ዜና

ታስክ ፎርሱ  2014 በጀት አመት የበጎችና ፋየሎች ደስታ መሰል በሽታ በመከላከል እረገድ የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ።

የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ በጎችና ፍየሎችን በከፍተኛ ደረጃ የሚገድል በሽታ ነው። በሽታውን በአለም ደረጃ 2030 በኢትዪጰያ 2027  ለማጥፍት  ግብ ተጥሎ  በርካታ ስራዎች እንደ ሀገር እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል። እንደ ከልል የበጎችና ፋየሎች ደስታ መሰል በሽታን ለመከላከል በምእራብና ምስራቅ አማራ በሚገኙ ሁለቱ የእንስሳትጤና ላብራቶሪዎች  በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል። በበጀት አመቱ የተሰሩ ስሪዎች አፈፃፀም ተግባሩን በበላይነት እየገመገመ ለሚመራው ታስክ ፎርስ ሁለቱ ላቦራቶሪዎች ሪፖርት አቅርበዋል።  በሪፓርቱ  በሽታዉን ማህበረሰብ  አሳታፊ በሆነ መልኩ  ለመከላከል በግንዛቤፈጠራ፣በስልጠና እና በክትባት ዙሪያ የተሰሩ ሰራዎች ቀርበዋል። በቀረበዉ ሪፖርትም 

ታስክ ፎርሱ ሰፊ ዉይይት በማድረግ 

_ በአፈጻጸም ረገድ  የታዩ ጥንካሬዎች  በቀጣይ ይበልጥ መጠናከር እንዳለባቸዉ እና

_ በቀጣይ ይበልጥ ትኩረት ሊሰጥባቸዉ የሚገቡ ጉዳዮችን እንደሚከተለው አስቀምጧል

1 የችግሩን ስፋት በተገቢዉ መልኩ መለየት እና ለዚህ የሚመጥን የጠራ እቅድ ማቀድ 

2 በእቅዱ ዙሪያ  ከባለድርሻ አካላት ጋር ግልጸኝነት መፋጠር።

3 የተቀመጠውን እቅድ በተያዘው ጊዜ መጠንና ጥራት መፈጸም

4 አፈጻጸሙን በየጊዜው  በታስክ ፎርስና በተቀመጠው አደረጃጀት እየገመገሙ መምራትና ግብረ መልስ መስጠት

5 በሽታውን በመከላከል እረገድ የሚሰሩና እየተሰሩ ያሉ ስሪዎችን በሚድያና በኮምንኪሽን ስራ አጠናክሮ  መቀጠል እና ቅንጅታዊ አሰራርን በየደረጃው  ማጠናከር እንደሚገባ  ታስክፎርሱ አቅጣጫ አስቀምጦ የእለቱ ውይይት ተጠናቋል።

 

መድረኩም በክልሉ እንሰሳትና አሳ ሃብት /ቤት ምክትል ሀላፊ በሆኑት በአቶ ነጋ ይስማው እና በዶ/ ታምሩ ተሰማ የእንሰሳት ጤና ዳይሬክተር ተመርቷል

ታስክ ፎርሱ  2014 በጀት አመት የበጎችና ፋየሎች ደስታ መሰል በሽታ በመከላከል እረገድ የተሰሩ ስራዎችን ገመገመ።

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |