ዜና

የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻል ስራ በተመለከተ የንቅናቂ መድረክ ተካሄደ ::

በዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻል ስራዎቻችን ላይ ያተኮረ የንቅናቂ መድረክ የክልል፣ የዞን ስራ ሀላፊዎችና ቁጥራቸው 417 የሆኑ አዳቃይ ቴክኒሻኖች በተገኙበት ሀምሌ 1/2014ዓ.ም በደብረታቦር ከተማ ተካሄደ፡፡

የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራባቸው ዋና ዋና ስራዎች አንዱ እና ዋነኘው የዝርያ ማሻሻል ስራ ነው ፡፡

በ2015 በጀት ዓመት ከዝርያ ማሻሻል ስራ ጋር ተይዞ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት በቅድመ ዝግጅት እንዲህ አይነት የንቅናቂ መድረክ መካሄዱ በ2014 በጀት ዓመት በአፈጻጸም ረገድ የነበሩ ውስንነቶችን በተገቢው መልኩ ለይቶ በቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያግዛል ፡፡

በተመሳሳይ ውጤታማ የሆኑ ስራዎችንም በቀጣይ ይበልጥ ተጠናክረው እንዲሄዱ ልምድ የሚወሰድባቸው ይሆናል ፡፡

በመድረኩ የዝርያ ማሻሻል አፈጻጸም ሪፖርትና የቀጣይ አቅጣጫዎች በክልሉ የዝርያ ማሻሻል ባለሙያ በአቶ አህመድ አልቃድር ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል ፡፡

በውይይቱ የተሻለ የፈፀሙ አዳቃይ ቴክኒሻኖች እና ዞኖች ተሞክሯቸውን ያካፈሉ ሲሆን በተቃራኒ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸው አዳቃይ ቴክኒሻኖችና ዞኖች ለአፈፃጸማቸው ማነስ ችግር ናቸው ያሏቸውን ምክንያቶች አስቀምጠዋል ፡፡በውይይቱ በችግር ውስጥም ሆነው የተሻለ የፈፀሙ አዳቃይ ቴክኒሻን ባለሙያዎች ሊመሰገኑ እና የእነሱ ተሞክሮ ወደ ሁሉም አካባቢዎች ሊሰፉ እንደሚገባ ተመላክቷል ፡፡ ለዚህም ሁሉም አዳቃይ ቴክኒሻኖች የተሻለ አፈፃፀም ካላቸው አዳቃይ ቴክኒሻኖች ልምድ በመውሰድ በቀጣይ የ2015 እቅድን ለማሳካት ጥረት ማድረግ እንደሚገባ በውይይቱ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል ፡፡

መድረኩን የመሩት የጽ/ቤቱ ም/ኃላፊ አቶ ነጋ ይስማው በማጠቃለያ መልክታቸው የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከምንሰራቸው በርካታ ስራዎች አንዱና ዋነኛው የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻል ስራ መሆኑን በመጠቆም ለዚህም ስራ ውጤታማነትና የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት የአዳቃይ ቴክኒሻን ባለሙያዎች የሚያነሷቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች ተቋቁመው በችግር ውስጥም ሆነው ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ሙያዊ ሀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል ፡፡

ኃላፊው አክለውም በችግር ውስጥም ሆነው ውጤታማ ስራ ለሰሩ አዳቃይ ቴክኒሻኖች ጽ/ቤቱ ክብር እንዳለው እና በቀጣይም በተሻለ ሁኔታ እውቅና እየሰጠ እንደሚቀጥል ጠቁመዋል ፡፡

በተመሳሳይ ያለ በቂና አሳማኝ ምክንያት ስራ የሚበድሉ አዳቃይ ቴክኒሻኖች በቀጣይ በየደረጃው ባለው መዋቅር በትኩረት ተይዞ የእርሞት እርምጃ እንደሚወሰድ አሳስበዋል ፡፡ ከመልካም አስተዳደር ጋር ተያይዞ ለሚነሱ ጥያቄዎች ጽ/ቤቱ ከመቸውም ጊዜ በተሻለ ምላሽ ለመስጠት እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

በመጨረሻም ከ2015 የዝርያ ማሻሻል ስራዎቻችን አንጻር ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶ የሚገባቸው ስራዎች ዙሪያ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ፡፡

በማጠቃለያም በ2014 በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አዳቃይ ቴክኒሻኖች የምስክር ወረቀትና የገንዘብ ስጦታ በማበርከት መድረኩ ለቀጣይ ስራ መነሳሳት በሚፈጥር መልኩ ተካሂዶ ተጠቋል ፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |