ዜና

የአማራ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከብሄራዊ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ማአከል ጋር በመተባበር  ከታህሳስ 3—12/04/2013 ዓ.ም በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት ማአከል ቁጥራቸዉ 48 ለሚሆኑ የአዳቃይ ቴክኒሻን ባለሙያዎች የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ተሰጠ ፡፡

የአማራ ክልል እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ከሚሰራቸዉ ስራዎች አንዱ የእንስሳትን ዝርያ በመረጣና በማዳቀል የማሻሻል ስራ ነዉ፡፡ በክልሉ 310 የመንግስት፣23 የግል፣21 የአርሶ አደር እንዲሁም 23 በወተት ተፋሰስ ወረዳዎች በሚገኙ የወተት ህብረት ስራ ማህበራት ያሉ አዳቃይ ቴክኒሻኖች በጥቅሉ 377 የሚሆኑ አዳቃይ ቴክኒሻኖች በተለያዩ ጊዚያት በዝርያ ማሻሻል ስራ የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ እንዲገቡ አድርጓል ፡፡ ኤጀንሲዉ የእነዚህ አዳቃይ ቴክኒሻኖችን የመፈጸም አቅም በማሳደግ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከሚሰራቸዉ በርካታ ስራዎች አንዱ የሙያተኞችን አቅም በአጫጭር ስልጠናዎች በየጊዜዉ ማሳደግ ነዉ፡፡

በመሆኑም ኤጀንሲዉ ከብሄራዊ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል ማአከል ጋር በመተባበር ከታህሳስ 3—12/04/2013 ዓ.ም በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት ማአከል ቁጥራቸዉ 48 ለሚሆኑ የአዳቃይ ቴክኒሻን ባለሙያዎች የንድፈ ሀሳብና የተግባር ስልጠና እየሰጠ ሲሆን በስልጠናዉ የእንስሳት መረጣ፣የክብድና ምርመራ ፣የሴል ልየታ እንዲሁም የድቀላ ቴክኒክ ላይ ሰልጣኞች በዋናነት ስልጠና እንደሚያገኙ የኤጀንሲዉ እንስሳት ዝርያ ማሻሻል ባለሙያ የሆኑት አቶ አህመድ አልቃድር ገልጸዋል፡፡አቶ አህመድ አክለዉም በዚህ ስልጠና 2 ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የመጡ አዳቃይ ቴክኒሻኖች በስልጠናዉ ተሳታፊ የሆኑ መሆኑን ገልጸዉ እንዲህ አይነቱ ተግባር የሁለቱን ክልል ህዝቦች በትብብር በልማቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ታስቦ የተሰራ ተግባር ነዉ ብለዋል፡፡ በስልጠናዉ ተካፋይ የሆኑ ሰልጣኞችም ስልጠናዉ በክህሎት ረገድ የነበሩባቸዉን ክፍተቶች እንደሞላላቸዉ እና በቀጣይም ተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚያግዛቸዉ ገልጸዋል፡፡ በስልጠናዉ ተካፋይ ከነበሩት ሰልጣኞች ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የመጡ ሁለት ሰልጣኞችም የአማራ ክልል እንዲህ አይነት የተግባር ስልጠና በማዘጋጀቱና እና በስልጠናዉም እንዲሳተፉ ስላደረጋቸዉ የተሰማቸዉን ደስታ በመግለጽ ሁለቱም ክልሎች በቀጣይ በሁለንተናዊ መስክ ተደጋግፈዉ በመስራት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንዳለባቸዉ ገልጸዋል፡፡

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |