ዜና

በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 04 በወተት ሃብት ልማት ስራ ጥሩ እንቅስቃሲ እያደረጉ ያሉ ግለሰብ

አቶ እንድሪስ አደም ነዋሪነታቸው በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 04 ነዋሪ ሲሆኑ ግለሰቡ ከዚሀ በፊት የመንግስት ሰራተኛ የነበሩ ሲሆን ግለሰቡ ከ 2010 ዓ.ም ጀምሮ 5 የወተት ላሞችን በመያዝ ወደ ስራ የገቡ ሲሆን አሁን ላይ ጊደሮች እና ጥጃዎችን ጨምሮ ከ 30 ያላነሱ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸውን እንስሳት ይዘዋል፡፡ ግለሰቡ ለላሞቻቸው ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል እውቀትና እና የስራ ተነሳሽነት ያላቸው ሲሆን በባለሙያዎች ዘንድ የሚደረግላቸውን ድጋፍም በአግባቡ እንደሚተገብሩ የወተት ላም እርባታ ጣቢያቸውን በጐበኝንበት ወቅት ማረጋገጥ ችለናል፡፡

አቶ እንድሪስ በቀን ከ 200 ሊትር ወተት ያላነሰ የሚያገኝ መሆኑን ገልፀው ወተቱን የሚሸጡበትም ጦይባ የወተትና የወተት ተዋጽኦ መሸጫ የሚባል ድርጅት እንዳላቸው አክለዉ ገልፀውልናል፡፡

በአጠቃላይ የግለሰቡ የስራ እንቅስቃሴ ለሌሎት የህ/ሰብ ክፍሎች አርያነት ያለው በመሆኑ ከእሳቸው ተሞክሮ ተምረን የበለጠ ውጤታማ እንድንሆን እንትጋ መልዕከታቸን ነው፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |