ዜና

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የ2014 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2015 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ ፡፡

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የሚመለከታቸው የክልል እና የፕሮጀክቱ ወረዳ የስራ ሃላፊዎችና ሙያተኞች በተገኙበት የፕሮጀክቱን የ2014 በጀት ዓመት የዋና ዋና ስራዎችን አፈፃፀም ግምገማ እና የ2015 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ፡፡

የፕሮጀክቱ የዋና ዋና ስራዎችን አፈጻጸም እና የ2015 እቅድ በፕሮጀክቱ Monitering and Evalation ባለሙያ በሆኑት በአቶ እንደሻው ቀርቧል ፡፡

በቀረበው ሪፖርትም ፡-

  • የእንስሳት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሰሩ ስራዎች
  • 33 መሰረታዊ የህብረት ስራን ከማደራጀትና መደገፍ አንጻር የተሰሩ ስራዎች
  • የተቋማትን የመፈጸም አቅም ለማሳደግ መሰረተልማት ከማሟላት ፣ ግብአት ከማቅረብ እና የባለሙያዎችን አቅም ከማሳደግ አንጻር የተሰሩ ስራዎች በሪፖርቱ በዝርዝር ቀርበዋል ፡፡
  • በቀረበው ሪፖርትም ተሳታፊዎች ሰፊ ጊዜ ወስደው ተወያይተዋል ፡፡ በውይይቱም ፕሮጀክቱ በ3ቱ ኮምፖነንቶች እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን የሚበረታቱ እና ወደፊትም ተጠናክረው መቀጠል ያለባቸው መሆኑን በስፋት ተነስቷል ፡፡ እንደችግር እና መስተካከል ያለበት በርካታ የጋራፍላጎት ቡድኖች ወደ መስረታዊ ህብረት ስራ በማምጣት በኩል የተሰሩ ስራዎች ስራ አናሳ መሆኑን ወደ መሰረታዊ ህብረት ስራ የመጡትንም በሚፈለገው ጊዜ በተገቢው መልኩ ደግፎ ወደ ስራ ፈጥነው እንዲገቡ በማድረግ በኩል የተሰራው ስራ አናሳ መሆኑን ተገምግሟል ፡፡

በቀጣየም በእጥረቶች ዙሪያ ይበልጥ ትኩረት ሰጥቶ መሰራት እንዳለበት የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ፡፡ በመቀጠልም በ2015 በጀት አመት በ426 ሚሊዮን ብር በ3ቱ ኮምፖነንቶች የሚሰሩ ስራዎች በፕሮጀክቱ ከቀረበ በኃላ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ተሳታፊዎች ለእቅዱ ተፈጻሚነት የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ የጋራ መግባባት በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል ፡፡

lfsdpselectedkosober (19)

 

lfsdpselectedkosober (10)

lfsdpselectedkosober (11)

lfsdpselectedkosober (7)

lfsdpselectedkosober (12)

lfsdpselectedkosober (18)

lfsdpselectedkosober (25)

lfsdpselectedkosober (27)

lfsdpselectedkosober (30)

lfsdpselectedkosober (31)

lfsdpselectedkosober (32)

lfsdpselectedkosober (3)

 

 

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |