ዜና

የአብክመ ህብረት ስራ ማደራጃ ባለስልጣን ከክልሉ እንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በእንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ፕሮጀክት ድጋፍ በቀይ ስጋ፣በወተት፣በዶሮ እና በአሳ ሀብት ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ የጋራ ፍላጎት ቡድኖችን እና መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራትን ከማደራጀት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ የሁለቱ ተቋማት ሰራተኞች በተገኙበት ገመገሙ።

መድረኩን የከፈቱት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አቶ ወልደተንሳይ ሲሆኑ ሀላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው የእንሰሳት ሃብት ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ገልፀው በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማደራጀት እና የድጋፍ እና ክትትል የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይሰራል ብለዋል። ለዚህም ሁሉም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል።

የእንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ፅፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ዶር ጋሻው ሙጨ በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት በዚህ መልኩ ስራ በጋራ መገምገማቸው ጥንካሬዎችና እጥረቶችን ለይቶ በቀጣይ ስራን ቆጥሮ በመከፋፈል ወደ ስራ ለመግባት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል። ሀላፊው አክለውም ወደፊት ተመሳሳይ መድረኮች እየተፈጠሩ ስራን በጋራ የመገምገም ስራ ይሰራል ብለዋል።

ተሳታፊዎችም እንዲህ አይነት መድረክ መፈጠሩ አስፈላጊ መሆኑን በመጠቆም በቀጣይ በእንሰሳትና አሳ ሃብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ድጋፍ ወደ ስራ የገቡ የጋራ ፍላጎት ቡድኖችን ወደ መሰረታዊ ህብረት ስራ እንዲመጡ የማድረግ እንዲሁም ማህበራትና ዩኔኖችን የማጠናከር ስራ በትኩረት ተይዞ መሰራት እንዳለበት የጋራ መግባባት በመፍጠር የእለቱ ውይይት ተጠናቋል።

cooprative (2)

cooprative (5)

cooprative (4)

cooprative (11)

cooprative (22)

cooprative (6)

cooprative (10)

cooprative (7)

cooprative (14)

cooprative (9)

cooprative (13)

cooprative (15)

cooprative (17)

cooprative (27)

cooprative (25)

cooprative (28)

cooprative (30)

cooprative (31)

cooprative (23)

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |