ዜና

በእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ኘሮጀክት በዓሣ ሃብት ልማት የተደራጁ ወጣቶች ና በአርሶ አደሮች የዓሳ ኩሪ ጫጩት የመጨመር ስራ ተሰራ

የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በክልሉ የዓሣ ሃብት ልማትን ለማሣደግ እና ህብረተሰቡን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ከባ/ዳር የዓሣ ምርምር ማዕከል የዓሣ ጫጩት በማራባት በእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ኘሮጀክት በዓሣ ሃብት ልማት የተደራጁ ወጣቶች ና በአርሶ አደሮች የዓሳ ኩሪ ጫጩት የመጨመር ስራ ተሰራ

 

 

 

ክልላዊ የዓሣ ሃብት ልማት መረጃ

 

ክልሉ ለዓሳ ሃብት ልማት አመች የሆነ የአየር ንብረት ያለዉ ሲሆን በዓመት ከ30 ሽህ እሰከ 40 ሽህ ቶን የዓሳ ምርት ለሚረት እንደሚችል መርጃዎች ያሳያሉ ፡፡ በዚህም መሰረት በGTP-1 2007 ዓ/ም መጨረሻ ከነበረበት 18,400 ቶን የዓሳ ምርት በየዓመቱ 15 በመቶ በማሳደግ በGTP-2 መጨረሻ በ2012 ዓ/ም ወደ 37,008 ቶን የዓሳ ምርት ለማድረስ ታቅዶ ወደ ተግባር በመግባት በዘረፉ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች አንደሚከተለዉ ቀርበዋል

 

  • የተከዜ የዓሳ ሃብት ልማት ጥቅም ላይ ለማዋል በርካታ ድጋፎች ተደርገዋል ፡፡
    • በክልሉ የዓሳ ጫጩት አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አንድ የዓሣ ጫጩት ማስፈልፈያና ማበዣ ማዕከል ማቋቋም መቻሉ
    • የዓሳ ማስገር ዝግ ወቅትን ሙሉ ለሙሉ ማስቆም ባይቻልም በየዓመቱ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች መኖራቸዉ በዚህም በሰዉ ሰራሽ ግድቦች ላይ ማስቆም የተቻለበት ሁኔታ መኖሩ
    • በአዲስ የተገነቡ ሰዉ ሰራሽ ግድቦች ላይ በመለየት በማጥናት እና የዓሳ ጫጩት በመጨመር የዓሣ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ በተጨማሪ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ /ርብ ግድብ ፣ቆጋ ግድብ እንዲሁም ገርይ ግድብ …/
    • የዓሳ ግብርናን ከማስፋፋት አኳያ አ/አደሮች ዓሳን ከደሮ እርባታ ፣ከመስኖ ልማትና ከአትክልትና ፍራፍሬ ጋር በማቀናጀት ማልማት መቻላቸዉ/አዊ ፣ምስራቅ ጎጃም ፣ምዕራብ ጎጃምና ሰ/ሸዋ ዞኖች /
    • የደጋ ዓሳ ጫጩት አቅርቦት ችግር ቢኖርም ከአጎራባች ክልል /ከኦሮሚያ/ ጋር በመነጋገር ከ85 ሽህ በላይ የደጋ ዓሣ ጫጩቶች ወደ አ/አደር ኩሬች መሰራጨት መቻላቸዉ/ሰሜን ሸዋ ዞን /
    • LFSDP ፕሮጀክት አማካኝነት የአ/አደር CIGዎችን በማደራጀት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኩሬ ተቆፍሮ የጫጩት ስርጭት ለማከናወን በዝግጅ ላይ መሆናችን
    • በተለያዩ ጊዜያት ከሚመለከታቸዉ የንግድ ፣ህብረት ስራ ማህበራት ፣የፖሊስና የምርምር ተቋማት ጋር በመዉጣት በመስክ በመዉጣት ከወጣውየዓሣማስገርናአዋጅ፣ደንብናመመሪያአኳያ፣የማስገርፈቃድናየብቃትማረጋገጫበመያዝየንግድፈቃድአውጥቶከመስራት እና ከዓሣምርትግብይትናግብዓትጋርበተያያዘያሉበት ደረጃ ፣ከአስጋሪአደረጃጀትአንጻርበግልበኢንተርፕራየዝእናህብረትስራ/ እናነጋዴ/የተደራጁአካላትያሉበትሁኔታናከዚህጋርተያይዞችግሮች በመለየት በርካታ ስረዎች መሰራታቸዉ

 

ሀ.ስልጠና- ለተሳትፎዊ የዓሳ አስተዳደር ኮሚቴዎች ፣ለዓሳ አስጋሪዎች ፣ለመምህራና ተማሪዎች እንዲሁም ለምግብ ቤት ሰራተኞች ለቤተ ክህነት አከላትና ለወረዳ ዓሳ ባለሙያዎች በዓሳ ድህር ምርት አያያዝና አጠቃቃም ፣በዓሳ ምግብ ጠቃሜታና ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡

 

ለ. የማስገሪያ መሳሪያ ግብዓት አቅርቦት-16 የዓሳ ማቀዝቀዣዲፕ ፍሪጅ ፣ጀልባ 28፣ላይፍ ጃኬት 20፣የዓሳ መያዣ ሳጥን 140፣የዉሃ ባልዲዎች 140 ፣የዓሳ ማጠቢያ ሳህን 40 ፣የዓሳ መበለቻ ቢለዋ 140 ፣የመረብ መስሪያ ክር ፣የመረብ መስሪያ መርፊ፣የተለያየ መጠን ያላቸዉ መንጠቆዎች ፣የዓሳ መበለች ጠረጴዛ ፣የዓሳ መመዘኛ ሚዛን እንዲሁም የዓሳ ማጓጓዣ የሞተር ጀልባ ደጋፍ ተደርጓል፡፡

 

. የዓሣ መበለቻና መገበያያ ሸድ ግንባታ /ዝቋላ፣ ሳህላ ሰየምት ፣አበርገሌ/እንዲሁም የሪስቶራንተ ህንፃ ግንባታ/ሰቆጣ ከተማና አበርገሌ /ወረዳዎች ላይ መገንባቱ

 

ሠ. የዓሳ ምርት ገቢያ በተመለከተየተከዜን የዓሣ ምርት ወደ ገበያ ለማድረስ 4 ፍሪጅ የተገጠመላቸው መኪኖች እንዲገዙ በማድረግ ለ4 ወረዳወች ማዳረስ መቻሉ

 

በድክመት

 

  • የወጡ የዓሣ ሀብት ልማና ጥበቃ ሕጎችና ደንቦች ተግባራዊ በማድረግ በኩል በሃይቆች ላይ ዉስንነት መኖር በተለይም የዓሳ ማስገር ፍቃድ አሠጣጥ መመሪያ ተግባራዊ አለመሆን
  • የዓሣ ተረፈ ምርትን ጥቅም ላይ ለማዋል ከዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዞች /ባለሀብቶች ጋር ተቀናጅቶ አለመስራት
  • ተሳትፎዊ የዓሳ አስተዳደር ኮሚቴዎች በማጠናከር በሙሉ አቅማቸዉ ወደ ስራ እንዲገቡ አለመደረጉ /በተለይም በሃይቆች የኮሚቴዎች መፍረስ መኖር /
  • በክልሉ በአዲስ የተገነቡ ሰዉ ሰራሽ ግድቦች ላይ በመሉ በማጥናት ተስማሚ የዓሳ ዝርያዎችን በመጨመር ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሪያ አለማድረግ
  • ሞኖፊላመንት መረብ በስፋት ከዉጭ በመተማ በኩል በህገ ወጥ መንገድ በመግባት በገቢያ ላይ የሚሽጥበት ሁኔታ በመኖሩ አብዛኛዉ አስጋሪ በዚህ መረብ መጠቀሙ እና በዓሳ ሃብት ልማቱ ሰፊ ጉዳት እያደረሰ ቢሆንም ማስቆም አለመቻሉ
  • በወንዞች ፔን ካልቸር እንዲሁም በግድቦች የኬጅ ካልቸር ቴክኖሎጅን ማስፋፋት አለመቻሉ እንዲሁም ግድቦች በሚገነቡበት ወቅት ለዓሳ ሃብት ልማት እንዲዉሉ ከሚመለከታቸዉ የምህንድስና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት አለመስራት
  • ሁሉም የመስኖተጠቃሚአርሶአደሮችባሉበትአካበቢዎችከሌሎቸየግብርናልማትእንቅስቃሴዎችጋርበማቀናጀትበአ/አደርደረጃ ኩሬ በማዘጋጀት በዓሳ ግብርና እንዲሳተፉ በማድረግ በኩል የተሰራዉ ስራ አናሳ መሆን
  • የዓሳ ግብርናን ከሩዝ ግብርና ጋር በማቀናጀት /አምባዛ /(የቀይ ዓሳ ዝርያዎችን) በሩዝ ማሳዎች ጫጩት በመጨመር አ/አደሮች የዓሳ ምርት ከማምረታቸዉ ባሻገር ከዓሳዉ የሚወጣዉ ፅዳጅ ለሩዙ ምርት መጨመር አሰተዋፅኦ ቢኖረዉም ወደ ስራ አለመገባቱ

 

 

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |