ዜና 

ሃገር አቀፍ የንቦች ቀን ግንቦት 12 በባህር ዳር ከተማ ተከበረ

Honeyexpo (50)በኢትዩጽያ ከ10-12 ሚሊዩን ህብረ ንቦች እንዳሉ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ከዚህ ሀብት ከ500000 ቶን ማር እና ከ50000 ቶን በላይ ሰም ምርት ማምርት እንደሚቻል መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይሁን እንጅ አሁን ላይ እየተመረተ ያለው ከ53000 ቶን በላይ ማርና ከ3800 ቶን ያልበለጠ የሰም ምርት ነው፡፡ ከአለን አቅም አንፃር ሲታይ የሚመረተውምርት ከ10% አይበልጥም ፡፡ ያም ሁኖ በአፍሪካ ከሚመረተው የማር ምርት 27% ከኢትዮጵያ ይሸፍናል፡፡ ከዓለም ደግሞ 2.7% የማር ምርት ድርሻ በማበርከት ከዓለም 10 ደረጃ ትገኛለች፡፡ በሰም ምርትም ከዓለም በ4ኛ ደረጃ በአፍሪካ 1ኛ ደረጃ ትገኛለች ፡፡ ወደ ክልላችን ስንመጣ በአማራ ክልል ከ1.3ሚ ያላነሰ ህብረ ንብ ይገኛል፡፡ ከዚህ ሃብት በዓመት እስከ 4ዐ000 ቶን የማር ምርት 4ዐዐ ቶን የሰም ምርት ማምረት ቢቻልም አሁን እየተመረተ ያለው 25000 ቶን ማር 1800 ቶን ሰም ነው፡፡ ይህም ከሃገር አቀፍ ድርሻው 20% ሲሆን ከአለን እምቅ ሃብት አንፃር ሲታይ አነስተኛ ነው፡፡ የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ይህንን ሃብት በተገቢው መልኩ አልምቶ የማርና የሰም ምርትን በጥራትና በብዛት ለማምረት ንብ አናቢውን በስልጠና፣ ዘመናዊ የማነቢያ ግብዓቶችን በማቅረብና የድጋፍና ክትትል ስራ የመስራት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡ በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘርፉ አበረታች ውጤቶች መመዝገብ ጀምረዋል፡፡

እነዚህን ውጤታማ የሆኑ ስራዎች ወደ ሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ለማስፋት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ለዚህ ስራም እንዲህ ዓይነት ሃገራዊ መድረኮች መዘጋጀታቸው ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ ሃገር አቀፍ የንቦች ቀን ንቦች ለተሻለ የግብርና ምርታማነትና ለምርት ጥራት በሚል መሪ ቃል የሚመለከታቸው የፌደራል፣ የክልልና የዞን ስራ ኃላፊዎች ቡዱን መሪዎች በተገኙበት በባ/ዳር ከተማ በፖናል ውይይትና በኢግዚቢሽን እየተካሂደ ይገኛል ፡፡

በፖናል ውይይቱ ፡- ስለ ሃገራችን ንብ ሃብት ፖቲንሻል ተግዳሮቶች

-    በንብ ሃብት ልማት ላይ እየደረሰ ያለውን የኬሚካል ተጽእኖ

-    አፒ ቴራፒ

-    በንብ ሃብት ልማቱ የኦሮሚያ ክልል ተሞክሮን በተመለከተ በተለያዩ ፁሁፍ አቅራቢ በዘርፉ ሙሁራን ቀርቧል፡፡ በቀረበው ፁሁፍም ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በመጨረሻም መድረኩን የመሩት አቶ ግርማ ሙሉጌታ የግብርና ሚኒስተር የእንስሳት ዘርፍ ሚኒስተር ዲታ አማካሪ ፣ ዶ/ር ጋሻው ሙጨ የአብክመ እንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ ሲሆኑ እንደ ሃገር በዘርፉ ያለንን እምቅ ሃብት ለማልማት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን በተሰሩ ስራዎችም የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችና በዘርፉ ያሉ ዋና ዋና ተግዳሮቶችንና እነዚህን ተግዳሮቶች በቀጣይ እንዲት እንፍታ በሚሉ ጉዳዮች ዝርዝር ማብራሪያ በመስጠት የፖናል ውይይቱ ተጠናቆል፡፡ በኢግዚቪሽን በዓሉ አብዛኛዎቹ ክልሎች የማርና የሰም ምርቶችን ለእይታና ለገበያ ያቀረቡ ሲሆን ኢግዚቪሽኑም የሚመለከታቸው የፌደራልና የክልል አካላት በተገኙበት በአብክመ ግብርና ቢሮ ኃላፊ በዶ/ር ኃይለማርያም ከፍያለው ተከፍቷል፡፡ በመቀጠልም በኢግዚቪሽኑ የቀረቡ የማር ምርቶች በእለቱ እንግዶች የተጐበኘ ሲሆን ኢግዚቪሽኑ እስከ 13/09/2014ዓ/ም የሚቀጥል ይሆናል፡፡

 

Honeyexpo (49)

Honeyexpo (52)

Honeyexpo (53)

Honeyexpo (39)

Honeyexpo (41)

Honeyexpo (42)

Honeyexpo (56)

 Honeyexpo (47)

Honeyexpo (34)

Honeyexpo (36)

Honeyexpo (14)

Honeyexpo (12)

Honeyexpo (19)

Honeyexpo (21)

Honeyexpo (22)

Honeyexpo (25)

Honeyexpo (26)

Honeyexpo (27)

Honeyexpo (33)

Honeyexpo (10)

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |