ዜና  

የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ጥበቃ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አጋር ተቋማት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

በመድረኩም ከዞን እና ከወረዳ ለተውጣጡ የአካባቢና ማህበረሰብ ጥበቃ ባለሙያዎች፣ የወረዳ እንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪና ባለሙያዎች እንዲሁም የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የሰራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ከጥር 05/2014 ዓም በእንጀባራ ከተማ ተካሄደ፡፡ የመወያያ ጽሁፎች የኘሮጀክቱ የአካባቢና ማህበረሰብ ደህንነት ባለሙያ በሆኑ በአቶ ሀሰን ሙሀባው ሰፋ ያለ የመወያያ ጽሁፎች አቅርበዋል፡፡

የውይይቱም ዓላማ

  • በዋነኝነት ኘሮጀክቱ ሲተገበር የአካባቢና የማህረሰብ ጥበቃ ላይ ሊኖሩ የሚችሉ አሉታዊ ተጽእኖዎችን ለማስቀረት ለመቀነስ እንዲቻል
  • አዎንታዊ ተፅዕኖዎችን ለማሳደግ/ ለማጎልበት የባለሙያዎችን የመፈጸም ሙያዊ አቅም ለማሳደግ ነው፡፡

በተለይ ኘሮጀክቱ የአለም ባንክን የሴፍጋርድ ስታንዳርድና የኢትዮጵያን የአካባቢ ጥበቃ ህግና ፖሊስ መሰረት በማድረግ የፈጻሚወችን አቅም ለማጎልበት እንደሆነ ከውይይቱ ከሚጠበቁ ውጤቶች አንዱ ነው፡፡

በውይይቱም ለማህረሰቡ ሊጠቅሙ የሚመጡ የኘሮጀክት ኘሮግራሞች ሲተገበሩ የአካባቢና ማህበረሰብ ድህንነት አሉታዊና አውንታዊ ተጽእኖ እንዳይኖረው ለባለሙያዎች የእውቀት ሽግግር ለማድረግና በቀጣይም ኘሮጀክቱ ሊኖረው የሚችለውን ተጽእኖ እየተለየ አስፈላጊውን የተጽእኖ ማቅለያ እየተዘጋጀ እንደሚተገበርም አቶ ሀሰን ገልጸዋል፡፡ የአለም ባንክን ስታንዳርድ ባሟላ መልኩ ከወረዳዎች የተጠናከረ የክትትልና ሪፖርት ስርዓት ይዘረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ጠቁመዋል፡፡ በመጨረሻም የአካባቢና የደህንነት ስራ እንደ ዋና የኘሮክቱ አካል ተደርጎ መታየትና በትኩረት መሰራት እንዳለበት ተገልጾ የእለቱ የውይይት ኘሮግራም ተጠናቋል፡፡

invarometal challage LFSDP(14)

invarometal challage LFSDP(9)

invarometal challage LFSDP(2)

invarometal challage LFSDP(1)

invarometal challage LFSDP(21)

invarometal challage LFSDP(5)

invarometal challage LFSDP(4)

invarometal challage LFSDP(3)

invarometal challage LFSDP(7)

invarometal challage LFSDP(10)

invarometal challage LFSDP(12)

invarometal challage LFSDP(13)

invarometal challage LFSDP(15)

invarometal challage LFSDP(16)

invarometal challage LFSDP(20)

invarometal challage LFSDP(22)

invarometal challage LFSDP(23)

 

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |