ዜና

የአብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ icipe Moyeshe ፕሮጀክትጋር በመተባበር ከታህሳስ 3__4/2013 በባህርዳር ከተማ የማር ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱ አካሄደ፡፡

 

የአማራ ክልል ባለው የአየር ፀባይ እና የመሬት አቀማመጥ ለተለያዩ የቀሰም እፅዋቶች እንዲኖሩ ምቹ አከባቢ በመሆኑ 

ለንብ ሃብት ልማት ተግባር ተስማሚ ነው ክልላችን 1,349,320 ህብረ ንብ እንዳለውና ከሃገር አቀፍ ጥቅል የህብረ 

ንብ ብዛት ደግሞ 20% ድርሻ እንዳለው 2012 የማዕከላዊ ስታትስቲክስ /CSA/ መረጃ ያሳያል፡፡

ክልሉ ካለው አጠቃላይ አግሮ ኢኮሎጂ አንፃር የቆላ እና ወይና ደጋ የመሬት ሽፋን 72.8% መሆኑ ለንብ ሃብት ልማት ስራ 

የበለጠ ተስማሚ ያደርገዋል፡፡ ክልሉ በማርና ሰም ልማት ከጥንት ጀምሮ ሲሰራበት የቆየ የካበተ ልምድ ቢኖረውም ዘመናዊ 

ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እና አሰራሩን ወደ ዘመናዊ የማነብ ዘዴ በማሸጋገር ከዘርፉ መገኜት ያለበትን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በአግባቡ እንዳያገኝ አድርጎታል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በንብ ሃብት ልማት ስራዎች መሬት አልባ ስራ አጥ 

ወጣቶችን በቡድን እና በኢንተርፕራይዝ በማደራጀት፣ የተሻለ የመልማት አቅም ያላቸውን የተከዜ ተፋሰስ እና የአባይ ሸለቆ አካባቢዎችን የንብ ሃብት ልማት ኮሞዲቲ ተቀርፆ ተግባራዊ እንዲደረግ በማመቻቸት እና ወጣቶች የተሻሻሉ 

የቴክኖሎጅ ውጤቶችንና ግብዓቶችን በመጠቀም በአካባቢያቸው ለሚገኙ አናቢ አርሶ አደሮች የቴክኒኖሎጅ ሽግግር 

ለማምጣት የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከዓለም አቀፉ የስነ ነፍሳት እና ስነ ምህዳር የምርምር 

ተቋም /icipe/ ከሚያስተባብራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ጋር በጋራ በመሆን ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡

ክልላችን ካለው እምቅ የንብ ሃብት አቅም አኳያ የአብክመ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከዓለም አቀፉ የስነ ነፍሳት እና ስነ ምህዳር የምርምር ተቋም /icipe/ ጋር በጋራ በመሆን ከ4 ዞኖችና 13 ወረዳዎች 

የተውጣጡ ማርና ሰም አምራች ኢንተርፕራይዞች፣ ማህበራት፣ ቡድኖች እና ግለሰቦችን ጨምሮ ሌሎች ተሳታፊ እንግዶች

በተገኙበት ከታህሳስ 03-04/2013 . በባህር ዳር ከተማ የፓናል ውይይትና ኤግዚቢሽኑን ተካሂዷል፡፡ ይህም ለገበያ ትስስር፣ 

ባለሃብቶችን ለመሳብ፣ ክልል አቀፍ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥና ለማስፋት፣ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ግብዓቶችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም ለዘርፉ መነቃቃት ታላቅ አስተዋፅዖ ይኖረዋል፡፡

 

ዓላማ

የንብ ውጤቶች ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱ የሚከተሉት ዋና ዋና ዓላማዎች ይኖሩታል፡-

Ø የአማራ ክልልን የማርና ሰም ምርት ለማስተዋወቅ

Ø  የማርና ሰም የግብይት ስረዓትን በማዘመን አምራቹ ምርቱን ቀድሞ የመሸጥምምነት እንዲጀመር ለማድረግ

Ø  ከፍተኛ የመግዛት አቅም ያላቸው ነጋዴዎች ወደ ክልሉ እንዲመጡ ለማድረግ እና በአምራችና በገዥ መካከል ያለውን የገበያ ትስስር ለማጠናከርና ጤናማ የገበያ ውድድር ስረዓትን ለመዘርጋት

Ø የቀፎ ውጤቶችን ለዓለማቀፍ ገበያ ለማቅረብ እንዲቻል የተሻለ ልምድ ለመውሰድ እና ምርቶቻችንን ወደ ውጭ በመላክ ዘርፉ ለአናቢዎች እና ለሃገር ኢኮኖሚ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ

Ø የማርና ሰም ምርትን እሴት በመጨመር የራሱ ብራንድ ያለው ምርት ለገበያ ለማቅረብ የሚያስሉ ተሞክሮዎችና ልምዶችን ለመውሰድ

Ø ዘመናዊ የምርትና ግብይት ሥረዓትን ለመዘርጋት የሚመለከታቸውን ባለ ድርሻ አካላት ያሳተፈ ኮንፈረንስ በማድረግ ችግሮቻችንን በጋራ በመለየት ለቀጣይ ስራዎቻችን ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር

 

 

ግብ

Ø በክልሉ ውስጥ በማርና ሰም ምርትና ግብይት ስራዎች ላይ የሚሳተፉ ተዋናዮችና ባለ ድርሻ አካላት በጋራ በመሆን የንብ ውጤቶች ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንስ በክልል ደረጃ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት በብቃት መፈፀም፡፡

 

የኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱ አስፈላጊነት

Ø የማር አምራቹን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና የሃገር አቀፍ ገበያን ለማመቻቸት፣

Ø  ከገበያ ትስሰር ጋር በተያያዘ የምርትና ግብይት ተዋንያንን አቅም ለመገንባት፣

Ø በሚቀርቡ ጥናታዊ ፅሑፎች በቂ ክህሎት እና ልምድ ለማግኘት፣

Ø የክልሉን የማርና ሰም ምርት ለማስተዋወቅ፤

Ø  በማር ምርት ጥራትና አስተሻሸግ ዙሪያ ልምድ ለማግኘት፤

Ø  በዘርፉ ስራዎች ዙሪያ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት፣

 

ከየኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱ የሚጠበቅ ዉጤት

Ø የግብይት ተዋንያኖች ስፊ የግብይት ልምድ ያገኛሉ፣

Ø  የክልላችን የንብ ሃብት አቅም ማስተዋወቅና ባለሃብቶችን መሳብ ያስችላል

Ø  የንብ ሃብት ልማት የስራ እንቅስቃሴ የበለጠ መነቃቃት ይችላል 

Ø  በማር፣ ሰምና ሌሎች የቀፎ ውጤቶች ዘላቂ የገበያ ትስስር ይፈጠራል፣

Ø  ባለሙያዎች ከኮንፈረንሱ በቂ ልምድና ክህሎት ያገኛሉ፣

Ø ከተለያዩ ተሞክሮዎች የተሻሉ ልምዶችን ማግኜት ይቻላል

 

በኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱ የተሳተፉ አካላት

በክልል ደረጃ በተካሄካሄደው የንብ ውጤቶች ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን የክልሉ ርዕሰ መስተረዳድር አማካሪ አቶ ዓለሙ

ጀምበርን ጨምሮ የቢሮ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣የicipe አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ ዞኖች እና 13 ወረዳዎች ዋና አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የማርና ሰም አምራቾች፣ በዘርፉ ወደ ስራ የገቡ ቡድኖች፣ ኢንተርፕራይዞች፣ ማህበራት፣ነጋዴዎች፣ ዩኒኖች፣ የማርና ሰም ግብዓት 

አቅራቢዎች፣አቀነባባሪዎች፣ ዘርፉን የሚደግፉ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማቶች፣ አገልግሎት ሰጭ የመንግስት መስሪ ቤቶች፣

የምርምር ተቋማት  እና የመሳሰሉት ተሳትፈዋል፡፡

የፓናል ውይይቱ በዩኒሰን ሆቴል ለ2 ቀናት የተካሄደ ሲሆን የአራቱም ዞኖች ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የተገኙ ውጤቶችን በቀጣይ

አጠናክሮ ለማስቀጠል እና የዘርፉ ዋና ዋና ችግሮች ናቸው ተብለው የቀረቡትን የብድር አቅርቦት ችግር፣ የገበያ ትስስር ማነስ፣

ህገ ወጥ የኬሚካል ርጭት እና የመሳሰሉት ሃሳቦች ላይ ምክክር በማድረግ በቀጣይ ችግሮቹን ለመቅረፍ በሚያስችሉ መፍትሄዎች

ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

የንብ ውጤቶች ኤግዚቢሽን በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ለተመሳሳይ 2 ቀናት የተካሄደ ሲሆን ከ4 ዞኖች የተመረጡ ከ13

ወረዳዎች የተገኙ ማር አምራች ወጣቶች ጥራቱን የጠበቀ ማር፣ ሰም እና ፕሮፖሊስ በማቀነባበር እና በማሸግ ለኤግዚቢሽን

በማቅረብ ለከተማው ህብረተሰብ በማስተዋወቅ ግብይ ተካሂዷል፡፡

 

በመጨረሻም YESH ፕሮጀክት ከሚሰራባቸው 13 ወረዳዎች በስራ አፈፃፀም 1ኛ ደሃና ወረዳ፣ 2ኛ አዋበል ወረዳ፣ 3ኛ ጓንጓ

ወረዳ በደረጃ ተለይተው ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

 

 

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |