ዜና
በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለወረዳና ለቀበሌ የእንሰሳት ጤና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ ።
Healthy selected (34)የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ከአለም ምግብና እርሻ ድርጅት(FAO) ባገኘው የበጀት ድጋፍ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አራት ወረዳዎች ጠለምት ፣ አዲአርቃይ ፣ ደባርቅ እና ላይ ጋይንት ወረዳ የሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችን ለአምስት ተከታታይ ቀናት በደብረ ታቦር ከተማ ስልጠና ተሰጠ ።ስልጠናውን የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ተሰማ በእንስሳት ጤና ላይ እየተሰሩ የነበሩ ስራዎች በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ በመሆኑ የበሽታ ፍንዳታዎች እየተከሰቱ ስለሆነ የእንስሳት ጤና ባለሙያውን ስልጠና በመስጠት እና የግብዓት አቅርቦት በመስጠት ክትባቶች በዘመቻ መልኩ ለመስጠት የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል ።የስልጠና ጽሑፎን አዘጋጅተው ያቀረቡት የባህርዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ እና የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ የተወጣጡ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች

• በበሽታ ቅኝትና ዳሰሳ

• በእንስሳት በሽታ ክስተት በማህበረሰቡ ላይ የሚያደርስ ጉዳት

• የእንስሳት በሽታ መከላከልና ቁጥጥር እና
• በእንስሳት በሽታ መረጃ አያያዝና ሪፖርት አደራረግ ዙሪያ ሰፋ ያሉ የስልጠና ጽሑፎች የቀረቡ ሲሆን ሰልጣኞችም በተሰጣቸው ስልጠና ከአሁን በፊት የነበረባቸውን የክህሎት ክፍተት የሞላላቸው ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል ። በመጨረሻም በቀረቡት የስልጠና ጽሁፎች ላይ ሰፊ ወይይት ከተደረገባቸው በኃላ በተሳታፊዎች በኩል ለተነሱ ጥያቄወች የዕለቱን መድረክ በመሩት የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ነጋ ይሰማው እና በእንስሳት ጤና ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ተሰማ በኩል በቂ ማብራሪያና መልስ ከተሰጣቸው በኃላ የቀጣይ አቅጣጫወች አስቀምጠው የዕለቱ ስልጠና ተጠናቋል ።
Healthy selected (25)
Healthy selected (7)
Healthy selected (11)
Healthy selected (3)
Healthy selected (17)
Healthy selected (18)
Healthy selected (16)
Healthy selected (12)
Healthy selected (6)
Healthy selected (21)
Healthy selected (20)
Healthy selected (19)
Healthy selected (10)
Healthy selected (9)
Healthy selected (4)
Healthy selected (2)
Healthy selected (5)
Healthy selected (33)
Healthy selected (32)
Healthy selected (30)
Healthy selected (31)
Healthy selected (27)
Healthy selected (29)
Healthy selected (1)
Healthy selected (34)
LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |