ዜና

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማ ፕሮጀክት ከጋራ ፍላጎት ቡድን ወደ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ያደጉ ማህበራትን አፈጻጸም ገመገመ ፡፡

 የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማ ፕሮጀክት በ2011 በጀት አመት በክልሉ በ15 ወረዳዎች በ4 የእሴት ሰንሰለት ለመስራት ወደ ተግባር ስራ የገባ ሲሆን ፕሮጀክቱ እስከ 2014 በጀት አመት 2700 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች 36851 አባላትን በቀይ ስጋ ፣ በወተት ፣ በዶሮ እና በዓሳ ተጠቃሚዎችን አደራጅቶ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል ፡፡ ከእነዚህ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች አሁን ላይ 82 ህብረት ስራ ማህበራት 5839 ተጠቃሚዎችን በማቀፍ በ4ቱ የእሴት ሰንሰለቶች ተደራጅተው ወደ ስራ ገብተዋል ፡፡

ፕሮጀክቱ የህብረት ስራ ማህበራትን አፈጻጸም ለመገምገም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ4/11/2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ የግምገማ መድረክ አካሄዷል ፡፡

በመድረኩ ሁሉም ወረዳዎች ህብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት ዙሪያ የሰሩትን ስራና ያጋጠማቸውን ችግር በሪፖርት መልክ አቅርበዋል ፡፡ በህብረት ስራ ማደራጃ ኮሚሽን በኩልም ማህበራቱን ከማደራጀት አንጻር የተሰሩ ስራዎችን እና በቀጣይ ሊሰሩ የሚገቡ ተግባራትን በተመለከተ በሪፖርት መልኩ ቀርቧል ፡፡ በቤቱም በቀረቡ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም ፕሮጀክቱ በጋራ ፍላጎት ቡድን ደረጃ በርካታ ወጣቶችና ሴቶችን እንዲሁም አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ማድረጉ በስፋት ተነስቷል ፡፡

ይሁን እንጅ በቀጣይ ቢስተካከሉ የተባሉ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች ወደ ማህበራት በማምጣት በኩል የተሰራው ስራ ጥሩ ቢሆንም አሁንም ድረስ በርካታ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች ወደ ማህበር ያልመጡ በመሆኑ በቀጣይ በዚህ ዙሪያ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ የመጡትንም መመሪያው በሚያዝዘው መሰረት አስፈላጊውን ድጋፍ ተደርጎ ወደ ስራ እንዲገቡ ቢደረግ የሚሉ ሃሳቦች ተነስተዋል ፡፡ በተጨማሪም የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባቸውን የጋራ ፍላጎት ቡድኖች አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው የሚጠናከሩበት ሁኔታ እንዲፈጠርና በቀጣይም ወደ መሰረታው ህብረት ስራ ማህበር እንዲያድጉ የክትትልና ድጋፍ ስራው እንዲጠናከር የሚሉ ዋና ዋና የውይይት ሃሳቦች ተነስተዋል ፡፡

በመጨረሻም ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ኃላፊነት የሚወጡበት በቀጣይ ጊዜያት የሚሰሩ ስራዎችን የያዘ የድርጊት መርሃ ግብር ቀርቦ በዚህ ዙሪያ የጋራ መግባባት ተፈጥሮ የእለቱ ውይይት ለቀጣይ ስራ መነቃቃጥን በመፍጠር ተጠናቋል ፡፡

website gonder (24)

website gonder (4)

website gonder (9)

website gonder (8)

website gonder (6)

website gonder (3)

website gonder (2)

website gonder (30)

website gonder (13)

website gonder (12)

website gonder (11)

website gonder (19)

website gonder (20)

website gonder (21)

website gonder (18)

website gonder (23)

website gonder (1)

website gonder (27)

website gonder (29)

website gonder (31)

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |