ዜና

በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ከአረብ ሃገር ተመልሳ በወተት ሃብት ልማት ስራ የተሰማራችው ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን በ2010 ዓ.ም 4 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ ወደ ስራ የገባች ሲሆን አሁን ላይ በቀን ከ650 ብር ያላነሰ ከወተት ሽያጭ ታገኛለች፡፡

የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ በውስን ካፓታል እና መሬት ለወጣቶችና ለሴቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር ትልቅ አቅም ያለው ዘርፍ ነው፡፡ በዘርፉ በርካታ ወጣቶች እና ሴቶች ወደ ስራ በመግባት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ወጣቶችና ሴቶች መካከለ ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን አንዳ ናት፡፡ ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን ነዋሪነቷ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ሲሆን ግለሰቧ የወተት ሀብት ልማት ስራ የጀመረችው በ2010 ዓም ነው፡፡ አሁን ላይ 4 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ እና ባላት ውስን ቦታ የተሻሻሉ የመኖ ልማቶችን በማልማትና

እንስሳቶችን በመመገብ ተጠቃሚ መሆን ችላለች፡፡ ግለሰቧ እንደገለፀችው በቀን ከ650 ብር ያላነሰ ከወተት ሽያጭ እንደምታገኝ ገልፃ ከዚህ በላይ የተሻሻለ ስራ ለመስራት የቦታ ጥበት እና የብድር አቅርቦት ችግር እንዳለባት ጠቁማናለች፡፡ እኛም የሚመለከታቸው አካላት የግለሰቧን ችግር ተረድታችሁ የተሻለ ስራ እንድትሰራ አግዟት የሚለው መልክታችን ነው፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |