ዜና  

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት በ28/07/2014 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ፡፡ በንቅናቄ መድረኩ የፊደራል የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ቢሮ ኃላፊዎችና ም/ኃላፊዎች፣ ዩኒቨረስቲዎች፣ የምርምር ተቋማት እና የዞንና ወረዳ የዘርፍ ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

መድረኩን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ኃይለማሪያም ከፍያለው ሲሆን ሀላፊው በመልዕክታቸው ክልሉ ሰፊ የሆነ እንስሳት ሀብት ክምችት ያለው መሆኑን ገልጸው ይህን ሀብት ለማልማት በየደረጃው ያለው የዘርፍ አመራርና ሙያተኞች ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት እንደ ግብርና ቢሮም ይህን ዘርፍ በል ሁኔታ ለመደገፍ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል፡፡

በመቀተል የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌደራል ግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ሚኒስቴር ድኤታ ዶ/ር ፍቅሩ ረገሳ ሲሆኑ ኃላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው ዘርፉ የግብርናው የጀርባ አጥንት፣ ለሀገር ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም ያለው እንዲሁም ለወጣቶችና ሴቶች ስራ ዕድል በመፍጠርም ትልቅ አበርክቶ ያለው ዘርፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው አክለው ዘርፉ የበለጠ ቢሰራበት የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ለሀገር ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ከፍ ማድረግ ይቻላል ብለዋል፡፡ ለዚህም በየደረጃው ያለው የዘርፉ አመራርና ሙያተኛ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የሚሰሩ የዝሪያ ማሻሸል፣ የእንስሳት መኖ ልማትና ስነ አመጋገብን የማሻሻል እንዲሁም የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ላይ በደንብ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ እንደሚገባ አጽዕኖት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡ ለዚህም ሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትም የበኩላቸውን ሀላፊነት መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም ሚኒስቴር ድኤታው የፌደራል ግብርና ሚኒስቴር በክልሉ የሚሰሩ የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ስራዎችን በተሟላ ሁኔታ ለመደገፍ ቁርጠኛ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የክልሉ የዕለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት ክብርት አይናለም ንጉሴ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ እንዲህ አይነት ክልላዊ መድረክ በእንስሳት ሀብት ልምት ዘርፍ መፈጠሩ የሚበረታታ መሆኑ ገልጸዋል፡፡ ኢኮኖሚያችን የተመሰረተው በግብርና ነው፡፡ ግብርናም የተመሰረተው በእንስሳት ነው ሲሉ የዘርፉን ኢኮኖሚያዊ ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑን የሚያሳይ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ሃላፊዋ አክለውም የትግራይ ወራሪ ሀይል በዚህ ዘርፍ ላይ ትልቅ ጉዳት ያደረሱ መሆኑን በመተቆም በየደረጃው ያለውን የዘርፍ አመራርና ሙያተኛ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በቁጭት መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ሃላፊው አክለውም ግብርና ማለት ሰብል፣ ተፈጥሮ ሀብት፣ መስኖ፣ አትክልትና ፍራፍሬ እና እንስሳት ማለት ነው፡፡ የሚነጣጠሉ አይደሉም ከዚህ አንጻር በየደረጃው ያለውን የዘርፍ አመራርና ሙያተኛ ይህን በአግባቡ ተገንዝቦ ለአንድ አርሶ አደር ተጠቃሚነት ተደጋግፎ መስራት ይጠይቃል ብለዋል፡፡ በመቀጠልም የዳቦ ቆረሳ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡

የዕለቱ የመወያያ ጽህፎች በዶ/ር ዘውዱ ውለታው የGIZ ዳይሬክቶሬት እና ዶ/ር ተሾመ ዋለ የአማራ ክልል የATA ዳይሬክቶሬት ቀርበዋል፡፡ በመወያያ ጽህፎች ዘርፉ በአደጉ ሀገራት እንዲሁም በሀገራችን ለኢኮኖሚ እያበረከተ ያለው አስተዋጽኦ በጥናቱ ጎልቶ ተመላክቷል፡፡ አንድ ሀገር የዘርን ልማት ለማልማት የፖሊስና ስትራቴጅ ጉዳዮች ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

በተጨማሪ ካለን የእንስሳት ሀብት አቅም አንጻር የዘርፉን ልማት በተገቢው መልኩ አልምቶ ዘርፉ ለአጠቃላይ ኢኮኖሚ የሚያበረክተውን አስተዋጽኦ ከፍ ሊያደርግ የሚችሉ ጉዳዮችን በመወያየት ጹሁፉን አመልክተዋል፡፡ በመቀጠልም ዶ/ር ተሾመ ዋለ የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮ ጥሬ ሀቆች በንጽጽር በማሳየት እንደ ሀገር ያለንን ሀብት እንዴት መጠቀም እንዳለብን የሚያሳይ ስሜት ኮርኳሪ የሆነ የወይይት ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ የቀረበው መወያያ ጽሁፍ እንደ ክልል ካለው የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ስራዎች ጋር በማዛመድ ሰፊ ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን መድረኩን በመሩት በዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ የግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ሚኒስቴር ድኤታ ፣

በዶ/ር ሀይለማሪያ ከፍያለው የአብክመ ግብርና ቢሮ ሃላፊ እንዲሁም በዶ/ር ጋሻው ሙጨ የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ ማጠቃለያ ተሰጥቷል፡፡ በመጨረሻም ዶ/ር ሀይለማሪያም ከፍያለው የግብርና ቢሮ ሃላፊ የቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጠዋል

  1. ትልቁን አስተሳሰብ መግዛትና በአዲስ ሀይል በተነሳሽነት መስራት
  2. ችግሮችን መለየትና ትልቁን ችግር ቀድሞ ለመፍታት ጥረት ማድረግ
  3. የተለያዩ ችግሮችን በአጭር በመካከለኛና በረዥም ጊዜ ብሎ መለየትና መፍታት
  4. የፕሮጀክቶችን ሀብት በፍትሀዊነት ለመጠቀም ጥረት ማድረግ
  5. መተማመንና መከባበር መሰረት ያደረገ ስራ መስራት
  6. የየአካባቢውን ፓቴንሻሉን በአግባቡ ለይቶ ወደ ስራ መግባት መጠቀም
  7. የመፈጸም አቅማችን ማሳደግ
  8. የድጋፍና ክትትል ስርዓታችንን በአግባቡ መፈተሸ እና ማስተካከያ ማድረግ
  9. ደንቦች፣ መመሪያዎችን እና የአሰራር ማንዋሎችን መፈተሸ እና ለስራ ምቹ ያልሆኑትን ማሻሻል የሚሉ ዋና ዋና ነጥቦች በቀጣይ ሊተኮርባቸው እንደሚገባ ተመላክተው የዕለቱ የንቅናቄ መድረክ በአማረና በደመቀ እንዲሁም ተግባቦት በተሞላበት ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (20)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (22)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (21)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (19)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (16)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (15)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (14)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (13)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (12)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (11)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (10)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (9)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (8)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (7)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (6)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (5)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (4)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (3)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (2)

ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ (1)

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |