የሀዘን መግለጫ

 

melesechየመስሪያ ቤታችን ባልደረባ በሆኑት በወ/ሮ መለሰች መርሻ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሠማንን ጥልቅ ሀዘን እንገልፃለን!

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ባልደረባ የነበሩት ወ/ሮ መለሰች መርሻ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

ቅንና በባልደረቦቻቸው ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት ወ/ሮ መለሰች መርሻ በመስሪያቤቱ ውስጥ በኤክስኪዩቲቭ ሴክሪታሪነት ያገለግሉ ሲሆን በሥራቸው ታታሪና ትጉህ እንዲሁም ሰው አክባሪ ሰራተኛ ነበሩ፡፡

ወ/ሮ መለሰች መርሻ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ምክንያት በባህርዳር ፈለገ ህይወት ሆስፒታል ለህክምና ቢወሰዱም በነበረባቸው የልብ ህመም ምክንያት ሊሻላቸው ባለመቻሉ በህክምና ላይ እንዳሉ ሰኔ 22/2014 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

የቀብር ስነ ስርዓቱም በዛሬው እለት(በ23/10/2014 ዓ.ም) ማሪያም ቤተክርስቲያን ( በመርጡለ ማርያም ከተማ) ይፈፀማል

በወ/ሮ መለሰች መርሻ ድንገተኛ ህልፈተ ህይወት የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቿ ፣ ለሥራ ባልደረቦቿ እና ለወዳጅ ዘመዶቿ መፅናናትን እንመኛለን፡፡

ነፍስ ይማር
የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |