ዜና

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በእንስሳት ጤና ለገጠር ልማት (HEARD) ፕሮጀክት በታቀፉ ወረዳዎች ለሚገኙ የመንግስትና የግል እንስሳት ጤና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

heard selected DESSI 01 (35)ስልጠናው በምስራቅ አማራ ለሚገኙ ዞኖች ዋግኽምራ ብሔረሰብ ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ኦሮሞ ብሔረሰብ እና ሰሜን ሽዋ ዞን ለሚገኙ የዞንና እንስሳት ጤና ባለሙያዎች እና ለወረዳ የእንስሳት ጤና ብድን መሪ ፣ ለመንግስት እንስሳት ጤና ባለሙያዎች እና ለግል የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች በመንግስትና በግል የእንስሳት ጤና ተቋማት ጥምረት ላይ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችና በግል እንስሳት ጤና ተቋማት ለመሰማራት የወጡ መመሪያዎችን በግልፅ አውቆ በቀጣይ የእንስሳት ጤና አገልግሎት በጋራ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያግዝ ስልጠና በደሴ ከተማ ተሰጠ ፡፡

መድረኩን የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሮክቶሪት ዶ/ር ተምሩ ተሰማ የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በአስር አመት እቅዱ ላይ አሁን ያለውን 10% የሚሸፍነውን የግል የእንስሳት ጤና ተቋማት ለማሳደግ የግል የእንሳሳት ጤና ባለሙያዎችን በማበረታታትና አቅም በመገንባት በቀጣይ 10 ዓመት ውስጥ የግል የእንስሳት ጤና ተቋማትን ሽፋን 35% ለማድረስ አቅዶ እየሰራ ነው ፡፡

ስለሆነም የመንግስትና የግል እንስሳት ክሊኒክ ባለሙያዎች ህብረተሰቡን ሙያዊ ስነመግባር በተሞላበት መስራት እንዳለባቸው እና ከአሁን በፊት የመንግስቱ እንደ ተቆጣጣሪ የግሉ እንደ ጠላት የሚታይበት ስርዓት አቆመን አንዱ ለአንዱ አጋዥ መሆኑን ተገንዝቦ በመቀራረብ ለህብረተሰቡ ማገልገል እነዳለባቸው ገልጸዋል ፡፡

የስልጠና ጽሑፉን አዘጋጅተው ያቀረቡት የክልሉ እንስሳት ጤና ባለሙያዎች እና የእንስሳት መድሒኒትና መኖ ቁጥጥር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት

  • የእንስሳት መድሐኒት የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ችርቻሮ የንግድ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት አሰጣጥ
  • በእንስሳት መድሐኒትና መኖ ችርቻሮ ተቋማት የሚስተዋሉ ችግሮችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች
  • በግል የእንስሳት ጤና ክሊኒክ ፍቃድ መመሪያ አሠጣጥ ዙሪያ ሰፋ ያሉ የስልጠና ጽሁፎችና መመሪያዎች የቀረበ ሲሆን ሰልጣኞችም የተሰጣቸው ስልጠና የክህሎት ክፍተታቸውን የሞላላቸው ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል፡፡
  • በመጨረሻም በቀረቡት የስልጠና ጽሁፎች እና መመሪያዎች ላይ ሰፊ ውይይት ከተደረገባቸው በኃላ በተሳታፊዎች በኩል በተነሱ ጥያቄዎች
  • ከሰው መድሐኒት ቤት የእንስሳት መድሐኒት ይዘው እየሰሩ ስለሆነ በምን መልኩ እንቆጣጠራቸው
  • ምን ያህል ከሊኒኮች ነው በአንድ ቀበሌ መገንባት ያለበት ዝርዝር ሁኔታ ቢቀመጥ
  • አንድ ወረዳ ላይ ክሊኒክ ከፍቶ እየሰራ ሌላ ወረዳ ላይ ቅርንጫፍ መክፈት ይቻላል ወይ
  • በእንስሳት ጤና ሙያ የተመረቁ ነገር ግን ያልጠቀጠሩ ባለሙያዎች ወደ ግሉ ዘርፍ ለማስገባት የብድር አገልግሎት የት እና እንዴት ማግኘት እንዳለባቸው ቢጠቆም
  • አንድ የእንስሳት ጤና ክሊኒክ ሲገነባ ሦስት ክፍል መሆን የነበረበት ቀርቶ ወደ ሁለት ክፍል ዝቅ ብሎ በቀላሉ መስራት ብንችል
  • የመዳሕኒት ኬላ ጣቢያዎች በክልል ብቻ እየተሰጠ ስለሆነ ዞንን አሳታፊ ቢያደርግ እና የመዳህኒትና መኖ ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ዞን ላይ አሳታፊ ቢያደርግ በሚሉ የተነሱ ጥያቂዎች ዙሪያ የእለቱን መድረክ በመሩት የአማራ ክልል እንስሳት ጤና ለገጠር ልማት (HEARD) ፕሮጀክት አስተባባሪ ዶ/ር ውበት ስንሻው እና የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሬክቶሪት ዶ/ር ታምሩ ተሰማ በቂ ማብራሪያና መልስ ከተሰጣቸው በኃላ የእለቱ የስልጠና ፕሮግራም ተጠናቋል ፡፡

heard selected DESSI 01 (2)

heard selected DESSI 01 (20)

heard selected DESSI 01 (19)

heard selected DESSI 01 (4)

heard selected dessi02 (13)

heard selected DESSI 01 (14)

heard selected DESSI 01 (22)

heard selected DESSI 01 (35)

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |