ዜና
የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከሴፍ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በቀን 11/02/2012 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ የወተት ቀን አከበረ፡፡
የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከሴፍ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በቀን 11/02/2012 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ የወተት ቀን አከበረ፡፡ በበአሉ ጥሪ የተደረገላቸዉ የክልል፣የዞን እና የወረዳ ተሳቴፊዎች እና የዳንግላ ከተማ 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ በአሉን አስመልክቶ የፕሮጀክቱ ሀላፊ አቶ ደስታ ዳመና እንደገለጹት ሴፍ ፕሮጀክት በአማራ ክልል በ2 ዞኖች በምእራብ ጎጃምና በአዊ ብ/አ/ዞን በሚገኙ 4 ወረዳዎች የወተት ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ እና ገቢን በመጨመር በሴቶችና
ወንዶች ፍትሀዊ
ሀብት ተጠቃሚነት ላይ አልሞ የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም የወተት ቀን በአልን በተማሪዎች ምገባ መልክ ማካሄድ ያስፈለገበትን ሁኔታ በዝርዝር ለታዳሚዎች አስረድተዋል፡፡ በመቀጠልም ለበአሉ ተሳታፊዎች እና ለተማሪዎች የወተት ምገባ ስነስርአት ከተካሄደ በኋላ በወተት ሀብት ልማት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ በኤጀንሲዉ በኩሉ አጭር መነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ዉይይት በማድረግ የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡