ዜና

በሰሜን ውሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ሀራ 01 ቀበሌ ከአረብ ሃገር ተመልሰው በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተደራጁት ኢብራሂም ሁሴን እና ጓደኖቹ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊ ኢንተርኘራይ በ2009 ዓም 1000 ጫጩቶችን በመያዝ ስራ የጀመሩ ሲሆን አሁን ላይ በዓመት ከ20,000 ያላነሱ ጫጩቶችን በማሳደግ ለተጠቃሚዎች ያቀርባሉ፡፡

የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ህ/ሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከስራቸው ስራዎች አንዱ የተሻለ የእንቁላል እና የስጋ መጠን የሚሰጡ የዶሮ ዝርያዎችን በግብዓት አቅራቢዎች አማካኝነት ለህብረተሰብ እንዲዳረስ እና ሳይንሳዊ አሰራሩን ተከተለው እንዲሰሩ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ነው፡፡ ኢብራሂም ሁሴን እና ጓደኖቹ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊ ኢንተርኘራይዝ የሚገኝው በሰሜን ውሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ሀራ 01 ቀበሌ ሲሆን ኢንተርኘራይዙ በ2009 ዓም 1000 ጫጩቶችን በማሳደግ ስራ የጀመረ ሲሆን

አሁን ላይ በአመት ከ 20.000 ያላነሱ ጫጩቶችን በማሳደግ ለተጠቃሚዎች ያቀርባል፡፡ የኢንተርኘራይዙ አባል አቶ ኢብራሂም ሁሴን እንደገለፁልን ከዚህ በፊት በአረብ አገር ይኖሩ እንደነበር ገልፀውልናል፡፡ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ በኃላ በባለሙያዎች በተደረገላቸው ድጋፍ በዚህ ዘርፍ በመሰማራት ራሳቸውን ከመጥቀም ባለፈ ለ 3 ሰው የሰራ ዕድል መፍጠራቸውን ጠቁመውናል፡፡ ግለሰቡ አክለውም ይህ ዘርፍ እጅግ አዋጭ መሆኑን ጠቅሰው በርካታ ስራ አጥ ወጣቶች በዚህ ዘርፍ ቢሰማሩ ከራሳቸው ባለፈ አገርን ተጠቃሚ ያደርገሉ ብለዋል፡፡ እኛም በስፍራው ተገኝተን ያየነው ስራ የሚበረታታ በመሆኑ ይህን ተሞክሮ ሌሎች ወስደው ተግባራዊ ቢያደርጉት ተጠቃሚ ይሆናሉ እንላለን፡፡

 

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |