ዜና

የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት በ 20/06/2013 ዓም በእንጅባራ ከተማ የ6 ወሩን የኘሮጀክት አፈፃፀም በቴክኒክ ኮሚቴው ገመገመ፡፡

የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት በ 20/06/2013 ዓም በእንጅባራ ከተማ የ6 ወሩን የኘሮጀክት አፈፃፀም በቴክኒክ ኮሚቴው ገመገመ፡፡ የኘሮክቱ የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም በኘሮጀክቱ በኩል ከቀረበ በኃላ ከቤቱ በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ በስፋት ተወያያቶ የሚከተሉትን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡

 

      ነባር የጋራ ፍላጐት ቡድናትን ያለበትን ሁኔታ ለይቶ የማወቅና የማጠናከር ስራ ይሰራ ለዚህም መስፈርት የተዘጋጀ በደረጃ ለይቶ የተሻለ አፈፃፀም ባላቸው የጋራ ፍላጎት ቡድኖች ሌሎች እንዲማሩ ፊልድ

      የህብረት ስራ ማደራጃ ኤጀንሲ በየወረዳው ያሉ የህብረት ስራ ማህበራትን የማጠናከር ስራ መሰራት አለበት

      በ 15 ወረዳ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች የተመሠረቱ ተዋፅኦችን በኘሮጀክቱ የገቢያ እሴት ሰንሰለት እና በንግድ ቢሮ በኩል ስራዎች ተሰርተው የመፍትሄ አቅጣጫዎች ይቀመጡ፡፡

      ከመሬት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን መሬት አስተዳደር ወስኖ መፍታት አለበት፡፡ ለዚህም በቢሮዉ የተወከሉ አካላት በቅርበት መከታተል አለባቸው፡፡

      ቴክኒክና ሙያ ነባሮችም ሆነ አዲሶችን የጋራ ፍላጎት ቡድኖች በአመለካከት የማብቃት ስራ መስራት አለበት

      ግዥን በተመለከተ በየእለቱ እያንዳንዱ ወረዳ ያለበትን ሁኔታ መረጃ እየተያዘ ለፌስ ብክ ይሰጣል

      በክልል ደረጃ የመድሃኒት ግዥ በትኩረት ተይዞ ይሰራል አፈፃፀሙም በየጊዜወ ሪፖርት ይቀርባል

      መኖ ሳይገባ ዶሮ እንዳይገባ ጥንቃቄ ይደረግ

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |