ዜና

የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በእንስሳት ጤና ቅድመ መከላከል ስራዎች ዙሪያ ለሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አካሄደ፡፡

የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የእንስሳትን ጤንነት ለመጠበቅ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱና ዋነኛው ካሌንደርን መሰረት ያደረገ የቅድመ መከላከል ስራ ነው፡፡

ጽ/ቤቱ በጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው 5 ዞኖች ስር ለሚገኙ 1ዐ ወረዳዎች 2ዐዐ ለሚሆኑ የቀበሌ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች በቅድመ መከላል ስራዎች ዙሪያ ከዚህ በፊት የተሰጠውን ስልጠና መሬት ለማስነካት እና ተግባሩ በሚፈፀምበት አሰራር ዙሪያ  የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር የወረዳ አስተዳዳሪዎች የዘርፉ የዞን የወረዳ ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች በተገኙበት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል፡፡

 

በመድረኩ ለውይይት መነሻ የሚሆን ፁሁፍ በክልሉ የእንስሳት ጤና ዳይሬክተር በሆኑት ታምተ ተሰማ ዶ/ር የቀረበ ሲሆን የቀረበውን የመወያያ ፁሁፍ መሰረት በማድረግ ተሣታፊዎች ተግባሩ በሚፈፀምበት ሁኔታ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡ በመጨረሻም እንዲህ አይነት የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በክልሉ መዘጋጀቱ ግልፀኝነት ፈጥሮ ተግባሩን በተቀመጠው ጊዜ ለመፈፀም የሚያስችል መሆኑን በመግልጽ ለተግባራዊነቱም የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃል በመግባት ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |