ዜና

የንብ ሃብት ልማትን ለማዘመን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እና በተሰሩ ስራዎች የህ/ሰቡ ተጠቃሚነት በተለይ ዘርፉ ለወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር ያለው ፋይዳ

በኢትዮጰያ 6,523,969 የሚጠጋ የንብ መንጋ ብዛት እንዳለ የCSA-2010 መረጃ ያሳያል ከዚህም ውስጥ በአማራ ክልል 1,154,094 የንብ መንጋ ብዛት እንዳለ ያሳያል ይህም ከሃገሪቱ የንብ ሃብት ብዛት 17.7% ድርሻ ይኖረዋል ማለት ነው እንዲሁም በ2010 CSA መረጃ መሰረት በአማራ ክልል 1,115,835 ባህላዊ ቀፎ እንዲሁም 5,986 የሽግግር ቀፎ እና 32,273 ዘመናዊ ቀፎ ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡ የንብ ሀብት ተግባር ከተለያዩ አቅጣጫወች ሲታይ ሁለገብና አስተማማኝ ዘላቂ የሆነ ጥቅም የሚያስገኝ ስራ ነው፡፡ ከጤና አንጻር በመዳህኒትነት የሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮችን የያዘና በምግብነትም ከፍተኛ የሆነ የሀይል ምንጭ ሲሆን ፣ ከኢኮኖሚ ጠቀሜታ አንጻር ሲታይ በቀጥታ

የንብ ውጤቶችን ማለት ማር ሰም   ዞፍ (የንብ ሙጫ) ድኝ መርዝ ለገበያ በማቅረብ ገቢ የሚያስገኝ ዘርፍ ነዉ፡፡የንብ እርባታ ስራ በአነስተኛ የመነሻ ካፒታልና በውስን የመሬት ይዞታ ወደ ልማቱ በማስገባት የምግብ ዋስትናን ያረጋግጣል፡፡ ዘርፉ በርካታ ስራ አጥ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በአጭር ጊዜ ስልጠና ሰጥቶ ወደ ልማቱ በማስገባት የስራ እድል ሊፈጥር የሚችል የስራ መስክ ነው፡፡ ንቦች እንደ ሌሎች ተመሳሳይ በራሪ ነፍሳት በማንኛውም የእነባ ዘዴ፡- የእጽዋትን ሽፋን በመጨመር ፣የአፈር መሸርሸርን በመከላከልና የውሀ ስርገትን መጨመር ጎርፍን በመቀነስ የበለጠ ምቹና አስተማማኝ አካባቢን ይፈጥራሉ:: እንዲሁም ውብና ጽዱ አካባቢን ለመፍጠር የንብ ሀብት ተግባራት ከማርና ሰም ምርት ያለፈ ወሳኝ ተግባር ያላቸው መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት የወጡ መረጃወች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ሲታይ የንብ ማነብ ስራ የሰብል ምርትን በመጨመር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አንጻር አይነተኛ አማራጭ ነው፡፡ ንቦች እጽዋትን በማራከብ ከ20-140% የእጽዋትን ምርት እንደሚያሳድጉ ልዩልዩ መረጃወች ይጠቁማሉ፡፡ ከ300 የገበያ ሰብሎች /commercial crops/ ውስጥ 84% ያህሉ በነፍሳት የሚዳቀሉ ናቸው፡፡ አማራ ክልል የንብ ሃብት ልማት ምቹ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች ስንመለከት ፡-ክልሉ ለንብ እርባታ ስራ ተስማሚ ስነ ምህዳር ያለዉ ክልል ነዉ ፡፡በክልሉ ከ800 በላይ የማር የቀሰም እፅዋቶች ይገኛሉ፡፡በአማራ ክልል የንብ ማነብ ስራ ለረጅም ዘመናት ሲከናወን የነበረ ተግባር በመሆኑ የአናቢዎች ከባቢያዊ እውቀት እና ልምድ የተሻለ መሆኑ ለንብ ማነብ ስራዉ ምቹ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑና የንብ ሃብት ፖሊሲና ስትራቴጂ መቀረፁ ፣ የንብ ሃብት ልማትን የሚደግፉ አዋጆች፣ደንቦችና መመሪያዎች መዘጋጀታቸው ፣ለገጠር ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ካለው ድርሻ አንፃር የመንግስት ዋነኛ አጀንዳ መሆኑ የማር ምርትና ምርታማነት በመጨመሩ ወደ ገበያ የሚወጣው የማር ምርት ከዕለት ወደ ዕለት እያደገ መሄዱና አማራጭ የገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱ ፣ እንዲሁም የተመረተውን የማር ምርት የገበያ ችግር ለመቅረፍና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ የሚያስችሉ 5 የማር ምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች መኖራቸው እና ዘርፉን በምርምር፣በአቅም ግንባታ፣ በግብዓትና ቴክኖሎጂ ስራዎች የሚደግፉ አካላት /ተቋማት መኖራቸው ፣ እና በዘርፉ በርካት መንግስታዊ ልሆኑ ድርጅቶች የዘርፉን ልማት ለማገዝ እያሳዩት ያለዉጥረት አበረታች መሆኑና በለሙ ተፋሰሶች ላይ ከኬሚካል ርጭት ነፃ የሆነ የንብ እርባታ ስራ ለመስራት አመቺ መሆኑ ሀብቱን ለማልማት በምቹነት የሚጠቀሱ ጉዳዮች ናቸዉ፡፡ በተቃራኒዉ የንብ ሃብት ልማትና ግብይት ዋና ዋና ችግሮች ተብለዉ ከተለዩት ዉስጥ ፡-የባለሙያዎችና አናቢዎች የክህሎት ከፍተት መኖር፣ የማነቢያ ቁሳቁሶች በበቂ ሁኔታ አለመሟላትና ፡- የዋጋ ውድነት፣ የአቅርቦት ማነስ፣ የጥራት ችግሮች መኖር፣ህገ ወጥ የፀረ ተባይና ፀረ አረም ኬሚካል አጠቃቀም ፣ የማር ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ አለመግባት ፣ በማር እና ሰም ምርት የተደራጁ የንብ ውጤቶች ልማትና ግብይት ኅ/ሥራ ማህበራቶች የተጠናከሩ አለመሆን እና ዘላቂነት ያለው የገበያ ትስስር አለመኖር፣ የዘርፉን ልማት ለማዘመን በመሰረታዊነት ሚጠቀሱ ተግዳሮቶች ናቸዉ፡፡ ንብ አናቢዉ የህብረተሰብ ክፍል ዘመናዊ አሰራሮችን ተከትሎ እንዲያንብና የማር ምርትን በብዛትና በጥራት አምርቶ ራሱንና ሀገሩን የበለጠ ተጠቃሚ እንዲያደርግ የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ወደፊትም ይበልጥ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |