ዜና

በፎገራ ወረዳ ዓሣን ከእሩዝ ማሳ ጋር አጣምሮ የመከወን የሰራ እንቅስቃሴ ተጎበኝ

fish wereta Rice (6)የአማራ ክልል የበርካታ ሀይቆች፣ ወንዞች እና ኩሬዎች መገኛ ክልል ነው፡፡ እነዚህ ሀይቆች፣ ወንዞች እና ኩሬዎች ለአሳ ሀብት ልማት ከፍተኛ ጠቀሚታ አላቸው፡፡

ኤጀንሲው ይህን ምቹ ሀብት በመጠቀም የአሳ ሀብት ልማቱን ለማልማት የሚያስችሉ የሰልጠና የግብዓት አቅርቦት እና የድጋፍና ክትትል ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ኤጀንሲው የአሳ እርባታ ስራን ከላይ ከተጠቀሱ የውሃ አካላት በተጨማሪ በአርሶ አደር ደረጃ በተዘጋጀ ኩሬዎችን በሰፋት በማስፋፋት፣ የኬጅ እና ፒን ካልቸር አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችን ለተጠቃሚ በማስተዋወቅ በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡

በተሰሩ ስራዎችም በአሳ ሀብት ልማት ዘርፍ የተሰማራውን የህ/ስብ ክፍል የተጠቃሚ የሚያደርጉ አበረታች ውጤቶች መታየት ጀምርዋል፡፡ ኤጀንሲው በቅርብ ጊዜም አሳን ከእሩዝ ጋር አቀናጅቶ የማርባታ አዳዲስ አሰራር በፎገራ ወረዳ በተመረጡ 2 ቀበሌዎች ተግባራዊ አድርጓል፡፡

 

በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ የአርሶ አደሮችም እንደገለፁት ይህ ጥምር ግብርና ተግባራዊ መደረጉ በአንድ ጊዜ ሁለት ምርት እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ የአሳው አይነ ምድር ለእሩዙ እድገት ከፍተኛ አሰተዋፅኦ እንዳለው በተደረገው የመስክ ምልከታ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ በመስክ ምልከታው የተገኙ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ የስራ ሀላፊዎች እና ባለሙያዎችም አሳን ከ እሩዝ ማሳ ጋር አቀናጅቶ የማርባት ዘዴ በተጨባጭ ከፍተኛ የሆነ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን በመስክ ምልከታው እና በውይይቱ ላይ በስፋት በማንሳት ይህ ተግባር በቀጣይ በስፋት መስራት እንዳለበት እና ለዚህም የግብርና እና የእንስሳት ሃብት ባለሙያዎች ተቀናጅተው እና ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው አፅእኖት ሰጥተው በማሳሰብ የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡

fish wereta Rice (7)

fish wereta Rice (6)

fish wereta Rice (5)

fish wereta Rice (4)

fish wereta Rice (2)

fish wereta Rice (1)

fish wereta Rice (9)

fish wereta Rice (13)

fish wereta Rice (11)fish wereta Rice (14)

fish wereta Rice (16)

fish wereta Rice (12)

fish wereta Rice (10)

fish wereta Rice (15)

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |