የአብክመ እ/ሀ/ል/ማ/ኤጀንሲ ተግባርና ኃላፊነት

የክልሉ እ/ሃ/ል/ማ/ኤጀንሲ በዚህ አዋጅ መሰረት የሚከተሉት ዝርዝር ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

1) ዘርፉን በሚመለከት ቀደም ሲል  የወጡና ለወደፊት የሚወጡ ፖሊሲዎችን ስትራቴጅዎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በክልሉ ውስጥ ያስፈፅማል፣ ይቆጣጠራል፡፡

2) በክልሉ ውስጥ የሚገኙ የእንስሣት ዝርያዎች በልማት ቀጠናዎች ይለያል፣ የልማት ቀጠናውን መሰረት ያደረገ ስትራቴጅክ እቅድ ያዘጋጃል፣ ይተገብራል፣ ይከታተላል ይቆጣጠራል፡፡

3) የእንስሣት መኖ ልማት ያካሂዳል፣  የግጦሽ መሬትና የእንስሣት ዝርያ እንዲሻሻልና እንዲጠበቅ ያደርጋል፡፡

4) የእንስሣት ሃብት ልማት ጤና አጠባበቅ ፖኬጆች ይፈጽማል፣ ይከታተላል፣ ከምርምር አካላት ጋር በመቀናጀት ያሻሽላል አዳዲሶችንም እየለየ ይቀርፃል፣ ቴክኖሎጅን አባዝቶ ያስፋፋል፡፡

5) የእንስሣት ምርት ግብዓት አቅርቦትና ብድርን ያመቻቻል፣ ያስተባብራል፡፡

6) የእንስሣት የመጠጥ ውሃ እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር የውሃ እጥረቱ እንዲፈታ ያደርጋል፣ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፡፡

7) የሃገር ውስጥ እንስሣትን ዝርያ ለመጠበቅ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በቅንጅት ይሰራል፡፡

8) የእንስሣት ሃብት ልማቱን ከደን ልማቱ ጋር በማቀናጀት ከደን ልማቱ ውስጥ የሚገኙ ውጤቶችን በአግባቡ ለመጠቀም ከሚመለከታቸው  አካላት ጋር በቅርብ ይሰራል፡፡

9) አግባብ ካላቸው ባለድርሻዎች ጋር በመተባበር ህጋዊና ህገ ወጥ ፣ የቆዳና ሌጦ  የእንስሣት እርድ፣ የግል እንስሣት መድሃኒትና የክሊኒክ አገልግሎት ንግድና ሌሎች ንግዶችን ይቆጣጠራል፣ የብቃት መስፈርቶችን ያወጣል፣ ማስረጃ ይሰጣል፣ በወጡና በሚወጡ ህጐች መሰረት እርምጃዎችን ይወስዳል፣ እንዲወሰዱ ያደርጋል፡፡

10) በክልሉ ውስጥ የእንስሣት ንግድ የጉዞ መስመሮችን በመለየት በህግ እንዲታወቁና ተገቢውን ጥበቃ እንዲያገኙ ያደርጋል፤ የኳራንታይንና የፍተሻ ማዕከላትን ያደራጃል፣ ከአጐራባች ክልሎችና ከፌደራል መንግስት አካላት ጋር በትብብር ይሰራል፡፡

11) የበሽታ መከላከልን መሰረት ያደረገ የእንስሳት ጤና አገልግሎት ይሰጣል፣ የእንስሳት በሽታዎች ምርመራ፣ አሰሳና ቁጥጥር ስራዎችን ያካሂዳል፣ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ የእንስሳት እንቅስቃሴን ይገድባል፣ ክልል አቀፍ የበሽታ ቁጥጥር ስትራቴጂ ይነድፋል፣ ነፃ የበሽታ ቀጠናዎችን ያቋቁማል፤

12) ለዘርፉ ልማትና ጥበቃ የሚያስፈልጉ መሰረተ ልማቶችን ያቋቁማል፣ እንዲቋቋሙና እንዲስፋፉ ያደርጋል፣ አደረጃጀታቸውን በማሟላት ሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፣

13) ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ከበሽታ ነፃ የሆነና ጥራቱ የጠበቀ ስጋ እንዲቀርብ በቄራዎች የስጋ ምርመራ እንዲካሄድ የደርጋል፣ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ደረጃውን የጠበቁ ቄራዎች በየከተሞች እንዲገነቡ ያደርጋል፤

14) በዘርፉ የተሰማሩ ባለሀብቶች ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ የእንስሳት ምርት እንዲያቀርቡና አገልግሎት እንዲሰጡ ያደርጋል፣ የአቅም ግንባታ ስራና የሙያ ድጋፍ ይሰጣል፤

15) ለእንስሳት ምርቱ የገበያ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣ የገበያ መረጃ ለተጠቃሚው በወቅቱ እንዲደርስ ያደርጋል፤

16) በየደረጃው የእንስሳት ጤና አጠባበቅ አገልግሎትን ለማሻሻል የሚያግዙ የእንስሳት እርባትና ጤና ባለሙያዎች ምክር ቤቶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ያቋቁማል፤ይከታተላል፣ይደግፋል፤

 

17) ውሎችን ይዋዋላል፣ የንብረት ባለቤት ይሆናል፣ በህግ መሰረት ይከሳል፣ ይከሰሳል፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |