ዜና

 

በሰሜን ጎንደር ዞን አዲ-አርቃ ወረዳ በሳንቅ ብስኒት ቀበሌ ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ (ፒፒአር) የክትባት አገልግሎት ሲሰጥ

ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ (ፒፒአር)

ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ (ፒፒአር) አደገኛ የበጎችና ፍየሎች በሽታ በመባል ይታወቃል፡፡ በጣም አደገኛና በፍጥነት ተዛማችነት ያለው በዋነኝነት ትናንሽ አመንዣኪ የቤትና የዱር እንስሳትን የሚጠቃ ሞርቢሊ ቫይረስ (Morbillivirus) ዝርያ ካለው ከፓራሚኦክሶቫይሪዴይ (Paramixoviridae) አካል የሚመደብ በሽታ ነው፡፡በሽታው በአዲስ መልክ በመንጋ ውስጥ መግባት ከቻለ የመንጋውን ከ50-90% ሊያጠቃ የሚችል ሲሆን በአብዛኛው እስከ 70% እና አንዳንድጊዜ ከዛም በላይ የመግደል አቅም ያለው አደገኛ በሽታ ነው፡፡

ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ (ፒፒአር) ሰውን አያጠቃም  ነገር ግን በከፍተኛ ሁኔታ የግለሰብንም ሆነ የሃገር ኢኮኖሚ የሚጎዳ በሽታ ነው፡፡

  • የበሽታው ስር

ፒፒአር መጀመሪያ በአፍሪካ አይቮሪኮስት በ1945 እአአ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ በጥናት እንደተረጋገጠው በሰፊው አህጉራችን አፍሪካ ሃገራችንን ኢትዮጲያን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅና በእሲያ ሀገራት ተሰራቶ ይገኛል፡፡

በሽታው የሚከሰትበት ወቅት

በሽታው በሁሉም ወቅት የሚከሰት ሲሆን ነገርግን ብዙውን ጊዜ የበሽታ ፍንዳታ የሚከሰተው በዝናባማ እና ደረቃማ ወቅቶች ላይ ነው፡፡

ለበሽታው ተጋላ የሆኑ እንስሳት

      ከቤት እንስሳት፡በግና ፍየሎች፡ እንዲሁም የሜዳ ፍየል ፊቆ ሚዳቋ፣ አጋዘንና ዋሊያ ወዘተ… ተመሳሳይነት ያላቸው ከዱር አራዊትን ጨምሮ ያካትታል፡፡

       የቀንድ ከብቶችና አሳማ የሚያጠቃ ሲሆን፤ ነገር ግን ምንም አይነት የበሽታ ምልክትም ሆነ በሽታውን አያሳዩም፤ አያስተላልፉምም፡፡

የመተላለፊያመንገድ

ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ የመተላለፊያመንገድ በዋነኝነት

        ታማሚ በግ ወይም ፍየል ከጤነኛው እንስሳ ቀጥታ በሆነ ንክኪና ግንኙነት አማካኝነት ነው

የበሽታው ምንጭ

ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ ከተጠቃ እንስሳ ላይ በሚወጣ

      እንባ

      የአፍንጫ ፈሳሽ

      ከሰውነት በሚመነጭ በሚወገድና በማሳል በሚወጣ ቫረሱን በያዘ ፈሳሽ አማካኝነት ከበሽተኛው ወደ ጤነኛው እንስሳት ይተላለፋል፡፡

ኢኮኖሚያዊ ጉዳት

      የመንጋውን ውሰጥ በሽታው ከተከሰተ ከ50-90% ያህል የማሳመም አቅም አለው በዚህም ምክንያት እንስሳውን ለማዳን የሚወጣ የህክምና ወጪ መድሀኒትን ጨምሮ ወዘተ… አርቢውን ማህበረሰብ ከፍተኛ ለሆነ የገንዘብ ወጪ ይዳርገዋል

      ከ 70%  በላይ ታማሚ እንስሳትን ይገድላል በዚህም አርቢውን ማህበረሰብ ከእንስሳውና ከተዋጽኦው ሊያገን ሚችለውን ጥቅም  በማሳጣትና ለድህነት ከመዳረጉ በተጨማሪ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል፡፡


 

የሚታዩ ምልክቶች

እንስሳው በህይወት እያለ የሚታዩ ምልክቶች

      ከአፍንጫና ዓይን የሚወጣ መግል መሳይ ወፍራም ፈሳሽ

      የአፍ ዓይንና አፍንጫ አካባቢ በቅርፊት የተሸፈነ ቁስል

      መጥፎ ጠረን ያለው ተቅማጥ

እንስሳው ከሞተ በኋላ የሚታዩ ምልክቶች

      ሳንባው በደም የተሞላ ይሆናል

      ትልቁ አንጀት የዜብራ መስመር (ቀይ ሸንተራራማ ምስል) መታየት

     

ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ ከተጠቃ እንስሳ የሚያሳይ ምስል በከፊል

ከሌሎች ተመሳሳይ ምልክት የሚያሳዩ በሽዎች መለየት የሚገባቸው

ü  የደስታ በሽታ (Rinderpest)

ü  ተዛማች የፍየሎች የሳምባ በሽታ (CCPP)

ü  ፓስቶሮሎሲሰ(Pasteurellosis)

ü  ኦፈማዝ  (Contagious ecthyma)

ü  አፍተግር (Foot and mouth disease)

ü  የደምተቅማጥ በሽታ(Coccidiosis)

ü  ብሉታንግ (Bluetongue)

የመከላከልና የመቆጣጠሪያ መንገድ

ይህንን በሽታ የሚያድን መድሀኒት የለም ነገርግን በሌላ ሁለተኛ ተጨማሪ በሽታ እንዳይጋለጥ ለመከላከል ፀረ-ተዋሀሲያን (Antibiotics) መጠቀም ተገቢ ነው፡፡

      በግና ፍየሎች በሽታው እንዳይዛቸው መከላከል የሚያስችል ክትባት በነፃ የሚሰጥ በመሆኑ አርቢው ባለቤት የክትባት አቅርቦት ባለበት ቦታ/ የእንስሳት ጤና ተቋም/ በመሄድ በግና ፍየሎቻቸውን እንዲከተቡ ማድረግ ዋነኛ ተግባራቸው ማድረግ ይጠበቅባቿል፡፡

      አዲስ የተገዙ እንስሳትንም ሆነ ለሽያጭ ወደ ገበያ የወጡና ሳይሸጡ ቀርተው የተመለሱ በግና ፍየሎችን ቢያንስ ለ21 ቀናት ለብቻቸው እንዲቆዩ ማድረግ፡፡

      እንስሳትን ዝውውር ከአንድቦታ ወደ ሌላ መቆጣጠር (በጣም አስቸጋሪ ቢሆንም)

      ንቁ የሆነ የበሽታ ምልክቶች ቅኝት ክትትል ማካሄድ

መመርመሪያ ዘዴዎች

በበሽታው ከሚጠረጠር በግና ፍየል ላይ የተለያዩ ናሙናዎችን በመውሰድ

      የደም ቅራሪ ምርመራ ( Serology) ELISA

      በመስክ ላይ ከእንባው ከአፍ ና አፍንጫው ፈሳሽ ላይ ናሙና በመውሰድ ፈጣን በሆነ መመርመሪያ (ኪት) penside test kit በመመርመር ወዲያውኑ በሽታውመኖሩንበማረጋገጥአስፈላጊው ቄጥጥር ክትባት (Vaccination) እንዲከተብ ይደረጋል፡፡

ዋቢ ተጠቃሽ (REFERENCES AND OTHER INFORMATION)

 Classified as an OIE List A disease (A050)                                                                                    

World Animal Health and the OIE Bulletin.

                                                                            International Animall coad(CDC)


 

መግቢያ፡-

በባ/ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርመራ ላቦራቶር ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ፕሮግራም ማስተባበሪያ ቅ/ጽ/ቤት በብሄራዊ ደረጃ የተቋቋመውን መቆጣጠሪያና መከላከያ ፕሮግራም ለመፈጸምና ለመተግበር የምዕራብ አማራ የስራ ክልል በ8 ዞኖች በ91 ወረዳዎችና በ2 ሜትሮፖሊታን ከተሞች ለማስተባበር በመጋቢት ወር 2011 ዓ/ም በባ/ዳር እ/ጤ/ቅ/ምርመራ ላቦራቶሪ ስር ተመሰረተ፡፡

በወቅቱ በኮቪድ19 ምክንያት ወደ ሙሉ የሥራ ትግበራ ባንገባም ከመስከረም ወር 2013 ዓ/ም ጀምሮ ግን የፒፒአር በሽታ የቁጥጥርና አሰሳ ስራዎች ከማህበረሰቡ ጋር በጋራ በመስራት እንደሁም አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ የበሽታ ልየታ በማከናወን  በሽታው ከተገኘ አስፈላው የመከላከያ ክትባት እንዲሰጥ በማድረግ በሽታውን የመቆጣጠርና የመከላከል ስራ እየተሰረ ይገኛል፡፡ ለዚህም ያግዝ ዘንድ የወረዳና የጣቢያ የእንስሳት ባለሙያዎችን ስልጠና በመስጠትና በማስተባበር ለአርቢው ሕብረተሰብ  ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ  እንዲያስገኝለት ከፍተኛ ድጋፍ እንዲሰጡ እየተደረገ ይገኛል፡፡

የተከናወኑ ተግባራት መግለጫ

1. የበሽታ ፍንዳታ ክትትልና የክትባት ትግበራ

በማዕ/ ጎንደር ዞን  በጎንደር ዙሪያ ወረዳ፣ በሰ/ጎንደር ዞን በአዲአርቃይ ወረዳ፣ በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰ/አቸፈር፣ ደቡብ አቸፈር፣ወንበርማና ባ/ዳር ዙሪያ ወረዳዎች፣ በአዊ ዞን ጃዊና  አየሁ ጓጉሳ ወረዳዎች፣ በምዕ/ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ እንዲሁም በደቡብ ጎንደር ዞን በላይ ጋይንት ወረዳ የፒፒአር በሽታ ፍንዳታ ጥሪን በማስተናገድና ምርመራ በማድረግ በምርመራው መሰረት የፒፒአር (PPR) በሽታ መኖሩን በመረጋገጡ የመከላከልና ማጥፋት እርምጃ እንዲወሰድ ተደርጓል፡፡

ምርመራውን መሰረት በማድረግ የጋራ ገበያ፣የእንስሳት ግጦጭሽና መጠጥ ውሃን በማገናዘብ በሰሜንና ደቡብ/አቸፈር ፣ባ/ዳር ዙሪያ፣መተማ፣ ጃዊ፣አየሁጉጉሳ በተመረጡ ቀበሌዎች 383,732በግና ፍየሎች ክትባት እንዲሰጥ ተደርጓል በዚህም 11,903አባወራዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ይህ ቁጥር አሁን በመሰራት ያሉ ወረዳዎችን ማለትም በላይ ጋይንት፣ አዲአርቃይና ወንበርማ ወረዳዎችን የክትባት ቁጥር አያካትትም፡፡

Zone

Name of Wereda

  Date of Vaccination

No of S.R Vaccinate

Noof Beneficiary

NO of experts

 trained

Before vaccination

W/Gojjam

B/Dar Zuriya

17/07/2020  01/08/2020.

14,066

816

 8

W/Gojjam

N/Achefer

28/7/-13/8/20

33,754

 2,831

20

W/Gojjam

S/Achefer

4-20/8/2020

48,340

2,546

16

W/Gondar

Metema

25/10/202-17/11/2020

230,155

3,265

33

Awi

Jawi

0819-/11/2020

42,121

1,162

21

Ayehuguagusa

04/03/2021-30/03/2020

15,300

1273

24

       Total

     6

 

383,732

11,903

122

የክትባት ትግበራ (Vaccination Performance)


2. የማህበረሰብ ተሳትፎ የፒፒአር በሽታ ቅኝት፡- 

በግና ፍየል አርቢ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎችን ማለትም ወጣቶች፣ ሴቶች እንደሁም ጎልማሳና አረጋውያንን  ያካተተ ስለ ፒፒአር  በሽታና ተያያዠ ስለሆኑ የበግና ፍየል እውቀት ያላቸውን   የህብረተሰብ ክፍሎች ባሳተፈ የተለያዩ የበሽታ ቅኝት ዘዴዎችን (Epidemiological tools)    ከማህበረሰብ አገር በቀል እውቀት (conventional knowledge) ጋር በማቀናጀት  የፒፒአር በሽታ አሰሳና ቅኝት ስራ ተሰርቷል፡፡ በዚህም በ 5 ዞኖች በ10 ወረዳዎች ላይ ፍተሻ ተደርጓል፡፡ ይህ ተግባር በእቅድና በተግባር ዓመቱን በሙሉ የሚሰራ ስራ ነው፡፡ የፒፒአር በሽታ አሰሳና ቅኝት ላይ በበሽታው የሚጠረጠር እንስሳ ምርመራ ይደረግለታል በሽታው በምርመራ ከተረጋገጠ በቁጥር 1 ላይ የተጠቀሰው ተግባር ተፈጻሚ ይሆናል፡፡     

Zone

Name of Wereda

Participatory Disease  Surveillance

Out Com /Result

C/Gondar

W/Belesa

PDS

-Ve/negative

Alefa

  //

-Ve

E/Gojjam

Enebsie

Dejen

PDS

PDS

-Ve

-Ve

 W/Gojjam

Burie

N/Mecha

Quarit

 PDS

PDS

PDS

-Ve

-Ve

-Ve

Awi

Dangela

PDS

-Ve

S/Gondar

Libokemkem

Dera

PDS

PDS

-Ve

-Ve

5

10

 

10-Ve

  

ከማህበረሰብ ጋር የሚሰራ የአካባቢው ካርታ                 ከማህበረሰብ ጋር ስለ በሽታው ውይይት 

                                                     PDS team discussing with community,

(Participatory Mapping)

ከማህበረሰብ ጋር የተለያዩ የበሽታ ጥናት ዘዴዎችን (Epidemiological tools) በመጠቀም በሽታዎችን በማወዳደር ደረጃ በማውጣት እንደየቅደም ተከተሉና ጉዳት መጠኑ ምዘና ሲካሄድ

3. ስልጠና መስጠት

ማስተባበሪያ ቅ/ጽ/ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ከ7ቱም ዞኖች ለተወጣቱ በየደረጃው ላሉ የእንስሳት ጤና ባለሙዎች 4 ስልጠናዎች  ተሰጥተዋል፡፡ በዚህም መሰረት 161 ባለሙያዎች በስልጠናው ተሳትፈዋል፡፡ በተጨማሪም ቅድመ ክትባት ለማስተግበር 155 ለወረዳና ለቀበሌ የእንስሳት ጤናና እርባታ ባለሙያዎች፣ ለቀበሌ ገበሬ ማኅ/ሊቀመናብርት ስለ ፕሮግራሙ እስትራቴጂ፣ ስለክትባት አሰጣጥ፣ አጠቃቀም፣ ስለክትባት ቅዝቃዜ ሰንሰለት አጠባበቅና ተጠቃሚው ኅብረተሰቡን እንዴት መቀስቀስ እንዳለበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

ለባለሙያዎች የማህበረሰብ ተሳትፎ የፒፒአር በሽታ ቅኝት (PDS)ና የበሽታ ሪፖርት አደራረግ DOVAR, ADNIS ስልጠና ተሰጥቷል፡፡  

Zone

Type of training

Number  of trainees

In a total of 7 zones & 2 city administraion

PDS

93

Dovar

35

ADNIS

33

                                 Total

161

ቅድመ ክትባት ለማስተግበር የግንዛቤ ማስጨበጫ ባለሙያዎችና ለቀበሌ ገበሬ ማኅ/ሊቀመናብርት  የተሰጠ ስልጠና 

ዞን

ወረዳ

የሰልጣኝ ብዛት

ሰ/ጎንደር

አዲርቃይ

51

አዊ

አየሁጓጉሳ

24

ደ/ጎንደር

ላይ ጋይንት

55

መዕ/ጊጃም

ወንበርማ

25

                   ድምር

155

  

4. ይህን ስራ ውጤታማ ለማድረግ ከባለድርሻ አካል የሚጠበቅ

4.1. ከክልሉ እንስሳት ኤጀንሲ

ü  ለክትባት አገልግሎት የሚውሉ የህክምና ቁሳቁስ በተሟላ ሁኔታ እንዲቀርብ ማድረግና ማሟላት ማለትም  ፍሪጅ፣የክትባት ሲሪንጅና መርፌ፣የክትባትና የበረዶ መያዣ ወዘተ…

ü  የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ሙያዊ ስነምግባርን በተላበሰ ለአርቢው ህብረተሰብ በቅንነትና በታማኝነት ግልጋሎት እንዲሰጡ ክትትል፣ ቁጥጥርና ድጋፍ ማድረግ፤

ü  ከፍዴራል ማስተባበሪያ ጋር ግንኙነትን በማጠናከር አስፈላጊው ሁሉ እንዲሟላ ማድረግ፡፡

4.2. የባ ዳር እ/ጤ ላቦራቶር

ü  አስፈላጊውን መኪና፣ ክትባት ፣ ሳላይን ፣ አስተባባሪ ማቅረብ አለበት፡፡

4.3.የዞንና ወረዳ እ/ተጠሪ ጽ/ቤቶች

ü  ለስራው አስፈላጊ ባለሙያዎችን ዝግጁ ማድረግ፣

ü  በግና ፍየል  አርቢውን ህብረተሰብ ስለበሽታው አስከፊነት ግንዛቤ መፍጠር፣

ü  በግና ፍየል  አርቢውን ህብረተሰብ ለበሽታው ቁጥጥርና ማጥፋት ተባባሪ እንዲሆኑ ቅስቀሳ ማድረግ፣

ü  ክትባት በሚሰጥባቸው ቦታዎች ላይ ፕሮግራምና ስምሪት መስጠትና ማውጣት፡፡

4.4.በግና ፍየል አርቢው ህብረተሰብ፡-

ü  በግና ፍየል አርቢውን ህብረተሰብ የፕሮግራሙን ተፈጻሚነት ከግብ ለማድረስና ይህን በሽታ ከክልላችን ብሎም ከሃገራችን ለማጥፋት የባለሙያዎችን ምክር በመስማት በግና ፍየሉን ለክትባት በአካባቢው በሚገኝ መክተቢያ ጣቢያ ወይም ወደ እ/ጤ ክሊኒክ በመውሰድ ተባባሪነቱን ማሳየት አለበት፡፡

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |