ዜና

ክልላዊ የወተት ቀን በዓል ተከበረ

የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ጽ/ቤት በምዕ/አማራ ክልል፣ የዞን እና የማዕከላት የዘርፉ ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደንግላ ከተማ የወተት ቀን በአልን አክብሯል፡፡

ኘሮግራሙን በንግግር የከፈቱት የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ ዶ/ር ጋሻው ሙጨ ሲሆኑ ሀላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው ክልላችን ሰፊ የሆነ የእንስሳት ሃብት ክምችት ያለው መሆኑን እና ይህንን ሃብትም ለማልማትና በአግባቡ ለመጠቀም በመሰረታዊነት በእንስሳት መኖ ልማትና ስነ-አመጋገብን ማሻሻል፣ በእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እንዲሁም በእንስሳት ጤና አጠባበቅ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተሰሩ ስራዎችን ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል

እነዚህን ውጤታማ ስራዎች ለማስፈፀም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት እንዲህ አይነት ኘሮግራም መዘጋጀቱ አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆም ተሳታፊዎች በቆይታቸው የተመለከቷቸውን ውጤታማ ስራዎች በቀጣይ ወደ የአካባቢያቸው ለማስፊት ትኩረት ሰጥተው መሰራት እንዳለባቸው አፅእኖት በመስጠት አሳስበዋል፡፡

በኘሮግራሙም ሁለት የተመረጡ የእርባታ ጣቢያዎች ተጎብኝተዋል፡፡ እንዲሁም የሂወት የወተት ግብይትና ህብረት ስራ ማህበር የሰራ እንቅስቃሴ ተጎብኝቷል፡፡ በመቀጠልም ለበአሉ ተሳታፊዎች እና ቁጥራቸው ከ100 ላላነሱ ህፃናት ተማሪዎች የወተት ተዋፅኦ ምገባ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

በመጨረሻም በወተት ሃብት ልማት ዙሪያ እንደ ክልል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተመለከተ በክልሉ እንስሳት ተዋፅኦ ባለሙያ በአቶ ደመላሽ አይችሌ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በውይይቱም ተሳታፊዎች በመስክም ባዩት ስራና በመወያያ ፁሑፉ ከቀረበው በመነሳት አስተያየት የሰጡ ሲሆን ተሳታፊዎቹ በመስክ ባዩትና በቀረበው የመወያያ ፁሑፍ በመነሳት ዘረፉን ለማዘመን እንደ ክልል እየተሰራ ባለው ሰራ የሚበረታታ መሆኑን እና በቀጣይም የበኩላቸውን ኃለፊነት በመወጣት የዘርፉን ልማት ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡ በየዞኑ የመጡ የዘርፉ የስራ ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች በዳንግላ ከተማ የወተት ሃብት ልማት ስራን ከተሻሻለ መኖ ልማት ጋር አቆራኝቶ በመስራት የታየው ውጤታማ ተሞክሮ በቀጣይ ወደ ዞናቸው ወስደው ለማስፋት ትልቅ ተሞክሮ ያገኙ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የዕለቱ መርሃ ግብሮችም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ባማረ መልኩ ተከናውኖ ኘሮግራሙ ተጠናቋል፡፡

milk day dangela (10)

 

milk day dangela (44)

milk day dangela (45)

milk day dangela (32)

milk day dangela (8)

milk day dangela (7)

milk day dangela (6)

milk day dangela (5)

milk day dangela (4)

milk day dangela (39)

milk day dangela (40)

milk day dangela (41)

milk day dangela (42)

milk day dangela (43)

milk day dangela (1)

milk day dangela (2)

milk day dangela (3)

milk day dangela (15)

milk day dangela (14)

milk day dangela (13)

milk day dangela (11)

milk day dangela (16)

milk day dangela (29)

milk day dangela (17)

milk day dangela (30)

milk day dangela (23)

milk day dangela (20)

milk day dangela (22)

milk day dangela (18)

milk day dangela (21)

milk day dangela (19)

milk day dangela (24)

milk day dangela (25)

milk day dangela (46)

milk day dangela (47)

milk day dangela (48)

milk day dangela (49)

milk day dangela (50)

milk day dangela (51)

milk day dangela (52)

milk day dangela (37)

milk day dangela (38)

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |