የክልል የህብረት ስራ ማስፋፊያ ባለሙያዎች ፣ የእንስሳት እና ዓሳ ልማት ጽ/ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት የግንዛቤ ፍጠራ መድረክ አካሄደ፡፡

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች በደረጃ አንድ (በጋራ ፍላጎት ቡድን) ተደራጅተው ሲሰሩ የቆዩትን በአዲስ መልክ ወደ ህብረት ስራ ማህበር በማሳደግ እና በደረጃ አንድ ተጠቃሚ የነበሩትን ወደ ነባር ህብረት ስራ ማህበራት እንዲገቡ በማስቻል በ2015 ዓ/ም 112 ህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት በፕሮጀክቱ የተቀመጡትን መስፈርቶች በመከተልና በማወዳደር 70 የህብረት ስራ ማህበራትን ለእያንዳንዳቸው 1,580,000 ብር በድምሩ 110,600,000.00 ብር ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡:

የዕለቱን ፕሮግራም የከፈቱት የአማራ ክልል ህብረት ስራ ማስፋፊያ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ የዝና ደስታ በምስራቅ አማራ ፕሮጀክቱ ድጋፍ የሚያደርግባችሁ ወረዳዎች በጦርነቱ የደረሰባችሁን ጉዳት የምታካክሱት ይህ ፕሮጀክት በሚያደርገው ድጋፍ ነው ፡፡ ስለዚህ ሁሉም የማህበራት አባላትና አመራሮች ይሄን ስራ የእኔ ነው በሚል ስሜት መስራት አለባችሁ ፡፡ በዘመናዊ የግብይት ስርዓት ሻጭና ገዥ ውል የሚይዙት ምርት ተመርቶ አይድለም ምርቱ ሳይመረት ነው የግብይቱ ስርዓት ሚያለውቀው ያሉት ም/ኮሚሽነሩ ሻጭና ገዥን በአካል በማገናኘት መብትና ግዴታዎቻቸው ምንድን ነው የሚለውን በማወቅ መስራት አለባቸው ብለዋል ፡፡   

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልሉ ውስጥ ድጋፍ በሚያደርግባቸው 15 ወረዳዎች ውስጥ በ2013/12 ዓ.ም በአራት መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች ላይ የጋራ ፍላጎት ቡድኖችን በማደራጀት ስራዎችን ስራ ቆይቶል ፡፡ ፕሮጀክቱ በቀይ ስጋ (በግና ፍየል ማድለብ) ፣ በዶሮ ሃብት ልማት ፣በዓሳ ሃብት ልማት እና በወተት ሃብት ልማት አርሶ አደሮችን ፣ ወጣቶችን እና ሴቶችን በደረጃ አንድ (በጋራ ፍላጎት ቡድን) በማደራጀት ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ዘሪሁን ገልጸዋል ፡፡

አቶ ሙሉቀን አክለውም ፕሮጀክቱ በ2014 ዓ.ም 33 የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት ወደ ስራ አስገብቷል፡፡ በመቀጠልም በ2015 ዓ.ም ወደ ህብረት ስራ ማህበር የሚያድጉ ነባር እና አዲስ ማህበራት የሚያማላቸውን አምስት መሰረታዊ ነጥቦችን ገልጸዋል ፡፡

  • የተደራጁ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት ህጋዊ ሰውነት ማግኘት አለባቸው(ህጋዊ ሰርተፍኬት መያዝ አለባቸው)
  • ከህብረት ስራ ማህበሩ አባላት የሚጠበቀውን 10% መነሻ ካፒታል ማሟላት አለባቸው
  • የመስሪያ ቦታ ህጋዊ ማረጋገጫ ደብተር መያዝ አለባቸው
  • ወደ ነባር ህብረት ስራ ማህበሩ የሚካተቱ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች መጠን በትክክል የተሟላ መሆን አለበት እና
  • ትክክለኛ ገዥዎች ናቸውን ውል ወስደው ከእናንተ የሚሰሩት የሚሉትን ዋና ዋና ነጥቦችን አንስተዋል፡፡

በመቀጠልም በእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የግብይት እሴት ሰንሰለት ባለሙያ በአቶ መብራቱ ስማቸው የመወያያ ነጥቦች ቀርበዋል ፡፡

è  ወደ ህብረት ስራ ያደጉ አምራቾች ደረጃ ሁለት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የመወዳደሪያ መስፈርቶች እና የማመልከቻ ሂደቶች ዙርያ ለታሳቢ ተጠቃሚዎች ግንዛቤ መፍጠር

è  በፕሮጀክቱ ሚሰጠው ድጋፍስለ ውጤታማ የውል ስምምነት አሰራር ግንዛቤ መፍጠር

è  ህጋዊ የግብይት ኮንትራት ውል ለመፍጠር ምርት አቅራቢና ተረካቢን በማገናኘት ክፍተቶቻቸዉን ለመሙላት ስቻል

è  ባልድርሻና አጋር አካላት ስለሚጠበቅ ተግባርና ሃላፊነትን ለማስገንዘብ

è  እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ምንነት

è  በ2014ዓ/ም ድጋፍ የተደረገላቸው 33 የህብረት ስራ ማህበራት ያሉበት ሁኔታ መገምገም

è  የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች እነማን ናቸው

è  የፕሮጀክቱ ደረጃ 2 ተጠቃሚ ለመሆን መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች

è  የመካከለኛ ንኡስ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚንከተላቸው ቁልፍ ደረጃዎችየሚሉ የመወያያ ጽሁፎች ቀርበዋል ፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት የመወያያ ጽሁፎች ላይ ሰፊ ወይይት ከተደረገባቸው በኃላ በተሳታፊዎች በኩል ለተነሱ ጥያቄወች የዕለቱን መድረክ በመሩት የአማራ ክልል ህብረት ስራ ማስፋፊያ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ የዝና ደስታየእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ዘሪሁን እና በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት አማካሪ አቶ ፈንቴ ቢሻው በኩል በቂ ማብራሪያና መልስ ከተሰጣቸው በኃላ የቀጣይ አቅጣጫወች አስቀምጠው የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል ።

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |