ዜና

በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተሰማሩ ወጣቶች የስራ እንቅስቃሲ

የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ሰንቶ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የተሻለ የእንቁላል ምርትና ስጋ መስጠት የሚችሉ የውጭ ደም ያላቸው የዶሮ ዝርያዎች ከ 1 ቀን ጫጩት አቅራቢ ካምፓኒዎች አሳዳጊዎች እየወሰዱ እንሚያሳደጉ አስፈላጊ ሙያዊ እገዛዎችን በቅድመ ዝግጅትና በተግባር ምዕራፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ ኤጀንሲው በ2012 በጀት አመት በ 1 ቀን ጫጩት ማሳደግ ስራ በሰራ ላይ ሆነው ድጋፍ የተደረገላቸው በኢንተርኘራይዝ የተደራጅ አሳዳጊዎች ቁጥር 2250 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 754 ሴቶች ናቸው፡፡

ወጣት ብስራት እንዳላማው እና መዝገቡ የተባሉ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊዎች ነዋሪነታቸው በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ ሲሆኑ ወደ ስራ የገቡት በ 2012 ዓም እና በ2010 ዓ.ም 500 እና 300 ጫጩቶችን በመያዝ ነው፡፡ አሳዳጊዎቹ አሁን ላይ በቅደም ተከተል 1500 እና 3000 ጫጩቶችን ይዘው በማሳደግ ላይ ያሉ ሲሆን የስራውን አዋጭነት በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ከዚያ በፊት ምንም አይነት ስራ እንዳልነበራቸው እና ወደዚህ ስራ ከገቡ ጊዜ ጀምሮ የተሻለ ተጠቃሚ መሆናቸውን እና ወደ ፊትም ስራውን ይበልጥ ለማስፋፋት እቅድ እንዳላቸው ገልፀውልናል፡፡ የእነዚህን ወጣቶች አርአያነት በመውድ ሌሎች ወደ ስራ ያልገቡ ወጣቶች በዚህ ዘርፍ ወደ ስራ ቢገቡ ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እንጠቁማለን፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |