ዜና  

አማራ ክልል በተመረጡ አምስት ወረዳዎች የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡

የአማራ ክልል እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የዝርያ ማሻሻል ስራን በክልሉ ተደራሽና ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እንስት ጥጃ ብቻ የሚያስወልድ ሴክሲድ ሴመን የተባለውን አዲስ ቴክኖሎጅ በተመረጡ አምስት ወረዳዎች አስጀመረ፡፡ ሴክሲድ ሴመን ማለት በሠው ሠራሽ ማዳቀል ዘዴ እንስት ጥጃን ከ80-90% ማስገኘት የሚችል አባላዘር ማለት ነው ፡፡ ሴክሲድ ሴመን ከመደበኛ አባላዘር የሚለየው በአስተማማኝ ደረጃ ከ80-90% ማስወለድ መቻሉ ሲሆን መደበኛ አባላዘር ግን 50% እንስት እና 50% ተባዕት ጥጃ ሊያስገኝ የሚችል አባላዘር ሲሆን ሴክሲድ ሴመን በመጠቀም የዝርያ ማሻሻል ሥራን በማፋጠን በርካታ ቁጥር ያላቸውን እንስት ጥጆች ፤ጊደሮችና ላሞች ማስገኘት መቻሉ ነው፡፡ የሴክሲድ ሴመን አጠቃቀምን ውጤታማ ለማድረግ የሚወስኑ ጉዳዮች ውስጥ የእርባታ ወቅት ፤የወሊድ መጠን ፤የድቀላ አገልግሎት ብዛት ፤የአካባቢው ሁኔታ ፤የእርባታ መንጋ ቁጥር ፤የሚመረት የወተት መጠን መረጃ በማየት ይከናወናል፡፡

ሴክስድ ሴመን ከመጠቀማችን በፊት የእንሰሳትን ክለ አቋም፤የውልደት መጠን፤የዕድሜ፤ለእርባታ ብቁ መሆን እና የጤና ሁኔታ በመገምገም መምረጥ ይጠበቃል ፡፡

ሴክሲድ ሴመን በአብዛኛው ሀገራት የሚዘጋጅ ባለመሆኑ ሀገራችን ወደ ሀገርቤት ለማስገባት እስከ 5000ብር ለአንድ ላም የሚውል ወጪ ሲኖረው መደበኛ አባላዘር በሀገር ውስጥና በክልላችን የሚመረት ሲሆን እስከ 80 ብር ወጪ የሚጠይቅ ቢሆንም በመንግስት ድጎማ 7 ብር ለአርቢው እየቀረበ ይገኛል፡፡

ሴክሲድ ሴመን ካለው ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ አንጻር ከፍተኛ የሆነ የአርቢዎች ፍላጎትያሳየ በመሆኑ እንደ ክልል 3957 ዶዝ ፍላጎት ሲኖረው ለዚህም 3957 ላሞችና ጊደሮች ምርጫ የተካሄደ ሲሆን ፡፡ በነጻ የሚሰጥ ለሠርቶ ማሳያነት የሚውል እስከ አሁን 700 ዶዝ ሴክሲድ ሴመን ቀርቦ ለተመረጡ ወረዳዎችና የዳልጋ ከብት ብዜት ማዕከላት ሲሆን ለቻግኒ የዳልጋ ከብት ብዜት ማዕከላት 150 ዶዝ፣ ለ.ዳንግላ ከተማ 120 ዶዝ፣ለ./አቸፈር 100 ዶዝ፣ ለ./ሜጫ 80 ዶዝፋርጣ ወረዳ 170 ዶዝ፣ለ./ታቦር ከተማ 80 ዶዝ በድምሩ 700 ዶዝ የቀረበ ሲሆን፡፡ በሆርሞን ድራት ታግዞ በተገኘ ድራት ላሞችና ጊደሮች የሴክሲድ ሴመን ድቀላ አገልግሎት እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (10)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (7)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (4)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (5)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (1)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (11)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (6)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (2)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (9)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (12)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (13)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (3)

 የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (8)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (14)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (15)

የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡ (16)

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |