ዜና

ቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄደ ፡፡ 

Chageni 24 03 2014 (17)የአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ፣ በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ፣ ከምርምር ተቋማት የመጡ የስራ ሃላፊዎች እና ተመራማሪዎች ፣እንስሳት ሃብት ልማት ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች እና የዘርፉ የዞንና የወረዳ የሚመለከታቸው አመራሮች እና ሙያተኞች በተገኙበት በ24/03/2014 ዓ.ም በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስተዋወቅ እና ማዕከሉ ከዝርያ ማሻሻል እና መኖ ልማትና ስነ አመጋገብ ከማሻሻል አንጻር የሚሰራቸውን ስራዎች ለተሳታፊዎች የማስጎብኝት ፕሮግራም አካሄደ ፡፡

የእለቱን ፕሮግራም በንግግር የከፈቱት ዶ/ር ሃይለማርያም ከፍያለው የአብክመ ግብርና ቢሮ ሃላፊ ሲሆኑ ሃላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ምርታማ የሆነ የእንስሳት ዝርያዎችን በሚፈለገው መጠን ለማባዛት እና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለውን ፋይዳ በመግለጽ ይህ ቴክኒዮሎጅ በአግባቡ ስራ ላይ ውሎ የሚፈለገውን ውጤት እንዲያመጣ ባለሙያዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የበኩላቸውን ሀላፊነት ሊወጡ ይገባል ሲሉ አፅእኖት ሰጥተው አሳስበዋል ፡፡

የእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ዘርፍ ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት ክብርት አይናለም ንጉሴ ማዕከሉ የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን እያባዛ ለአርሶ አደሩ ከማሰራጨት በተጨማሪ የፎገራ ዳልጋ ከብት ዝርያን ከመጠበቅ አንጻር ትልቅ ፋይዳ ያለው በመሆኑ የማዕከሉን አፈጻጸም ሊያሳድጉ የሚችሉ አዳዲስ አሰራሮች እና ቴክኖሎጅዎችን በስፋት ተግባራዊ ማደረግ እንደሚገባ በመጠቆም ለዚህም የክልሉ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጽዋል፡፡

በመጨረሻም የእለቱ ተሳታፊዎች የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ለእንስሳት ሃብት ዝርያ ማሻሻል ያለውን አወንታዊ አስተዋፅኦ ገልጸው ለውጤታማነቱ የበኩላቸውን ፋይዳ እንደሚያደርጉ እና በማዕከሉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አድናቆት እንደፈጠረባቸው በመግለጽ የእለቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል ፡፡

Chageni 24 03 2014 (17)

 

Chageni 24 03 2014 (16)

Chageni 24 03 2014 (20)

Chageni 24 03 2014 (21)

Chageni 24 03 2014 (9)

Chageni 24 03 2014 (18)

Chageni 24 03 2014 (13)

Chageni 24 03 2014 (12)

Chageni 24 03 2014 (5)

Chageni 24 03 2014 (1)

Chageni 24 03 2014 (4)

Chageni 24 03 2014 (8)

Chageni 24 03 2014 (7)

Chageni 24 03 2014 (6)

Chageni 24 03 2014 (10)

Chageni 24 03 2014 (11)

Chageni 24 03 2014 (14)

Chageni 24 03 2014 (15)

Chageni 24 03 2014 (19)

Chageni 24 03 2014 (2)

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |