ዜና
የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የ2013 በጀት ዓመት የዝርያ ማሻሻል አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል እቅድን ገመገመ፡፡
ኤጀንሲው ከ19-21/1/2014 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ ባካሄደው መድረክ የሰሜን ሽዋ፣ ምዕ/ ጐጃም፤ማዕከላዊ ጎንደር እና የኦሮሞ/ብ/አ/ ዞን ተ/ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች ፤ የወረዳ ተ/ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ፤ ቡድን መሪዎች እንዲሁም የእርባታ ባለሙያዎችና የአዳቃይ ቴክኒሻኖች በተገኙበት የ2013 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል አፈፃፀም እና የ2014 ዓ.ም የዝርያ ማሻሻል እቅድ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ቀርበው ሰፊ ወይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በውይይቱም በአፈፃፀም ረገድ ክፍተት የሆኑ ችግሮች በተሳታፊዎች በኩል የቀረቡ ሲሆን በኤጀንሲው የስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በኩል ይህን ሊፈታ የሚችል ማብራሪያዎችና ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ በመስራት እና ለቀጣይ ስራ መነቃቃትን በመፍጠር መድረኩ ተጠናቋል፡፡