ዜና  

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ከአጋር ተቋማት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

እንስሳና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በ2012 እና በ2013 በደረጃ አንድ ከ10 እስከ 25 አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን በጋራ ፍላጎት ቡድን በማደራጀት የአመራረት ስረዓትን በማሻሻል ከእጅ ወደ አፍ ሲመረት የነበረዉን ትርፍ ምርት በማምረት ለገበያ ታሳቢ አድርጎ መስራትን ለማለማመድ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ በፕሮጀክቱ አሰራር መሰረት በደረጃ አንድ ድጋፍ የተደረገላቸውን በጋራ የማምረት ልምዳቸውን ለማዳበርና የገበያ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ወደ 31 ህብረት ስራ ማህበራት የማሳደግ ስራ በ2013 ተሰርቷል፡፡ በመሆኑም በ2013 በተሰራው ስራ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት በ2014 ዓ/ም በአዲስ ለማደራጀት የህብረት ስራ ኮሚሽን ተቋምን እና የእንስሳት ጽ/ቤት ተቋም ጋር የምክክር መድረክ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡

በመድረኩም የዞንና የወረዳ አሰተዳዳሪዎች፣የዞንና የወረዳ የህብረት ስራ ሃላፊዎች ባለሙያዎች ፣የወረዳ እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አሰተባባሪና ባለሙያዎች እንዲሁም የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች በተገኙ የመወያያ ጹሁፎች በእንስሳና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሙሉቀን ዘሪሁን እና ከህብረት ስራ ኮሚሽን በቄስ እሸቱ መብራቱ ስፋ ያለ የመወያያ ጹሁፎች እና ያከናወናቸውን ስራዎች አቅርበዋል ፡፡ በውይይቱም በአፈፃፀም ረገድ ክፍተት የሆኑ ችግሮች በተሳታፊዎች ተነስተው ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎባቸው እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ተሰጠው ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (1)

 

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (3)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (14)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (9)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (4)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (2)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (7)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (5)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (6)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (13)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (15)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (12)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (10)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (8)

LFSDP DEBER TABOR 15 04 2014 (11)

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |