ዜና

በአዊ ብ/አ/ዞን በእንጅባራ ከተማ በወተት ሃብት ልማት ሰራ የተሰማሩት አለም የወተት ላም እርባታ 18 ላሞች፣ ጊደሮች እና ጥጆች በመያዝ በዘርፉ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛል፡፡

በአማራ ክልል ከሚገኝ በርካታ የወተት ላም እርባታ ድርጅቶች አንዱ አለም የወተት ላም እርባታ ነው፡፡ የወተት ላም እርባታው የሚገኝው በአዊ ብ/አ/ዞን በእንጅባራ ከተማ ነው፡፡ የወተት ላም እርባታው በ 2003 ዓ.ም እንደጀመረ የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ የሽወርቅ ምህረት ገልፀውልናል፡፡የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ የሽወርቅ ምህረት አሁን ላይ በእርባታ ድርጅቱ ቁጥራቸው ከ 18 ያላነሱ ላሞች፣ ጊደሮች እና ጥጆች እንደሚገኙ ጠቁመው በቀን ከ 80 ሊትር ያላነሰ ወተት እንደሚያገኙና በዚህም ሂውታቸውን በተሻለ መልኩ እየመሩ እንደሆነ ገልፃዋል፡፡

ግለሰቧ አክለውም ከቦታ ጋር ተያይዞ ያሉባቸው ችግሮች በመንግስት በኩል ቢፈቱ ከዚህ የተሻለ ስራ በመስራት ራሳቸውን እና ህብረተሰቡን መጥቀም እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡ እኛም ከቦታው ተገኝተን ያየነው ስራ የሚያበረታታ በመሆኑ የአካባቢው አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ  እንዲደረግላቸው መልክታቸውን እናስተላልፋለን፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |