ዜና

የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ የአሰልጣኞች ስልጠና ሲያካሄድ፡፡

የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ  

1 በገቨርናንስና ንዑስ ፕሮጀክት አዘገጃጀት

2 በአካባቢ እና ማህበራዊ ደህንነት ጉዳይ

3 በግብይት ሰንሰለት ዙሪያ ከጥር 17-21/2013 በእንጅባራ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና አካሄደ፡፡

በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ባለሙያዎች እንደገለጹት እንዲህ አይነት ስልጠና ከዚህ በፊት አለማግኘታቸውን ጠቅሰው ስልጠናው ለቀጣይ ስራቸው ትልቅ አቅም እንደሚሆናቸው በመጠቆም  ወደ የመጡበት ወረዳ ሲመለሱ ስልጠናውን ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚያወርዱ ገልጸዋል ፡፡ መድረኩን የመሩት የኤጀንሲው ም/ስራ አስኪያጆች እና የፌደራል የፕሮጀክቱ አስተባባሪ በኩላቸው ፕሮጀክቱ የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፉን ለማዘመን በሚሰሩ ስራዎች ትልቅ ድርሻ ያለው መሆኑን ገልጸው በየደረጃው ያሉ የዘርፉ ሙያተኞች እና የሚመለከታቸው አጋር አካላት የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ በማሳሰብ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |