ዜና

በምዕራብ አማራ በእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ በጋራ ፍላጎት ቡድን ተደራጅተው ተጠቃሚዎችን ወደ ህብረት ስራ ማህበር ለማሳደግ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ ::

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች ተደራጁ ለሚገኙ 67 (ስልሳ ሰባት) የህብረት ስራ ማህበር አባላትና አመራሮች ፣ የወረዳ እና የክልል የህብረት ስራ ማስፋፊያ ባለሙያዎች ፣ የእንስሳት እና ዓሳ ልማት ጽ/ቤት አመራሮች እና ባለሙያዎች በተገኙበት የግንዛቤ ፍጠራ መድረክ አካሄደ፡፡

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች በደረጃ አንድ (በጋራ ፍላጎት ቡድን) ተደራጅተው ሲሰሩ የቆዩትን በአዲስ መልክ ወደ ህብረት ስራ ማህበር በማሳደግ እና በደረጃ አንድ ተጠቃሚ የነበሩትን ወደ ነባር ህብረት ስራ ማህበራት እንዲገቡ በማስቻል በ2015 ዓ/ም 112 ህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት በፕሮጀክቱ የተቀመጡትን መስፈርቶች በመከተልና በማወዳደር 70 የህብረት ስራ ማህበራትን ለእያንዳንዳቸው 1,580,000 ብር በድምሩ 110,600,000.00 ብር ተጠቃሚ ለማድረግ ፕሮጀክቱ በትኩረት እየሰራ ይገኛል፡

የዕለቱን ፕሮግራም የከፈቱት የአማራ ክልል ህብረት ስራ ማስፋፊያ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ የዝና ደስታ የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በሚሰራባቸው አራቱ መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች ላይ ማን ከማን ጋር መቀናጀት አለበት የሚለውን የህብረት ስራ የቅድም ስራ መስርት አለበት ብላዋል፡፡ም/ኮሚሽነሩ አክለውም በዘመናዊ የግብይት ስርዓት ሻጭና ገዥ ውል የሚይዙት ምርት ተመርቶ አይድለም ምርቱ ሳይመረት ነው የግብይቱ ስርዓት ሚያለውቀው ያሉት ም/ኮሚሽነር ሻጭና ገዥን በአካል በማገናኘት መብትና ግዴታዎቻቸው ምንድን ነው የሚለውን መስራት አለባቸው ብለዋል ፡፡   

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልሉ ውስጥ ድጋፍ በሚያደርግባቸው 15 ወረዳዎች ውስጥ በ2013/12 ዓ.ም በአራት መሰረታዊ የእንስሳት ዘርፎች ላይ የጋራ ፍላጎት ቡድኖችን በማደራጀት ስራዎችን ስራ ቆይቶል ፡፡ ፕሮጀክቱ በቀይ ስጋ (በግና ፍየል ማድለብ) ፣ በዶሮ ሃብት ልማት ፣በዓሳ ሃብት ልማት እና በወተት ሃብት ልማት አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን እንዲሁም ሴቶችን በደረጃ አንድ (በጋራ ፍላጎት ቡድን) በማደራጀት ሰፊ ስራ ሲሰራ መቆየቱን የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ዘሪሁን ገልጸዋል ፡፡

አቶ ሙሉቀን አክለውም ፕሮጀክቱ በ2014 ዓ.ም 33 የህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት ወደ ስራ አስገብተዋል በመቀጠልም በ2015 ዓ.ም ወደ ህብረት ስራ ማህበር የሚያድጉ ነባር እና አዲስ ማህበራት የሚያማላቸውን አምስት መሰረታዊ ነጥቦችን ገልጸዋል

  • የተደራጁ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራት ህጋዊ ሰውነት ማግኘት አለባቸው(ህጋዊ ሰርተፍኬት መያዝ አለባቸው)
  • ከህብረት ስራ ማህበሩ አባላት የሚጠበቀውን 10% መነሻ ካፒታል ማሟላት አለባቸው
  • የመስሪያ ቦታ ህጋዊ ማረጋገጫ ደብተር መያዝ አለባቸው
  • ወደ ነባር ህብረት ስራ ማህበሩ የሚካተቱ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች መጠን በትክክል የተሟሉ መሆናቸውን እና
  • ትክክለኛ ገዥዎች ናቸውን ውል ወስደው ከእናንተ የሚሰሩት የሚሉትን ዋና ዋና ነጥቦችን ገልጸዋል፡፡

በመቀጠልም በእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የእሴት ሰንሰለት ባለሙያ በአቶ መብራቱ ስማቸው የመወያያ ነጥቦች የቀረበ ሲሆን

 

የመድረኩ ዋና ዓላ

è  ወደ ህብረት ስራ ያደጉ አምራቾች ደረጃ ሁለት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የመወዳደሪያ መስፈርቶች እና የማመልከቻ ሂደቶች ዙርያ ለታሳቢ ተጠቃሚዎች ግንዛቤ መፍጠር

 

è   በፕሮጀክቱ ሚሰጠው ድጋፍስለ ውጤታማ የውል ስምምነት አሰራር ግንዛቤ መፍጠር

 

è  ህጋዊ የግብይት ኮንትራት ውል ለመፍጠር ምርት አቅራቢና ተረካቢን በማገናኘት ክፍተቶቻቸዉን ለመሙላት ስቻል

 

è  ባልድርሻና አጋር አካላት ስለሚጠበቅ ተግባርና ሃላፊነትን ለማስገንዘብ 

 

የግንዛቤ ፈጠራው ዋና ዋና ጭብጦች

 

è  እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ምንነት

 

è  በ2014ዓ/ም ድጋፍ የተደረገላቸው  33 የህብረት ስራ ማህበራት ያሉበት ሁኔታ መገምገም

 

è  የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎች እነማን ናቸው

 

è  የፕሮጀክቱ ደረጃ 2 ተጠቃሚ ለመሆን መሟላት የሚገባቸዉ መስፈርቶች

 

è  ንዑስ ፕሮጀክትን ከተሰጣቸው ትኩረት አንፃር በቅድ ተከተል ማስቀመጥ

      የመካከለኛ ንኡስ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ የሚንከተላቸው ቁልፍ ደረጃዎች

በመጨረሻም በቀረቡት የመወያያ ጽሁፎች ላይ ሰፊ ወይይት ከተደረገባቸው በኃላ በተሳታፊዎች በኩል ለተነሱ ጥያቄወች የዕለቱን መድረክ በመሩት የአማራ ክልል ህብረት ስራ ማስፋፊያ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ የዝና ደስታ እና የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ዘሪሁን በኩል በቂ ማብራሪያና መልስ ከተሰጣቸው በኃላ የቀጣይ አቅጣጫወች አስቀምጠው የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል ።

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |