ዜና

አራተኛውን ዙር የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ቁጥጥርና ማጥፋት ዘመቻ ተገመገመ፡፡

በመድረኩ የፊደራል ግብርና ሚኒስቴር ፣ከአጎራባች ክልል ከቤንሻጉል ጉምዝ ክልል እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ፣ከዩኒቨርስቲዎች ፣ የዞንና ወረዳ የሚመለከታቸው ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የክልል ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ እንደሚታወቀው በጎችና ፍየሎች ውሃ በሚጠጡበትና ለግጦሽ አብረው በሚውሉበት ጊዜ በትንፋሽ ስለሚተላለፍ በጎችንና ፍየሎችን በከፍተኛ ደረጃ በመግደል የሚታወቅ በሽታ ነው ፡፡

ይህን በሽታ ለመቆጣጠርና ለማጥፍት በአለም ደረጃ 2030 በኢትዩጽያ ደግሞ 2027 ለማጥፋት ትኩረት ተሰጥቶ በርካታ ስራዎች እንደ ሃገር እየተሰራ መሆኑ ታወቃል፡፡

በውይይት መድረኩ

በፌደራል ደረጃ የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ለመከላከል የተሰሩ ስራዎች፣በምራብና በምስራቅ አማራ የሚገኙ የእንስሳት ጤና ላብራቶሪዎች እንዲሁም የቤንሻጉል ጉምዝ ክልል የአሶሳ እንስሳት ጤና ላብራቶሪ የተሰሩ ስራዎች ቀርበዋል፡፡    

በቀረበው ሪፖርትም በሽታውን ለመቆጣጠር ህብረተሰቡን አሳታፌ በሆነ መልኩ ለመከላከል በግንዛቤ ፈጠራ ፣በስልጠናና በክትባቶቱ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችንና የመጡ ለውጦችን ፣ በክትባት ወቅት ያጋጠሙ ችግሮች እንዲሁም ከችግሮቹ ለመውጣት የተሄደበት እርቀት በሪፖርቱ ቀርቧል። በቀረበው ሪፖርት በተሳታፌዎች ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በመጨረሻም የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ ለመቆጣጠር ለማጥፋት  

 ህገ ውጥ የእንስሳት ዝውውር

   የግንዛቤ ፈጠራ

 ቅንጅታዊ አሰራር

 የመረጃ ልውውጥ ስርዓት

 የግብዓት አቅርቦት እና በተመሳሳይ ጉዳዩች ዙሪያ በቀጣይ ትኩረት ተደርጎ መሰራት እንዳለት በጽ/ቤቱ ሃለፊ የቀጣይ አቅጣጫ በመስጠት የእለቱ ፕግራም ተጠናቋል ፡፡  

የእለቱን መድርክ የክልሉ እንሰሳትና አሳሃብት ጽ/ቤት ሀላፊዎችና የቤንሻጉል ጉምዝ ክልል በመጡ የእንስሳና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ ተመረቷል፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |