ዜና

የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በእንስሳት ጤና ለገጠር ልማት (HEARD) ፕሮጀክት በታቀፉ ወረዳዎች ለሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ፡፡ 

heard selected dessi02 (35)ስልጠናው በምስራቅ አማራ ለሚገኙ ዞኖች ዋግኽምራ ብሔረሰብ ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ኦሮሞ ብሔረሰብ  እና ሰሜን ሽዋ ዞን ለሚገኙ የዞንና እንስሳት ጤና ቡድን መሪዎች እና ለወረዳ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የዶሮ ፈንግል ክትባት(NEWCASTLE_DISEASE) አሠጣጥ ዙሪያ የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና በደሴ ከተማ ተሰጠ ።

የዕለቱን መድረክ የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሬክቶሪት ዳይሪክተር ዶ/ር ተምሩ ተሰማ የማህበረሰብ አቀፍ የዶሮ ፈንግል በሽታ አደገኛ የሆነ በሽታ በመሆኑ ሰልጣኞች የሚሰጣቸው የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና በመከታተልና በዶሮ ፈንግል ክትባት አሰጣጥ ዙሪያ በቂ እውቀት በመያዝ በየወረዳዎቻቸው ክትባት የሚሰጡ ሴቶች በመመልመል የወሰዱትን ስልጠና እንዴሰጡ አሳስበዋል ።

የስልጠና ጽሑፉን አዘጋጅተው ያቀረቡት ከባህርዳር ዩኒቨርስቲ የእንስሳት ህክምና መምህር እና የክልሉ እንስሳት ጤና ባለሙያዎች   

• በማህበረሰብ አቀፍ የዶሮ ፈንግል በሽታን (NEWCASTLE_DISEASE) የመከላከያ ዘዴዎች ዙሪያ 

• በማህበረሰብ አቀፍ የዶሮ ፈንግል በሽታ ክትባት አሰጣጥ መመሪያ ዙሪያ እና  

• በአዋቂዎች ስልጠና አሰጣጥ ዘዴ(ADULT LEARNING) ዙሪያ የስልጠና ጹሑፎች እና መመሪያዎች የቀረቡ ሲሆን ሰልጣኞችም የተሰጣቸው የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና የክህሎት ክፍተታቸውን የሞላላቸው ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት የስልጠና ጽሁፎች እና መመሪያዎች ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገባቸው በኃላ በተሳታፊዎች በኩል በተነሱ ዋና ዋና ጥያቄዎች

• ያገባች ሴት ብቻ ለማህበረሰብ አቀፍ ከታቢዎች ብቻ ነው ወይ መሆን ያለበት የመመልመያ መስፈርቱ ቢሻሻል 

• መቸ ነው የክትባት አካሄድ መጀመር ያለበት 

• አንድ ክትባት ከተሰጠ በኋላ ከአንድ ስዓት በላይ መቆየት የለበትም ተብሏል ነገር ግን ከአንድ አርሶ አደር ወደ ሌላ አርሶ አደር ሲዟዟር ከአንድ ስዓት በላይ ከወደ ይችላል እና ምን ማድረግ አለብን

•  ለማህበረሰብ ከታቢዎች 10ኛ ክፍል መመልመያ መስፈርት ሁኖ ተቀምጧል እና እንደየ አካባቢው ሁኔታ ቢታይ  

• ክትባቱን ስናስቀምጥ በ+4°c ብቻ ነው ወይ የሚቀመጠው

• Lasota እንዴት በጡንቻ ይሰጣል ቢብራራ 

ከአዋጭነት አንጻር ጊዜ ስለሚወድ ውጤታማ እንዴት ይሆናል በሚል በተነሱ ጥያቂዎች ዙሪያ የእለቱን መድረክ በመሩት የአማራ ክልል እንስሳት ጤና ለገጠር ልማት (HEARD) ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ውበት ስንሻው እና በክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሬክቶሪት ዳይሪክተር ዶ/ር ታምሩ ተሰማ በቂ ማብራሪያና መልስ ከተሰጣቸው በኃላ የእለቱ የስልጠና ፕሮግራም ተጠናቋል 

heard selected dessi02 (6)

heard selected dessi02 (4)

heard selected dessi02 (3)

heard selected dessi02 (10)

heard selected dessi02 (12)

heard selected dessi02 (21)

heard selected dessi02 (28)

heard selected dessi02 (26)

heard selected dessi02 (24)

heard selected dessi02 (33)

heard selected dessi02 (35)

heard selected dessi02 (42)

heard selected dessi02 (48)

heard selected dessi02 (52)

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |