ዜና

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2012 እቅድ አፈፃፀም እና የ2013 የእቅድ በቴክኒክ ኮሚቴ ተገመገመ፡፡

የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2012 በጀት አመት የዋና ዋና ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና የ2013 በጀት አመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በ 3/01/2013 ዓ.ም በእንጀባራ ከተማ አካሄደ፡፡ ፕሮጀክቱ በበጀት አመቱ ያከናወናቸዉን ዋና ዋና ስራዎች ያቀረበ ሲሆን

ከወጣቶች አንጻር የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች በተመለከተ

በደሮ ለ2460 ወጣቶች(ሴ 1007) ለ1 ወጣት ባአማካኛ 25 ደሮዎችን እና የደሮ መጠላይ ግንባታ፣መኖ፣ መመገቢያና መጠጫ ቁሳቁስ የማሟላት

በቀይ ስጋ ለ1405 ወጣቶች (ሴ 348) በአማካኝ ለ15 ወጣቶች 30 በግ፣የበግ መጠለያ ፣መኖ፣መመገቢያና መጠጫ ቁሳቁስ የማሟላት

በአሳ ለ170 ወጣቶች(ሴ 25) የሸድ ግንባታ፣የመበለቻ ቁሳቁስ፣ዲፕ ፍሪጅ ፣ጄኔረተር እና የማጓጓዣ ቁሳቁሶችን የማሟላት ስራ መከናወኑ ተጠቅስዋል፡፡

በወተት ለ6023 አርሶ አደሮች (ሴ2081) የወተት ላሞችን ቤት በአዲስ የመገንባትና የማሻሻል፣ መኖ የማቅረብ እንዲሁም መመገቢያና የመጠጫ ገንዳ የማዘጋጀት ስራ የማሟላት

በደሮ ለ5341 አርሶ አደሮች (ሴ 3257) ለ 1 አርሶ አደር ባአማካኝ 25 የእንቁላል ጣይ ደሮዎችን ገዝቶ የማቅረብ፣ሸድ የመገንባት ፣መኖ የማቅረብ እና መመገቢያና የመጠጫ ቁሳቁሶችን አሟልቶ የማቅረብ

በቀይ ስጋ ለ4658 አርሶ አደሮች (ሴ1548) የበግ ጋጣ የማሻሻል፣መኖ ማቅረብ እንዲሁም መመገቢያና መጠጫ የማሟላት

በአሳ ለ 85 አርሶ አደሮች (ሴ9) የአሳ ኩሬ የማዘጋጀት፣መበለቻ ሸድ የመገንባት፣የአሳ ጫጩት ኩሬ ላይ የመጨመር፣ዲፕ ፍሪጅና ጀኔረተሮችን ገዝቶ የማቅረብ እንዲሁም የማስገሪያ ፣የመበለቻ እና የማጓጓዣ ቁሳቁሶችን ገዝቶ የማሟላት ስራ መከናወኑና ከላይ ለተጠቀሱ አጠቃላይ ተግባሮች 127,321,160 ብር ስራ ላይ መዋሉ በሪፖርቱ ተመላክትዋል፡፡

ከአርሶ አደሮች አንጻር የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች በተመለከተ

ፕሮጀክቱ በወጣቶችና በአርሶ አደር ደረጃ ካሉ ተጠቃሚዎች ከሚሰራዉ ስራ በተጨማሪ በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ የሚሰሩ ተቋማትን በግብአትና በመሳሰሉ ጉዳዮች የማጠናከር ስራ እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በዚህ ዙርያ በበጀት አመቱ

  • ለአርሶ አደር ሰርቶ ማሳያዎች ሞዴል መገንባትና ቁሳቁስ ማሟላት
  • ለወረዳ እና ለቀበሌ የእንስሳት ጤና ክሊኒኮች የህክምና ቁሳቁሶችን የማሟላት
  • ለአርሶ አደር ሰርቶ ማሳያዎች የመኖ ዘር እና ቴክኖሎጂ አቅርቦት
  • ለ 2 ላብራቶሪ ቁሳቁስ ግዥ
  • ለ 15 ወረዳዎች 15 መኪናዎች እና ለ 2 ላቦራቶሪዎች ለእያንዳንዳቸዉ 5 መኪናዎች
  • ለ15 ወረዳዎች 37 ሞተር ባይስክል ግዥ
  • ለባህር ዳር አሣ ምርምር ማዕከል ለአሣ ጫጩት ማምርቻ የሚያገለግል ቁሳቁስ የማሟላት
  • ለPPR መከላከልና ቁጥጥር

ድምር 28,935,170 ብር ስራ ላይ መዋሉ ተመላክትዋል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ በዝርዝር የተከናወኑ ስራዎች ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም ኘሮጀክቱ ያቀዳቸውን ስራዎች በአብዛኛው{94%} ከማሳካት አንፃር የሄደበት ርቀት የተሻለ መሆኑ መድረኩን በመሩት የኤጀንሲዉ ም/ስራ አስኪያጅና የቴክኒካል ኮሚቴዉ ሰብሳቢ በሆኑት በአቶ ፈንቴ ቢሻዉ እና በተወያዮቹ ተገልፃል፡፡ በአፈፃፀም ረገድ የታዮ ውስንነቶች ላይም በቀጣይ መሻሻል እንዳለባቸዉ ሰብሳቢዉ አሳስበዋል፡፡ በቀጣም የተሻለ ስራ ለመስራት ቅንጀቲዊ አሰራሮች ከላይ እስከ ታች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመድረኩ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኘሮጀክቱ የ2013 እቅድ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ እቅዱን የሚያዳብሩ ሀሳቦች ከተወያዮቹ ቀርቦ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |