ዜና

በክልሉ ከሚገኙ በርካታ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዞች አላውሃ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዝ አንዱ ነው፡፡

የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚሰራቸው በርካታ ስራዎች ውስጥ ወጣቶች በዘርፉ በስፋት ተደራጀተው እንዲገቡ እና የተሻለ አሰራር ተከትለው እንዲሰሩ ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡ በክልሉ ከሚገኙ በርካታ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዞች አላውሃ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዝ አንዱ ነው፡፡ኢንተርኘራይዙ የሚገኝው በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ላስታ ገራዶ 04 ቀበሌ ሲሆን ስራ የጀመረው በ2007 ዓም በ 5 ላሞች ነው፡፡

ኢንተርኘራይዙ አሁን ላይ 17 ላሞችና 7 ጊደሮች፣ 10 ጥጆች እና 1 ኮርማ ያለው ሲሆን አሁን ከሚታለቡ ላሞች ውስጥ በቀን እስከ 70 ሊትር ወተት ለገቢያ እንደሚያቀርቡ ጠቁመዋል፡፡ የኢንተርኘራይዙ አባል አቶ ያሴን ሸጋው እንደገለፁልን አባላቱ በአብዛኛው ከአረብ አገር ተመላሽ መሆናቸውን ገለፀው በዚህ የስራ መስክ መሰማራታቸው ከራሳቸው አልፎ ከ 4 ያላነሱ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠራቸውን ገልፀዋል፡፡ ግለሰቡ አክለውም አሁን የስራው እንቅፋት የሆነባቸው የውሃ እጥረት ቢፈታ በቀጣይ የተሻለ ስራ ሰርተው ራሳቸውን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ እኛም የሚመለከታችሁ አካላት ተገቢውን ድጋፍ ብታደርጉላቸው የሚል መልክታችን እናሳተላልፋለን፡፡

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |