ዜና

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በእንስሳት ዘርፍ የተሰማሩ የኒዬኖችን በከፍተኛ ደረጃ ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ

LFSDP Level3 (10)የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልላችን በ15 ወረዳዎች በእንስሳት ዘርፍ በ4 እሴት ሰንሰለቶች (ወተት፣ ቀይ ስጋ፣ ዓሳ እና ዶሮ) ላይ ተመሳሳይ ምርት የሚያርቱ አ/አደሮችንና ወጣቶችን በጋራ ፍላጎት ቡድን በማደራጀት 140000 ብር፣ በደረጃ ሁለት በጋራ ፍላጎት ተደራጅተው ትርፍ ምርት በማምረት ላይ የሚገኙትን ወደ ህብረት ስራ ማህበር በማሳደግ 1.3 ሚሊዬን ብር እና በከፍተኛ ደረጃ የማቀነባበር ስራ ላይ ለተሰማሩ ዩኒየኖችና ለተሻሻሉ ማህበራት 8.5 ሚሊዬን ብር በመሰረተ ልማት፣ በቁሳቁስ፣ በግብዓትና ስልጠና ድጋፍ በማድረግ የምርትና ምርታማነት በማሳደግ ድጋፍ እያደረገ ይኛል፡፡

በመሆኑም እስከ አሁን በደረጃ አንድና ደረጃ ሁለት የተሰማሩ 5 ዩኒዬኖችን/ጠንካራ የህብረት ስራ ማህበራትን/ በደረጃ 3 ለእያንዳንዳቸዉ በአይነት 8.5 ሚሊዬን ብር ድጋፍ ለማደረግ እየሰራ ይገኛል፡፡

ስለሆነም በፕሮጅክቱ የአሰራር ሂደት መሰረት ማህበራትን አወዳድሮ ተጠቃሚ ለማድረግ ምርት አምራቾች፣ ገዥዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ15/3/2014 ዓም በእንጅባራ ከተማ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሂዷል፡፡

የመድረኩ ዋና ዓላማ

  • በፕሮጀክቱ ስለሚሰጠው ድጋፍ፣ ሻጭና ገዥ አጋርነት አሰራር ላይ ግንዛቤ መፍጠር
  • የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ለመሆን የብቃት መለኪያ መስፈርቶች እና የማመልከቻ አካሄዶች ዙርያ የታሳቢ ተጠቃሚዎችን ግንዛቤ መጨመር
  • ህጋዊ የግብይት ኮንትራት ውል ለመፍጠር ምርት አቅራቢና ተረካቢን በማገናኘት በግብይት ሂደቶቻቸዉ ባጋጠማቸው ችግሮች ላይ ለመወያየትና መፍትሄ ለማስቀመጥ

በአጠቃላይ ለ5 ዩኒዬኖች እስከ 43 ሚሊዩን ድረስ በመሰረተ ልማት፣ በቁሳቅስ፣በግብዓትና ስልጠና ድጋፍ ለማድረግ የቅድመ ዝግጅት ስራ ለመስራት የተዘጋጀ መድረክ ነው፡፡ በመሆኑም ዩኔኖች ከፕሮጀክቱ የሚደረግላቸዉን ድጋፍ ለማግኘት በቅድመ ዝግጅት መተግበር የሚገባቸዉን ስራዎች እስከ ህዳር 30 ማጠናቀቅ እንዳለበቸዉ መድረኩን የመሩት የእንስሳት እና ዓሳ ሀብት ጽ/ቤት ሀላፊ ዶክተር ጋሻዉ ሙጨ በማጠቃለያ ንግግራቸዉ ያሳሰቡ ሲሆን በመድረኩ የተሳተፉ ድጋፍ የሚደረግላቸዉ ዩኔኖችም በዚህ አግባብ ወደ ስራ ለመግባት ማረጋገጫ በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

LFSDP Level3 (1)

LFSDP Level3 (2)

LFSDP Level3 (3)

LFSDP Level3 (7)

LFSDP Level3 (8)

LFSDP Level3 (5)

LFSDP Level3 (6)

LFSDP Level3 (4)

LFSDP Level3 (9)

LFSDP Level3 (10)

LFSDP Level3 (11)

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |