ዜና

የክልሉ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት   የወል ግጦሽ መሬቶችን ከልሎ በማልማት የተሻለ ተሞክሮ ባለው የምስራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳ  የልምድ ልውውጥ አካሄደ። 

የክልሉ እንስሳት ና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የእንሰሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው ስራዎች ዉስጥ አንዱና ዋነኛው የእንስሳት መኖ ልማትና ስነ አመጋገብን የማሻሻል ስራ ነው። መኖ የወተት፣የስጋ እና የእንቁላል ምርትን ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ አለው።

 

የመኖ ምንጮች በርካታ ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው የወል ግጦሽ መሬቶች ናቸው። እነዚህን የወል ግጦሽ መሬቶች

1 ዘለቄታዊነት እንዲኖራቸው ለማድረግ ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው በማድረግ

2 በአጥር አጥሮ ከንክኪ ነፃ በማድረግ

3 ምርታማነታቸውን የሚጨምሩ አረም የማረም፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ የመጨመር

4 የለማውን መኖ በወቅቱ አጭዶ እንሰሳትን በመመገብ እና ተጠቃሚዎች የሚተዳደሩበት ህገደንብ በማዘጋጀት የተሻለ ተሞክሮ ባለው የጎዛመን ወረዳ የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም ተካሂዷል። በልምድ ልውውጥ ፕሮግራሙ በእናራታና ለቅለቂታ ከ530 ሄ/ር መሬት በላይ ከንክኪ ነፃ ሆኖ የለማ መኖ ተጎብኝቷል።

በጉብኝቱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ለእንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። ዋና አስተዳዳሪው በመልእክታቸው የእንሰሳት ዘርፍ ለኢኮኖሚያችን ከየትኛውም ዘርፍ የተሻለ ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን በመጠቆም ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አፅእኖት ሰጥተው አሳስበዋል።

በመቀጠልም የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙሉሰው ቀሬ በወረዳው ከእንሰሳት ሃብት ልማት አንፃር እየተሰሩ ያሉ ስራዎችና የህብረተሰቡ ተጠቃሚነትን አብራርተዋል።ዋና አስተዳዳሪው አክለውም የመኖ ልማት ስራውን በተመለከተ እንዴት ለዚህ ውጤት እንደበቃ እና የአመራሩ ድጋፍ ምን እንደነበር ለታዳሚዎች አብራርተዋል።

በተመሳሳይ የዞን ተ/ጽ/ቤት ሀላፊው አቶ ጤናው በዞኑ ከመኖ ልማት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን ለተሳታፊዎች ገለፃ አድርገዋል። በተጨማሪም የቀበሌ ሙያተኛና ተጠቃሚዎች በመኖ ልማቱና የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት በተመለከተ ለታዳሚዎች ሰፊ ገለፃ አድርገዋል።

በመጨረሻም በአዳራሽ እንደ ክልል ከመኖ ሀብት ልማት አንፃር እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በውይይቱም መድረኩን የመሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብረሀም አያሌው እና የክልሉ እንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ ነጋ ይስማው የእንሰሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በዋናነት መኖ ልማት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራት እንዳለበት እና ለዚህም ይረዳ ዘንድ የወል ግጦሽ መሬቶችን ከንክኪ ከልሎ ምርታማነታቸውን የሚያሳድጉ ስራዎች መስራት እንደሚገባ ለተሳታፊዎች አፅእኖት ሰጥተው አሳስበዋል። ለዚህም የጎዛመን ወረዳ ተሞክሮ ወደ ሁሉም አካባቢዎች መስፋት እንዳለበትም ጠቁመዋል።

ተሳታፊዎችም በልምድ ልውውጡ ያዩት ነገር ያስደሰታቸው መሆኑን በመጠቆም በቀጣይ ወደ የመጡበት አካባቢ ተሞክሮውን ለማስፋት ተግተው እንደሚሰሩ ቃል በመግባት የልምድ ልውውጥ ፕሮግራሙ ተጠናቋል። በእለቱም የመኖ ችግኝ ተከላ ተካሂዷል።

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |