ዜና

ክልላዊ የወተት ቀን በዓል ተከበረ

milk day dangela (29)የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ጽ/ቤት በምዕ/አማራ ክልል፣ የዞን እና የማዕከላት የዘርፉ ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በደንግላ ከተማ የወተት ቀን በአልን አክብሯል፡፡

ኘሮግራሙን በንግግር የከፈቱት የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ ዶ/ር ጋሻው ሙጨ ሲሆኑ ሀላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው ክልላችን ሰፊ የሆነ የእንስሳት ሃብት ክምችት ያለው መሆኑን እና ይህንን ሃብትም ለማልማትና በአግባቡ ለመጠቀም በመሰረታዊነት በእንስሳት መኖ ልማትና ስነ-አመጋገብን ማሻሻል፣ በእንስሳት ዝርያ ማሻሻል እንዲሁም በእንስሳት ጤና አጠባበቅ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በተሰሩ ስራዎችን ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል

 

ዜና

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማ ፕሮጀክት ከጋራ ፍላጎት ቡድን ወደ መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበር ያደጉ ማህበራትን አፈጻጸም ገመገመ ፡፡

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማ ፕሮጀክት በ2011 በጀት አመት በክልሉ በ15 ወረዳዎች በ4 የእሴት ሰንሰለት ለመስራት ወደ ተግባር ስራ የገባ ሲሆን ፕሮጀክቱ እስከ 2014 በጀት አመት 2700 የጋራ ፍላጎት ቡድኖች 36851 አባላትን በቀይ ስጋ ፣ በወተት ፣ በዶሮ እና በዓሳ ተጠቃሚዎችን አደራጅቶ ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል ፡፡ ከእነዚህ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች አሁን ላይ 82 ህብረት ስራ ማህበራት 5839 ተጠቃሚዎችን በማቀፍ በ4ቱ የእሴት ሰንሰለቶች ተደራጅተው ወደ ስራ ገብተዋል ፡፡

ፕሮጀክቱ የህብረት ስራ ማህበራትን አፈጻጸም ለመገምገም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ4/11/2014 ዓ.ም በጎንደር ከተማ የግምገማ መድረክ አካሄዷል ፡፡

ዜና
websitebahirdar (24)የክልሉ እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ከዞን ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ፣የማዕከላት ሃላፊዎችና ፣የአዳቃይ ባለሙያዎች እንዲሁም የክልል ሃላፌዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ሰኔ 30/14ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ የ2014 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2015 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ አካሄደ፡፡ የ2014ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም በአቶ ጀማል ሙሃመድና በጽ/ቤቱ ሃላፊ በዶ/ር ጋሻው ሙጨ የ2015 ዓ.ም እቅድ ትውውቅ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ጽሁፍ ላይም የክልሉን የእንሰሳት ሃብት ፖቴንሻል ለይቶ በመስራት ረገድ፣ ከዘርፉ ልማት አንፃር የተሰሩ ስራዎችንና በተገኑ ውጤቶች ላይ እንዲሁም ወደሃላ የቀረንባቸውን የዘርፉን ስራዎች በቀጣይ በጀት አመት ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለብንና ዘርፉን በዘላቂነት ውጤታማ አድርጎ ለማስቀጠል የሁሉም ሃላፊዎች ፣ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድረሻ አካላት እርብርብ እንደሚጠበቅ በመድረኩ ተነስቶ ሰፌ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡  

ዜና

የአብክመ ህብረት ስራ ማደራጃ ባለስልጣን ከክልሉ እንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ጋር በመሆን በእንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ፕሮጀክት ድጋፍ በቀይ ስጋ፣በወተት፣በዶሮ እና በአሳ ሀብት ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ የጋራ ፍላጎት ቡድኖችን እና መሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራትን ከማደራጀት አንፃር የተሰሩ ስራዎችን በተመለከተ የሁለቱ ተቋማት ሰራተኞች በተገኙበት ገመገሙ።

መድረኩን የከፈቱት የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሀላፊ የሆኑት አቶ ወልደተንሳይ ሲሆኑ ሀላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው የእንሰሳት ሃብት ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው ያለው ፋይዳ ትልቅ መሆኑን ገልፀው በዚህ ዘርፍ የተሰማሩ አካላትን የተሻለ ውጤታማ እንዲሆኑ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የማደራጀት እና የድጋፍ እና ክትትል የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ይሰራል ብለዋል። ለዚህም ሁሉም የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች ሀላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ አሳስበዋል።

የእንሰሳት እና አሳ ሃብት ልማት ፅፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ዶር ጋሻው ሙጨ በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት በዚህ መልኩ ስራ በጋራ መገምገማቸው ጥንካሬዎችና እጥረቶችን ለይቶ በቀጣይ ስራን ቆጥሮ በመከፋፈል ወደ ስራ ለመግባት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል። ሀላፊው አክለውም ወደፊት ተመሳሳይ መድረኮች እየተፈጠሩ ስራን በጋራ የመገምገም ስራ ይሰራል ብለዋል።

ዜና

የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በእንስሳት ጤና ለገጠር ልማት (HEARD) ፕሮጀክት በታቀፉ ወረዳዎች ለሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጠ፡፡ 

heard selected dessi02 (35)ስልጠናው በምስራቅ አማራ ለሚገኙ ዞኖች ዋግኽምራ ብሔረሰብ ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ኦሮሞ ብሔረሰብ  እና ሰሜን ሽዋ ዞን ለሚገኙ የዞንና እንስሳት ጤና ቡድን መሪዎች እና ለወረዳ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች የዶሮ ፈንግል ክትባት(NEWCASTLE_DISEASE) አሠጣጥ ዙሪያ የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና በደሴ ከተማ ተሰጠ ።

የዕለቱን መድረክ የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሬክቶሪት ዳይሪክተር ዶ/ር ተምሩ ተሰማ የማህበረሰብ አቀፍ የዶሮ ፈንግል በሽታ አደገኛ የሆነ በሽታ በመሆኑ ሰልጣኞች የሚሰጣቸው የንድፈ ሃሳብ እና የተግባር ስልጠና በመከታተልና በዶሮ ፈንግል ክትባት አሰጣጥ ዙሪያ በቂ እውቀት በመያዝ በየወረዳዎቻቸው ክትባት የሚሰጡ ሴቶች በመመልመል የወሰዱትን ስልጠና እንዴሰጡ አሳስበዋል ።

 

ዜና

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በእንስሳት ጤና ለገጠር ልማት (HEARD) ፕሮጀክት በታቀፉ ወረዳዎች ለሚገኙ የመንግስትና የግል እንስሳት ጤና ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ፡፡

heard selected DESSI 01 (35)ስልጠናው በምስራቅ አማራ ለሚገኙ ዞኖች ዋግኽምራ ብሔረሰብ ፣ ሰሜን ወሎ፣ ደቡብ ወሎ፣ኦሮሞ ብሔረሰብ እና ሰሜን ሽዋ ዞን ለሚገኙ የዞንና እንስሳት ጤና ባለሙያዎች እና ለወረዳ የእንስሳት ጤና ብድን መሪ ፣ ለመንግስት እንስሳት ጤና ባለሙያዎች እና ለግል የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች በመንግስትና በግል የእንስሳት ጤና ተቋማት ጥምረት ላይ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችና በግል እንስሳት ጤና ተቋማት ለመሰማራት የወጡ መመሪያዎችን በግልፅ አውቆ በቀጣይ የእንስሳት ጤና አገልግሎት በጋራ ተቀራርቦ ለመስራት የሚያግዝ ስልጠና በደሴ ከተማ ተሰጠ ፡፡

መድረኩን የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሮክቶሪት ዶ/ር ተምሩ ተሰማ የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት በአስር አመት እቅዱ ላይ አሁን ያለውን 10% የሚሸፍነውን የግል የእንስሳት ጤና ተቋማት ለማሳደግ የግል የእንሳሳት ጤና ባለሙያዎችን በማበረታታትና አቅም በመገንባት በቀጣይ 10 ዓመት ውስጥ የግል የእንስሳት ጤና ተቋማትን ሽፋን 35% ለማድረስ አቅዶ እየሰራ ነው ፡፡

 

ዜና

በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለወረዳና ለቀበሌ የእንሰሳት ጤና ባለሙያዎች በደሴ ከተማ ስልጠና ተሰጠ

Dessi select FOA (35)የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ከአለም ምግብና እርሻ ድርጅት(FAO) ባገኘው የበጀት ድጋፍ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አራት ዞኖች ውስጥ ለሚገኙ ስድሰት ወረዳዎች መቄት ፣ ታች ጋይንት ፣ ሰቆጣ ዙሪያ ፣ አምባሰል ፣ ወረባቡ እና ተሁለደሬ ወረዳ የሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችን ለአምስት ተከታታይ ቀናት በደሴ ከተማ ስልጠና ተሰጠ ።

ስልጠናውን የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ተሰማ በእንስሳት ጤና ላይ እየተሰሩ የነበሩ ስራዎች በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ በመሆኑ የበሽታ ፍንዳታዎች እየተከሰቱ ስለሆነ የእንስሳት ጤና ባለሙያውን ስልጠና በመስጠት እና የግብዓት አቅርቦት በመስጠት ክትባቶች በዘመቻ መልኩ ለመስጠት የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል ።

 

ዜና

በአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ለወረዳና ለቀበሌ የእንሰሳት ጤና ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ ።
Healthy selected (34)የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ከአለም ምግብና እርሻ ድርጅት(FAO) ባገኘው የበጀት ድጋፍ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አራት ወረዳዎች ጠለምት ፣ አዲአርቃይ ፣ ደባርቅ እና ላይ ጋይንት ወረዳ የሚገኙ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎችን ለአምስት ተከታታይ ቀናት በደብረ ታቦር ከተማ ስልጠና ተሰጠ ።ስልጠናውን የከፈቱት የክልሉ እንስሳት ጤና ዳይሬክቶሪት ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ተሰማ በእንስሳት ጤና ላይ እየተሰሩ የነበሩ ስራዎች በጦርነቱ ምክንያት ተቋርጦ የነበረ በመሆኑ የበሽታ ፍንዳታዎች እየተከሰቱ ስለሆነ የእንስሳት ጤና ባለሙያውን ስልጠና በመስጠት እና የግብዓት አቅርቦት በመስጠት ክትባቶች በዘመቻ መልኩ ለመስጠት የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል ።የስልጠና ጽሑፎን አዘጋጅተው ያቀረቡት የባህርዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ እና የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ የተወጣጡ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያዎች

 

ዜና 

ሃገር አቀፍ የንቦች ቀን ግንቦት 12 በባህር ዳር ከተማ ተከበረ

Honeyexpo (50)በኢትዩጽያ ከ10-12 ሚሊዩን ህብረ ንቦች እንዳሉ የተለያዩ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ከዚህ ሀብት ከ500000 ቶን ማር እና ከ50000 ቶን በላይ ሰም ምርት ማምርት እንደሚቻል መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ ይሁን እንጅ አሁን ላይ እየተመረተ ያለው ከ53000 ቶን በላይ ማርና ከ3800 ቶን ያልበለጠ የሰም ምርት ነው፡፡ ከአለን አቅም አንፃር ሲታይ የሚመረተውምርት ከ10% አይበልጥም ፡፡ ያም ሁኖ በአፍሪካ ከሚመረተው የማር ምርት 27% ከኢትዮጵያ ይሸፍናል፡፡ ከዓለም ደግሞ 2.7% የማር ምርት ድርሻ በማበርከት ከዓለም 10 ደረጃ ትገኛለች፡፡ በሰም ምርትም ከዓለም በ4ኛ ደረጃ በአፍሪካ 1ኛ ደረጃ ትገኛለች ፡፡ ወደ ክልላችን ስንመጣ በአማራ ክልል ከ1.3ሚ ያላነሰ ህብረ ንብ ይገኛል፡፡ ከዚህ ሃብት በዓመት እስከ 4ዐ000 ቶን የማር ምርት 4ዐዐ ቶን የሰም ምርት ማምረት ቢቻልም አሁን እየተመረተ ያለው 25000 ቶን ማር 1800 ቶን ሰም ነው፡፡ ይህም ከሃገር አቀፍ ድርሻው 20% ሲሆን ከአለን እምቅ ሃብት አንፃር ሲታይ አነስተኛ ነው፡፡ የክልሉ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት ይህንን ሃብት በተገቢው መልኩ አልምቶ የማርና የሰም ምርትን በጥራትና በብዛት ለማምረት ንብ አናቢውን በስልጠና፣ ዘመናዊ የማነቢያ ግብዓቶችን በማቅረብና የድጋፍና ክትትል ስራ የመስራት ስራዎች እየተሰሩ ይገኛል፡፡ በዚህም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዘርፉ አበረታች ውጤቶች መመዝገብ ጀምረዋል፡፡

 

ዜና  

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ክልላዊ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት በ28/07/2014 ዓ.ም በባህርዳር ከተማ የንቅናቄ መድረክ አካሄደ፡፡ በንቅናቄ መድረኩ የፊደራል የስራ ኃላፊዎች፣ የክልል ቢሮ ኃላፊዎችና ም/ኃላፊዎች፣ ዩኒቨረስቲዎች፣ የምርምር ተቋማት እና የዞንና ወረዳ የዘርፍ ኃላፊዎችና ቡድን መሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

መድረኩን አስመልክቶ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ኃይለማሪያም ከፍያለው ሲሆን ሀላፊው በመልዕክታቸው ክልሉ ሰፊ የሆነ እንስሳት ሀብት ክምችት ያለው መሆኑን ገልጸው ይህን ሀብት ለማልማት በየደረጃው ያለው የዘርፍ አመራርና ሙያተኞች ትኩረት ሰጥቶ መስራት አለበት እንደ ግብርና ቢሮም ይህን ዘርፍ በል ሁኔታ ለመደገፍ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን ብለዋል፡፡

 

ዜና  

የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ጥበቃ ዙሪያ ከሚመለከታቸው አጋር ተቋማት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፡፡

በመድረኩም ከዞን እና ከወረዳ ለተውጣጡ የአካባቢና ማህበረሰብ ጥበቃ ባለሙያዎች፣ የወረዳ እንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪና ባለሙያዎች እንዲሁም የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የሰራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ከጥር 05/2014 ዓም በእንጀባራ ከተማ ተካሄደ፡፡ የመወያያ ጽሁፎች የኘሮጀክቱ የአካባቢና ማህበረሰብ ደህንነት ባለሙያ በሆኑ በአቶ ሀሰን ሙሀባው ሰፋ ያለ የመወያያ ጽሁፎች አቅርበዋል፡፡

 

ዜና 

አሸባሪው ህውሓት በኮምቦልቻ ዶሮ ሃብት ልማት ኢንተርፕራይዝ ላይ ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሷል

KOMBOLCHA POLITERY (9)አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ በቆየባቸው ጊዜያት የኮምቦልቻ ዶሮ ሃብት ልማት ኢንተርፕራይዝን ዘርፏል ንብረቶችን አውድሟል በተሰራው ጊዜያዊ ግምትም ከ67 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረቶች ወድመዋል ፡፡

ü  ለዶሮ እርባታ አገልግሎት የሚውሉ ከ15067 በላይ የእርባታ ዶሮዎች ታርደው ተበልቷዋል

ü  ለእርባታ አገልግሎት የሚውል ከ100ሽህ በላይ የዶሮ እንቁላል ተበልቷል መብላት ያልቻሉትን አውድመውታል

ü  ከ 12000 በላይ የእርቢ እጫጭቶችን ገሏል

ü  1 ትልቅ ጀነሬተር እና 2 ትራክተሮችን አውድሟል

 

ዜና  

በኮምቦልቻ ከተማ የሚገኘው የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘረፋና ወድመት ደርሶበታል፡፡

KOBOLCHA HEALTHY (4)አሸባሪው የህወሓት ቡድን በደቡብ ወሎ ዞን በቆየባቸው ጊዜያት የኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ ዘርፏል ፣ ንብረቶችን አውድሟል

በምስራቅ አማራ ላሉ ወረዳዎች የእንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ስራዎችን ይጠቀምባቸው የነበሩ ንብረቶችን ዘርፈዋል ፣ አውደመዋል

የቢሮ መስኮትና በሮች ተሰባብረዋል ፣ ኮምፒውተሮች እና ማይክሮስኮፖች ወድመዋል ፣ የተለያዩ የእንስሳት መድሐኒቶች እና መሳሪያዎች ተዘርፈዋል መውሰድ ያልቻሉትን አውደመውታል፡፡

ዜና  

በሰሜን ሽዋ ዞን የሚገኘው የአመድ ጉያ በግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ዘረፋና ወድመት ደርሶበታል፡፡

AMEDEGUYA SHEEP (1)አሸባሪው የህወሓት ቡድን በሰሜን ሽዋ ዞን በቆየባቸው ጊዜያት የአመድ ጉያ በግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከልን ዘርፏል ፣ ንብረቶችን አውድሟል

አሸባሪው ቡድን በዞኑ በቆየባቸው ጊዜ ካወደማቸውና ከዘረፋቸው ተቋማት መካከል አንዱ የአመድ ጉያ በግ ብዜትና ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ነው፡፡ ለዝርያ ማሻሻያ የሚውሉ በጎችን አርደው በልተዋል ፣ የበጎች መጠለያና ቢሮዎችን አቃጥለዋል ፣ ኮምፒውተሮች ፣ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች እና የበጎች መኖ ጨምሮ በርከት ያሉ ለማዕከሉ አገልግሎት የሚውሉ ንብረቶች በአሸባሪው ቡድን ተዘርፈዋል ፣ መውስድ ያልቻሉትን አቃጥለውታል፡፡

 

 

ዜና  

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ከአጋር ተቋማት ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ

እንስሳና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በ2012 እና በ2013 በደረጃ አንድ ከ10 እስከ 25 አርሶ አደሮችንና ወጣቶችን በጋራ ፍላጎት ቡድን በማደራጀት የአመራረት ስረዓትን በማሻሻል ከእጅ ወደ አፍ ሲመረት የነበረዉን ትርፍ ምርት በማምረት ለገበያ ታሳቢ አድርጎ መስራትን ለማለማመድ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ከዚህ ጋር በማያያዝ በፕሮጀክቱ አሰራር መሰረት በደረጃ አንድ ድጋፍ የተደረገላቸውን በጋራ የማምረት ልምዳቸውን ለማዳበርና የገበያ ችግሮቻቸውን ለመፍታት ወደ 31 ህብረት ስራ ማህበራት የማሳደግ ስራ በ2013 ተሰርቷል፡፡ በመሆኑም በ2013 በተሰራው ስራ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት በ2014 ዓ/ም በአዲስ ለማደራጀት የህብረት ስራ ኮሚሽን ተቋምን እና የእንስሳት ጽ/ቤት ተቋም ጋር የምክክር መድረክ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡

 

 

ዜና  

አማራ ክልል በተመረጡ አምስት ወረዳዎች የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ ተሰጠ፡፡

የአማራ ክልል እንስሳትና አሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የዝርያ ማሻሻል ስራን በክልሉ ተደራሽና ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ እንስት ጥጃ ብቻ የሚያስወልድ ሴክሲድ ሴመን የተባለውን አዲስ ቴክኖሎጅ በተመረጡ አምስት ወረዳዎች አስጀመረ፡፡ ሴክሲድ ሴመን ማለት በሠው ሠራሽ ማዳቀል ዘዴ እንስት ጥጃን ከ80-90% ማስገኘት የሚችል አባላዘር ማለት ነው ፡፡ ሴክሲድ ሴመን ከመደበኛ አባላዘር የሚለየው በአስተማማኝ ደረጃ ከ80-90% ማስወለድ መቻሉ ሲሆን መደበኛ አባላዘር ግን 50% እንስት እና 50% ተባዕት ጥጃ ሊያስገኝ የሚችል አባላዘር ሲሆን ሴክሲድ ሴመን በመጠቀም የዝርያ ማሻሻል ሥራን በማፋጠን በርካታ ቁጥር ያላቸውን እንስት ጥጆች ፤ጊደሮችና ላሞች ማስገኘት መቻሉ ነው፡፡ የሴክሲድ ሴመን አጠቃቀምን ውጤታማ ለማድረግ የሚወስኑ ጉዳዮች ውስጥ የእርባታ ወቅት ፤የወሊድ መጠን ፤የድቀላ አገልግሎት ብዛት ፤የአካባቢው ሁኔታ ፤የእርባታ መንጋ ቁጥር ፤የሚመረት የወተት መጠን መረጃ በማየት ይከናወናል፡፡

 

 

ዜና 

የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ EAAP በተባለ ኘሮጀክት በክልሉ በሚገኙ 6 ወረዳዎች ለ6 ኢንተርኘራይዞችን ለእያንዳንዱ 1.4 ሚሊዮን ብር ደጋፍ ተደረገ ፡፡

ATA 2014 (7)የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሣ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የክልሉን የንብ ሀብት ልማት ለማዘመን እና አናቢውን ተጠቃሚ ለማድረግ በስልጠና፣ በግብዓት አቅርቦትና ድጋፍና ክትትል በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ በተሰሩ ስራዎችም አበረታች ውጤቶች ተመዝገበዋል፡፡ ጽ/ቤቱ የሚሰራቸው ስራዎች በመደገፍ ኘሮጀክቶች ትልቅ ፋይዳ አላቸው፡፡ከነዚህ ኘሮጀክቶች ውስጥ በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ EAAP የተባለ ኘሮጀክት በክልሉ በሚገኙ 6 ወረዳዎች 6 ኢንተርኘራይዞችን ለእያንዳንዱ 1.4 ሚሊዮን ብር በመደገፍ በስልጠና በግብዓት አቅርቦትና መሠረተ ልማቶችን በማሞላት የንብ ሀብት ልማትን ለማዘመን የሚሰራውን ስራ ሲደግፉ ቆይተዋል፡፡ ኘሮጀክቱ የማጠቃለያ ስራ ርክክብ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በ 29/03/2014 በዳንግላ ከተማ የመስክ ጉብኝት እንዲሁም በ 30/03/2014 በባህር ዳር ከተማ ኘሮጀክቱ በቆይታው የሰራቸው ስራዎችና በቀጣይ እንዴት ማስቀጠል እንደሚገባ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡ በምክክር መድረኩ የተገኙ ተጠቃሚዎችና ባለድርሻ አካላትም በቀጣይ ስራውን ለማስቀጠል በሚችሉበት ሁኔታ በስፋት ተወያይተው የጋራ መግባባት በማድረግ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

 

ዜና  

በምክትል ርዕሰ መስተዳደርዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ /ሮ አይናለም ንጉሴ የቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከልን ጎበኙ

 

ዜና

የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ሃይለማርያም ከፍያለው ቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

ዜና

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽቤት ሃላፊ ዶር ጋሻው ሙጨ ቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም እና የመስክ ምልከታ ላይ የሰጡት አስተያየት

ዜና

በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዮት የደብረ ዘይት ግብርና ምርምር ኢንስቲቲዮት የእንስሳት ስነ-ተዋልዶ ከፍተኛ ተመራማሪ አቶ ታምራት ደገፋ በማዕከሉ ተገኝተው የሰጡት አስተያየት

ዜና

ቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል ሃላፊ አቶ ፈንታሁን ዳኛው በማዕከሉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች አስመልክቱ የሰጡት ማብራሪያ

 

ዜና

ቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስጀመሪያ ፕሮግራም አካሄደ ፡፡ 

Chageni 24 03 2014 (17)የአብክመ እንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ጽ/ቤት የሚመለከታቸው የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎች ፣ በክልሉ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲ ተወካዮች ፣ ከምርምር ተቋማት የመጡ የስራ ሃላፊዎች እና ተመራማሪዎች ፣እንስሳት ሃብት ልማት ላይ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች እና የዘርፉ የዞንና የወረዳ የሚመለከታቸው አመራሮች እና ሙያተኞች በተገኙበት በ24/03/2014 ዓ.ም በቻግኒ ዳልጋ ከብት ብዜት እና ጥበቃ ማዕከል የሴክሲድ ሴመን ቴክኖሎጅ የማስተዋወቅ እና ማዕከሉ ከዝርያ ማሻሻል እና መኖ ልማትና ስነ አመጋገብ ከማሻሻል አንጻር የሚሰራቸውን ስራዎች ለተሳታፊዎች የማስጎብኝት ፕሮግራም አካሄደ ፡፡

 

ዜና

የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በእንስሳት ዘርፍ የተሰማሩ የኒዬኖችን በከፍተኛ ደረጃ ድጋፍ ለማድረግ የተዘጋጀ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ

LFSDP Level3 (10)የእንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልላችን በ15 ወረዳዎች በእንስሳት ዘርፍ በ4 እሴት ሰንሰለቶች (ወተት፣ ቀይ ስጋ፣ ዓሳ እና ዶሮ) ላይ ተመሳሳይ ምርት የሚያርቱ አ/አደሮችንና ወጣቶችን በጋራ ፍላጎት ቡድን በማደራጀት 140000 ብር፣ በደረጃ ሁለት በጋራ ፍላጎት ተደራጅተው ትርፍ ምርት በማምረት ላይ የሚገኙትን ወደ ህብረት ስራ ማህበር በማሳደግ 1.3 ሚሊዬን ብር እና በከፍተኛ ደረጃ የማቀነባበር ስራ ላይ ለተሰማሩ ዩኒየኖችና ለተሻሻሉ ማህበራት 8.5 ሚሊዬን ብር በመሰረተ ልማት፣ በቁሳቁስ፣ በግብዓትና ስልጠና ድጋፍ በማድረግ የምርትና ምርታማነት በማሳደግ ድጋፍ እያደረገ ይኛል፡፡

 

ዜና 

የተሻሻለ የቤተሰብ ደሮ እርባታ የሙከራ ትግበራ የሚተገበርባቸዉ ሞዴል መንደሮች በተመለከተ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሄደ

ATA Poulitery (10)የፌደራል ግብርና ሚኒስቴር በአገር አቀፍ ደረጃ የተሻሻለ የቤተሰብ ደሮ እርባታ የሙከራ ትግበራ ለሚካሄድባቸዉ ወረዳዎች እና የተመረጡ ሞዴል መንደሮች በተመለከተ የሚመለከታቸዉ አጋር አካላት በተገኙነበት ግንቦት 25/2013 በባህርዳር ከተማ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ አካሄደ፡፡

በመድረኩ በግብርና ሚኒስቴር የደሮ እርባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኑት ወ/ሮ ጽጌረዳ ፍሬዉ የሙከራ ፕሮጀክቱን አስመልክቶ መነሻ የመወያያ ጽሁፍ አቅርበዋል፡፡ በቀረበዉ ጽሁፍ ፕሮጀክቱ እንደ ሀገር በ27 ወረዳዎች በአማራ ክልል ደግሞ በ7 ወረዳዎችና 35 ሞዴል መንደሮች ፣ በአንድ ሞዴል መንደር 60 ተሳታፊዎች( ተጠቃሚዎች) ያሉት ሆኖ በእያንዳንዱ ወረዳ 1 መኖ ማቀነባበሪያ እና 2 የ 1 ቀን የኮይኮይ ደሮ ዝርያ ጫጩት አሳዳጊዎች ተደራጅተዉ ወደ ስራ የሚገቡ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ሀላፊዋ አክለዉም ለዚህ ፓይለት ፕሮጀክት ማስፈጸሚ የሚሆን እንደ ሀገር 187 ሚሊዮን ብር የተመደበ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህ ዉስጥ ከፍተኛዉ በጀት ለመሰረተ ልማት እና ለግብአት አቅርቦት ሚዉል መሆኑን ገልጸዉ ቀሪዉ ብር ለተደራጁ ወጣቶችና ሴቶች በብድር መልክ ቀርቦ ለደሮ እና ለመኖ ግዥ አገልግሎት ሚዉል መሆኑን አሳዉቀዋል፡፡

በመድረኩ የተገኙ ተሳታፊዎችም በቀረበዉ የመወያያ ጽሁፍ ላይ ሰፊ ዉይይት ካደረጉ በኋላ ፕሮጀክቱ በቀጣይ 3 አመታት ለሚተገብራቸዉ ስራዎች ስኬታማነት የበኩላቸዉን ሀላፊነት እንደሚወጡ ገልጸዋል፡፡ የምክክር መድረኩም በዚሁ ተጠናቋል፡፡ 

ዜና   

የቻግኒ የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያና ጥበቃ ማዕከል የ10 ሚሊዮን ብራ ድጋፍ ተደረገለት፡፡ 

chagini recerh center (23)የኢፊድሪ ግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ፣ ፣የብሄራዊ ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስራት ቴራ እንዲሁም ከምርምር ፣ ከATA ፣ከLFSDP ፕሮጀክት የመጡ የስራ ሃላፊዎች በ24/09/2013 ዓ.ም ቻግኒ የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻያና ጥበቃ ማዕከል የስራ እንቅስቃሴ በመስክ እና በቢሮ ደረጃ ጎበኙ፡፡

 

ጎብኝዎች በመስክና በቢሮ ደረጃ ከቀረበው ሪፖርት ተነስተው ማዕከሉ ወደ ተሻለ የስራ ደረጃ ሊያሳድጉት በሚችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ወይይት ተደርጓል ፡፡

 

ውይይቱን የመሩት ክቡር ሚኒስትር ድኤታው ሲሆኑ በውይይቱ ማጠቃለያ ማዕከሉ ከዝርያ ማሻሻል እና ከፎገራ ዳልጋ ከብት ዝርያ ከመጠበቅ አንጻር ያለውን ፋይዳ ገልፀው ፡፡

 

ይሁን እንጅ ማዕከሉ አሁን ያለበት ሁኔታ በብዙ መልኩ የታለመለትን አላማ ከማሳካት አንፃር ሰፊ ውስንነት ያለበት መሆኑን እና በቀጣይ የማዕከሉን የአፈፃፀም ደረጃ በተሻለ ሁኔታ ለማሳደግ በአብክመ እንስሳት ኤጀንሲ በኩል የማዕከሉን ችግሮች ለመፍታት ታቅዶ በቀረበው እቅድ መሰረት ለእቅዱ ማስፈፀሚያ የተጠየቀው 10 ሚሊዮን ብር የተፈቀደ መሆኑን በመግለፅ የተመደበውን ገንዘብ በአግባቡ ስራ ላይ መዋሉን እና በማዕከሉ ያመጠው ለውጥ በቀጣይ እየተገመገመ አስፈላጊው ድጋፎች የሚደረጉ መሆኑን በመግለፅ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ዜና 

የአለም የወተት ቀን በደማቅ ሁኔታ በአገር አቀፍ ደረጃ በአማራ ክልል ተከበረ፡፡

milk day 2013 (16)በአለም ለ21ኛ ጊዜና በኢትዮጵያ ለ5ኛ ጊዜ በፈረንጆች አቆጣጠር በየአመቱ June 1 በሃገራችን ግንቦት 24 የሚከበረው አለም አቀፍ የወተት ቀን “ቀንዎን በአንድ ብርጭቆ ወተት ይጀምሩ” በሚል መሪ ቃል በአማራ ክልል በዳንግላ እና በባህር ዳር ከተማ በመስክ ጉብኝትና በፓናል ውይይት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ፡፡

በበአሉ የኢፊድሪ ግብርና ሚኒስቴር ድኤታ ክቡር ዶ/ር ፍቅሩ ረጋሳ ፣የብሄራዊ ዝርያ ማሻሻያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አስራት ቴራ እና ጥሪ የተደረገለቸው ከክልሎች ፣ ከዩንቨርስቲዎች እና ከምርምር ተቋማት የተገኙ የስራ ሃላፊዎች ፣ ባለሙያዎች እና ተመራማሪዎች ተገኝተዋል፡፡

በመስክ ጉብኝቱ የዳንግላ ወረዳ ዋና ከተማ አስተዳደር ወ/ሮ ንፁህ ሽፈራው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ዋና ሰራ አስኪያጅ አቶ ደበበ አድማሱ የበዓሉን የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ጉብኝቱን አስጀምረዋል ፡፡

በመስክ ጉብኝቱ ሞዴል የሆኑ ሁለት የአርሶ አደር የወተት ላም እርባታ ጣቢያዎች እና ሕይወት የወተት ግብይት ህብረት ስራ ማህበር የስራ እንቅስቃሴ ተጎብኝቷል ፡፡

የመስክ ተሳታፊዎችም በጉብኝቱ ወቅት በአዩት ስራ እጅግ መደሰታቸውን በውይይቱ ወቅት በስፋት አንስተው አስተያየት ሰጥተዋል ፡፡

በመጨረሻም የተሻለ አፈፃፀም ላላቸው 6 የወተት ላም አርቢዎች ከዝገት ነፃ የሆነ 10 ሊትር የሚይዝ የወተት ማጓጓዣ እቃዎች በማበረታቻነት ተበርክቷል ፡፡

የመስክ ጉብኝቱም በዚህ መልኩ ከተጠናቀቀ በኃላ በፓናል ውይይቱ በወተት ሃብት ልማት ላይ የሚያተኩር አለምአቀፋዊ እና አገራዊ ፁሁፎች ቀርበው በተሳታፊው ሰፊ ውይይት ተደርጎ የእለቱ መርሃ ግብር ተጠናቋል፡፡

ዜና 

የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የ3ኛው ሩብ ዓመት የዋና ዋና ስራዎች አፈፃፀም ገመገመ፡፡

LFSDP Third Quarter riport (11)በመድሩኩ የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም በሪፖርት ከመቅረቡ በተጨማሪ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት የሆኑ ሴክተር መ/ቤቶች በሩብ አመት ያከናወናቸውን ስራዎች በሪፖርቱ አቅርበዋል ፡፡ በቀረበው ሪፖርት ቤቱ በስፋት ከተወያየ በኋላ የሚከተሉትን የቀጣይ አቅጣጫዎች በማስቀመጥ የእለቱ ውይይት ተጠናቋል፡፡

 • በሌቭል 1 ደረጃ ያሉ ተጠቃሚዎች ውጤታማ ከማድረግ አንፃር የእንስሳት ሃት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ተቋም ከእርባታ እና ከጤና አንፃር የሚሰሩ ስራዎችን በመለከተ ችግር ፈች ድጋፍ እንዲያደርግ፡፡
 • በንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በኩል ከግብይት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን በተመለከተ በየአካባቢው የሚመረተውን የምርት መጠን ከእንስሳት ሃብት ተቋም መረጃ በመውሰድ የገበያ ትስስር መፍጠር እንዳለበት አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡
 • የማህበራት ማደራጃ ፣አካባቢ ጥበቃ ፣ ቴክኒክና ሙያ እንዲሁም መሬት አስተዳደር ከዚህ በፊት በየተቋማቸው እንዲሰሩ ተለይተው የተሰጡ ስራዎችን በቀጣይ ሩብ አመት አጠናቀው ሰርተው እንዲመጡ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
 • በወረዳ ደረጃ የተገዙ ግብዓቶች ወደ ቀበሌ ስለ መውረዳቸው ፣ የሚገቡ ግብዓቶች በስፔኩ መሰረት ስለመግባታቸው እንዲሁም ወደ ስራ የገቡ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች የተቀመጠውን ስታንዳርድ አግኝተው ወደ ስራ መግባታቸውን በተመለከተ ከኤጀንሲው ኮሜቲ ተቋቁሞ ወደ ታች ወርዶ የማጣራት ስራ እንዲሰራ፡፡
 • በደረጃ 2 ድጋፍ ለሚደረግላቸው ማህበራት ሁሉም ተቋማት በድርጊት መርሃ ግብሩ የተሰጣቸውን ስራ በተቀመጠው ጊዜ እንዲያጠናቅቁ፡፡
 • የማደራጃ ማህበራት 80 የጋራ ፍላጎት ቡድኖችን አባል ማድረጋቸውን እንዲያረጋግጥ፡፡
 • መሬት ሳይኖራቸው በማህበር ደረጃ የተደራጁ ማህበራት ተለይተው በአጭር ጊዜ መሬት የሚያገኙበት ሁኔታ እንዲመቻች ፡፡
 • የፕሮጀክቱ ስራዎች የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኙ ይደረግ፡፡
 • ከግዥ አንፃር የሁሉም ወረዳዎች የግዥ አፈፃፀም ከቀሪ ጊዜያት አንፃር ሲገመገም ያለበት ደረጃ ችግር ያለበት በመሆኑ ጥብቅ ክትትልና ድጋፍ ተደርጎ በቀሪ ጊዜያት እንዲጠናቀቅ ይደረግ የሚሉ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል፡፡

 

 

ዜና  

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሃብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክትና ማህበራት በዶሮ እርባታ፣ በቀይ ስጋ ፣ በወተትና በዓሣ ሃብት ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ማህበራት ውጤታማነትን አስመልክቶ ምክክር አካሂደዋል፡፡

የምክክሩ ዓላማ በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ የተሰማሩ ማህበራት ስራቸውን በእቅድ እንዲመሩ ማስቻል፤ ከሸማቹ የገበያ ትስስር መፍጠር ፣ የተሻለ ጥራት ያለው ምርት እንዲያመርቱ ማስቻልና መደገፍ እንደሆነ የአማራ ክልል የኀብረት ስራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ኃላፊ ኃይለልዑል ተስፋ ተናግረዋል፡፡

“አምራችና ሸማች ጥብቅ ትስስር መፍጠራቸው ለሀገር እድገት መሰረት ነው” ያሉት ኃላፊው ሁለቱ አካላት ትስስር የማይፈጥሩ ከሆነ ተጠቃሚ የሚሆነው ሕገ ወጥ ደላላው ብቻ ነው ብለዋል፡፡

ሸማቹ የሚፈልገው የምርት ጥራት ፣አይነት፣ብዛትና ጊዜን በአግባቡ መረዳት አምራቹን ስኬታማ ያደርጋል፤ ለዚህም በየወቅቱ መነጋገር እንደሚያስፈልግ አቶ ኃይለልዑል አስገንዝበዋል፡፡

የወተት ልማት ምርት ሸማቿ ወይዘሪት እልልታ ካሳ ውይይቱ ገዢና ሻጭን የበለጠ ሊያቀራርብ ይችላል ብላለች፡፡ በተለይ ገዢው ከየትኛው ሸማች መግዛት እንዳለበት አማራጮች እንዲኖሩት ያስችላልም ነው ያለችው፡፡

አቶ ዘየነው ዓለሙ የአውራምባ ማህበረሰብ የገበሬዎችና እደ ጥበባት ሁለገብ ህብረት ስራ ማህበራት ስራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ ማህበራት ውጤታማ እንዲሆኑ የገበያ ትስስሩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ዘርፍ ኘሮጀክት በክልሉ በእንስሳት ሃብት ልማት ለተሰማሩ ማህበራት ድጋፍ ከሚያደርጉ ኘሮጀክቶች ውስጥ አንዱ መሆኑን የአማራ ክልል እንስባት ሃብት ልማት ኤጀንሲ ማስፊፊያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዳዊት ገዳሙ አስረድተዋል፡፡

ኘሮጀክቱ በክልሉ በ15 ወረዳዎች የሚንቀሳቀስ ሲሆን በዶሮ ሃብት ልማት፣ በቀይ ስጋ፣ በወተትና በዓሣ ሃብት ልማት ላይ ተደራጅተው ለሚንቀሳቀሱ ማህበራት ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ አቶ ዳዊት ተናግረዋል፡፡ ማህበራቱ በተሰማሩበት የስራ መስክ ሁሉ ኤጀንሲው የቴክኒክና ሙያ ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡

የተደራጁ ማህበራት ለማጠናከር የእንስሳት ዝርያ ማሻሻያ ማድረግ ፣ የተሻለ መኖን ማቅረብና ጤንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን መስራት ኤጀንሲው ከኘሮጀክቶች ጋር የሚያከናውነው ተግባራት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ኘሮጀክቱ በ2ዐ12 ዓ.ም.በአማራ ክልል በ15 ወረዳዎች 1ሺ 35ዐ የጋራ ፍላጐት ቡድን አቅፎ ነበር ስራውን የጀመረው፤ ከነዚህ ውስጥ የተሻለ ፈአፃፀም ያሳዩ 31 ቡድኖች ወደ ደረጃ ሁለት ማህበር ተሸጋጋረዋል ብለዋል፡፡ ወደ ደረጃ ሁለት ለተሻጋገሩ ማህበራት ለእያንዳንዳቸው 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ እንደሚደረግላቸውም አቶ ዳዊት አስረድተዋል፡፡

በስራ አፈፃፀማቸው ለተመረጡ ማህበራት ድጋፍ ማድረግ ብቻ ሳይሆን ከሸማቹ ጋርም በማቀራረብ የገበያ ትስስር በሚፈጠርባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር መደረጉን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ጠቅሰዋል፡፡

በእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ከ2ዐ12 ዓ/ም ጀምሮ በውስን ሃብትና መሬት በርካታ የክልሉ ዜጐችን የስራ እድል ተጠቃሚ ማድረግ እንደተቻለም አቶ ዳዊት አመልክተዋል፡፡

በዚህ ኘሮጀክት ብቻ ከ2ዐ ሽህ በላይ ዜጐች የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ነው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ያብራሩት፡፡

ዜና

ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች (ፒፒአር) በሽታ ምንነት ፤ መተላለፊያና መከላከያ መንገዶች እንዲሁም በሽታውን ለመከላከል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ የምዕራብ አማራ ክፍል ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ ቁጥጥር አሰተባባሪ ከአቶ ኤሌያስ ደምሴ ጋር የተደረገ ቆይታ

ዜና

/ዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናትና ምርምር ላብራቶሪ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እስመልክቶ ከላብራቶሪ ስራ አስኪያጅ ከአቶ ወንደሰን ቁምላቸው ጋር ያደረግነው ቆይታ

ዜና

በሰሜን ጎንደር ዞን አዲ-አርቃ ወረዳ በሳንቅ ብስኒት ቀበሌ ደስታ መሰል የበጎችና ፍየሎች በሽታ (ፒፒአር) የክትባት አገልግሎት ሲሰጥ

 

ዜና

በአማራ ክልል የተሻለ የእንስሳት ማድለብ ስራ እንቅስቃሴ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን እና ባለሃብቶችን ምርጥ ተሞክሮዎችን ለሌሎች ለማሳየት የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር በመተባበር በኤስዲአይ ቮካ ፊድ ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጅቶ የቀረበ፡፡

ዜና

በአማራ ክልል የተሻለ የዶሮ ሃብት ልማት ስራ እንቅስቃሴ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን እና ባለሃብቶችን ምርጥ ተሞክሮዎችን ለሌሎች ለማሳየት የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር በመተባበር በኤስዲአይ ቮካ ፊድ ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጅቶ የቀረበ፡፡

ዜና

በአማራ ክልል የተሻለ የወተት ሃብት ልማት ስራ እንቅስቃሴ እየሰሩ ያሉ ወጣቶችን፤ባለሃብቶችንና አርሶ አደሮችን ምርጥ ተሞክሮዎችን ለሌሎች ለማሳየት የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ጋር በመተባበር በኤስዲአይ ቮካ ፊድ ፕሮጀክት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ተዘጋጅቶ የቀረበ፡፡

 

ዜና

በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ በዱርቤቴ ከተማ የሚገኘው ፍቃዱ ዘርፋለምና ጓደኞቻቸው የወተት ላም እርባታ ኢንተርፕራይዝ

ፍቃዱ ዘርፋለምና ጓደኞቻቸው የወተት ላም እርባታ ኢንተርፕራይዝ በምዕራብ ጎጃም ዞን ደቡብ አቸፈር ወረዳ ድርቤቴ ከተማ 5 አባላት በመያዝ በ2010 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን አሁን ላይ ማህበሩ 11 የተሻሻሉ የወተት ላሞችን በመያዝና የተሻሻለ የእንስሳት መኖ በማልማት አርአያነት ያለው ስራ እየሰሩ ይገኛል

 

 

 

 

 

 

 

ዜና

በአማራ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ፕሮጀክት የደስታ መሰል በሽታ ግብረ ሃይል የ8 ወር አፈጻጸም በግብረ ሃይሉ ተገመገም

በአማራ ክልል የእንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ፕሮጀክት የደስታ መሰል በሽታ ግብረ ሃይል በባህርዳር እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናት ምርመራ ላብራቶሪ እና በየኮምቦልቻ እንስሳት በሽታ ቅኝት ጥናት ምርመራ ላብራቶሪ በ8 ወር የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸም በግብረ ሃይሉ ተገመገም 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ዜና

የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የተጠሪ ማዕከላትን የ8 ወር አፈፃፀም በ 26/06/2013 በባህር ዳር ከተማ ገመገመ፡፡

የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የተጠሪ ማዕከላትን የ8 ወር አፈፃፀም በ 26/06/2013 በባህር ዳር ከተማ ገመገመ፡፡ ሁሉም ማዕከላት የ8 ወር አፈፃፀማቸወን በሪፖርቱ አቅርበዋል፡፡ ሪፖርቱ ከቀረበ በኃላም በቀረበው ሪፖርት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ከተደረገ በኃላ በኤጀንሲው ዋና ስራ አስኪያጅ በኩል የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ተለይቶ ወይይቱ ተጠናቋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

ዜና

የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት በ 20/06/2013 ዓም በእንጅባራ ከተማ የ6 ወሩን የኘሮጀክት አፈፃፀም በቴክኒክ ኮሚቴው ገመገመ፡፡

የእንስሳት እና ዓሣ ሃብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት በ 20/06/2013 ዓም በእንጅባራ ከተማ የ6 ወሩን የኘሮጀክት አፈፃፀም በቴክኒክ ኮሚቴው ገመገመ፡፡ የኘሮክቱ የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም በኘሮጀክቱ በኩል ከቀረበ በኃላ ከቤቱ በቀረበው የአፈፃፀም ሪፖርት ላይ በስፋት ተወያያቶ የሚከተሉትን የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀምጧል፡፡ ነባር የጋራ ፍላጐት ቡድናትን ያለበትን ሁኔታ ለይቶ የማወቅና የማጠናከር ስራ ይሰራ ለዚህም መስፈርት የተዘጋጀ በደረጃ ለይቶ የተሻለ አፈፃፀም ባላቸው የጋራ ፍላጎት ቡድኖች ሌሎች እንዲማሩ ፊልድ

      የህብረት ስራ ማደራጃ ኤጀንሲ በየወረዳው ያሉ የህብረት ስራ ማህበራትን የማጠናከር ስራ መሰራት አለበት

      በ 15 ወረዳ የጋራ ፍላጎት ቡድኖች የተመሠረቱ ተዋፅኦችን በኘሮጀክቱ የገቢያ እሴት ሰንሰለት እና በንግድ ቢሮ በኩል ስራዎች ተሰርተው የመፍትሄ አቅጣጫዎች ይቀመጡ፡፡

      ከመሬት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን መሬት አስተዳደር ወስኖ መፍታት አለበት፡፡ ለዚህም በቢሮዉ የተወከሉ አካላት በቅርበት መከታተል አለባቸው፡፡

      ቴክኒክና ሙያ ነባሮችም ሆነ አዲሶችን የጋራ ፍላጎት ቡድኖች በአመለካከት የማብቃት ስራ መስራት አለበት

      ግዥን በተመለከተ በየእለቱ እያንዳንዱ ወረዳ ያለበትን ሁኔታ መረጃ እየተያዘ ለፌስ ብክ ይሰጣል

      በክልል ደረጃ የመድሃኒት ግዥ በትኩረት ተይዞ ይሰራል አፈፃፀሙም በየጊዜወ ሪፖርት ይቀርባል

      መኖ ሳይገባ ዶሮ እንዳይገባ ጥንቃቄ ይደረግ

ዜና

ከአሁን በፊት በቆሎ እና ዳጉሳ ይዘሩበት የነበረውን ማሳቸውን የተሻሻለ የእንስሳት መኖ በመዝራት በወተት ሃብት ልማት ስራ ተጠቃሚ የሆኑት አርሶ አደር ተሾመ መለስ

 በምዕራብ ጎጃም ዞን በደቡብ አቸፈር ወረዳ አብችክሊ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አርሶ አደር ተሾመ መለስ ከአሁን በፊት በቆሎና ዳጉሳ ይዘሩት የነበረውን ማሳቸውን እንዲሁም ከግለሰቦች የማሳ መሬቶችን በመከራየት በ1.5 ሄክታር የተሻሻለ የእንስሳት መኖ በመዝራት በ2008ዓ.ም በወተት ሃብት ልማት ስራ የገቡ ሲሆን አርሶ አደሩ አሁን ላይ 7 የወተት ላሞች እና 5 ጥጆች ያሎቸው ሲሆን በቀን ከ52 ሊትር በላይ ወተት እንደሚያገኙ ገልጸውልናል ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 ዜና

የፌደራል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ እና የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ በተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ዙሪያ የሰጡት አስተያየት ፡፡

ዜና

የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ ከጥር 17-21/2013 ዓ.ም በእንጅባራ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና ሲያካሄድ፡፡በተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ላይ ተካፋይ የነበሩት ከአማራ ክልል ህብረት ስራ ኤጀንሲ እና ከአማራ ክልል ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ የመጡ ባለሙያዎች እና የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የወረዳ አስተባባሪዎች በተሰጠው የአሰልጣኞች ስልጠና ዙሪያ የሰጡት አስተያየት

 

 

ዜና

የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ የአሰልጣኞች ስልጠና ሲያካሄድ፡፡

የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ፕሮክቱ በሚሰራባቸው 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት በፕሮጀክቱ በደረጃ 2 እና 3 ተጠቃሚ ለማድረግ  

1 በገቨርናንስና ንዑስ ፕሮጀክት አዘገጃጀት

2 በአካባቢ እና ማህበራዊ ደህንነት ጉዳይ

3 በግብይት ሰንሰለት ዙሪያ ከጥር 17-21/2013 በእንጅባራ ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና አካሄደ፡፡በስልጠናው ተሳታፊ የሆኑ ከተለያዩ ተቋማት የመጡ ባለሙያዎች እንደገለጹት እንዲህ አይነት ስልጠና ከዚህ በፊት አለማግኘታቸውን ጠቅሰው ስልጠናው ለቀጣይ ስራቸው ትልቅ አቅም እንደሚሆናቸው በመጠቆም  ወደ የመጡበት ወረዳ ሲመለሱ ስልጠናውን ለሚመለከታቸው አካላት እንደሚያወርዱ ገልጸዋል ፡፡ መድረኩን የመሩት የኤጀንሲው ም/ስራ አስኪያጆች እና የፌደራል የፕሮጀክቱ አስተባባሪ በኩላቸው ፕሮጀክቱ የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፉን ለማዘመን በሚሰሩ ስራዎች ትልቅ ድርሻ ያለው መሆኑን ገልጸው በየደረጃው ያሉ የዘርፉ ሙያተኞች እና የሚመለከታቸው አጋር አካላት የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ በማሳሰብ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ዜና

በክልሉ ከሚገኙ በርካታ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዞች አላውሃ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዝ አንዱ ነው፡፡

የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የወተት ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ከሚሰራቸው በርካታ ስራዎች ውስጥ ወጣቶች በዘርፉ በስፋት ተደራጀተው እንዲገቡ እና የተሻለ አሰራር ተከትለው እንዲሰሩ ድጋፍ ማድረግ ነው፡፡ በክልሉ ከሚገኙ በርካታ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዞች አላውሃ የወተት ላም እርባታ ኢንተርኘራይዝ አንዱ ነው፡፡ኢንተርኘራይዙ የሚገኝው በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ላስታ ገራዶ 04 ቀበሌ ሲሆን ስራ የጀመረው በ2007 ዓም በ 5 ላሞች ነው፡፡ ኢንተርኘራይዙ አሁን ላይ 17 ላሞችና 7 ጊደሮች፣ 10 ጥጆች እና 1 ኮርማ ያለው ሲሆን አሁን ከሚታለቡ ላሞች ውስጥ በቀን እስከ 70 ሊትር ወተት ለገቢያ እንደሚያቀርቡ ጠቁመዋል፡፡ የኢንተርኘራይዙ አባል አቶ ያሴን ሸጋው እንደገለፁልን አባላቱ በአብዛኛው ከአረብ አገር ተመላሽ መሆናቸውን ገለፀው በዚህ የስራ መስክ መሰማራታቸው ከራሳቸው አልፎ ከ 4 ያላነሱ ስራ አጥ ወጣቶች የስራ እድል መፍጠራቸውን ገልፀዋል፡፡ ግለሰቡ አክለውም አሁን የስራው እንቅፋት የሆነባቸው የውሃ እጥረት ቢፈታ በቀጣይ የተሻለ ስራ ሰርተው ራሳቸውን እና የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡ እኛም የሚመለከታችሁ አካላት ተገቢውን ድጋፍ ብታደርጉላቸው የሚል መልክታችን እናሳተላልፋለን፡፡

 

ዜና

በሰሜን ውሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ሀራ 01 ቀበሌ ከአረብ ሃገር ተመልሰው በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተደራጁት ኢብራሂም ሁሴን እና ጓደኖቹ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊ ኢንተርኘራይ በ2009 ዓም 1000 ጫጩቶችን በመያዝ ስራ የጀመሩ ሲሆን አሁን ላይ በዓመት ከ20,000 ያላነሱ ጫጩቶችን በማሳደግ ለተጠቃሚዎች ያቀርባሉ፡፡

የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ ህ/ሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ከስራቸው ስራዎች አንዱ የተሻለ የእንቁላል እና የስጋ መጠን የሚሰጡ የዶሮ ዝርያዎችን በግብዓት አቅራቢዎች አማካኝነት ለህብረተሰብ እንዲዳረስ እና ሳይንሳዊ አሰራሩን ተከተለው እንዲሰሩ በማድረግ ተጠቃሚነታቸውን ማረጋገጥ ነው፡፡ ኢብራሂም ሁሴን እና ጓደኖቹ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊ ኢንተርኘራይዝ የሚገኝው በሰሜን ውሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ሀራ 01 ቀበሌ ሲሆን ኢንተርኘራይዙ በ2009 ዓም 1000 ጫጩቶችን በማሳደግ ስራ የጀመረ ሲሆን አሁን ላይ በአመት ከ 20.000 ያላነሱ ጫጩቶችን በማሳደግ ለተጠቃሚዎች ያቀርባል፡፡ የኢንተርኘራይዙ አባል አቶ ኢብራሂም ሁሴን እንደገለፁልን ከዚህ በፊት በአረብ አገር ይኖሩ እንደነበር ገልፀውልናል፡፡ ወደ ሀገር ቤት ከተመለሱ በኃላ በባለሙያዎች በተደረገላቸው ድጋፍ በዚህ ዘርፍ በመሰማራት ራሳቸውን ከመጥቀም ባለፈ ለ 3 ሰው የሰራ ዕድል መፍጠራቸውን ጠቁመውናል፡፡ ግለሰቡ አክለውም ይህ ዘርፍ እጅግ አዋጭ መሆኑን ጠቅሰው በርካታ ስራ አጥ ወጣቶች በዚህ ዘርፍ ቢሰማሩ ከራሳቸው ባለፈ አገርን ተጠቃሚ ያደርገሉ ብለዋል፡፡ እኛም በስፍራው ተገኝተን ያየነው ስራ የሚበረታታ በመሆኑ ይህን ተሞክሮ ሌሎች ወስደው ተግባራዊ ቢያደርጉት ተጠቃሚ ይሆናሉ እንላለን፡፡

 

 

ዜና

በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ከአረብ ሃገር ተመልሳ በወተት ሃብት ልማት ስራ የተሰማራችው ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን በ2010 ዓ.ም 4 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ ወደ ስራ የገባች ሲሆን አሁን ላይ በቀን ከ650 ብር ያላነሰ ከወተት ሽያጭ ታገኛለች፡፡

የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ በውስን ካፓታል እና መሬት ለወጣቶችና ለሴቶች የስራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር ትልቅ አቅም ያለው ዘርፍ ነው፡፡ በዘርፉ በርካታ ወጣቶች እና ሴቶች ወደ ስራ በመግባት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ወጣቶችና ሴቶች መካከለ ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን አንዳ ናት፡፡ ወ/ሪት ፋጡማ ሁሴን ነዋሪነቷ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ ሲሆን ግለሰቧ የወተት ሀብት ልማት ስራ የጀመረችው በ2010 ዓም ነው፡፡ አሁን ላይ 4 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ እና ባላት ውስን ቦታ የተሻሻሉ የመኖ ልማቶችን በማልማትና እንስሳቶችን በመመገብ ተጠቃሚ መሆን ችላለች፡፡ ግለሰቧ እንደገለፀችው በቀን ከ650 ብር ያላነሰ ከወተት ሽያጭ እንደምታገኝ ገልፃ ከዚህ በላይ የተሻሻለ ስራ ለመስራት የቦታ ጥበት እና የብድር አቅርቦት ችግር እንዳለባት ጠቁማናለች፡፡ እኛም የሚመለከታቸው አካላት የግለሰቧን ችግር ተረድታችሁ የተሻለ ስራ እንድትሰራ አግዟት የሚለው መልክታችን ነው፡፡

ዜና

 

በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ በወተት ሃብት ልማት ስራ የተሰማራው ወጣት ናስር ሙህመድ 9 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ በስፋት ወደ ስራው ገብቶል

የእንስሳት ሃብት ልማት ዘርፍ በውስን ካፓታል እና መሬት ለወጣቶችና የስራ ዕድል ከመፍጠር አንፃር ትልቅ አቅም ያለው ዘርፍ ነው፡፡ በዘርፉ በርካታ ወጣቶች ወደ ስራ በመግባት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ከነዚህ ወጣቶች መካከለ ናስር ሙህመድ አንዱ ነው ወጣት ናስር ሙህመድ ነዋሪነቱ በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ ነዋሪ ሲሆን ግለሰቡ የወተት ሀብት ልማት ስራ የጀመረችው በ2010 ዓም ነው፡፡ አሁን ላይ 9 የተሻሻለ ዝርያ ያላቸው የወተት ላሞችን በመያዝ በስፋት ወደ ስራው በመግባት በመርሳ ከተማ የወተት ተዋፅኦዎችን ለአካባቢው ማህበረሰብ እያቀረበ ይገኛል በዚህን ተጠቃሚ መሆኑን ገልጾልናል፡፡

 

ዜና

በአዊ ብ/አ/ዞን በእንጅባራ ከተማ በወተት ሃብት ልማት ሰራ የተሰማሩት አለም የወተት ላም እርባታ 18 ላሞች፣ ጊደሮች እና ጥጆች በመያዝ በዘርፉ ጥሩ እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛል፡፡

በአማራ ክልል ከሚገኝ በርካታ የወተት ላም እርባታ ድርጅቶች አንዱ አለም የወተት ላም እርባታ ነው፡፡ የወተት ላም እርባታው የሚገኝው በአዊ ብ/አ/ዞን በእንጅባራ ከተማ ነው፡፡ የወተት ላም እርባታው በ 2003 ዓ.ም እንደጀመረ የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ የሽወርቅ ምህረት ገልፀውልናል፡፡የድርጅቱ ባለቤት የሆኑት ወ/ሮ የሽወርቅ ምህረት አሁን ላይ በእርባታ ድርጅቱ ቁጥራቸው ከ 18 ያላነሱ ላሞች፣ ጊደሮች እና ጥጆች እንደሚገኙ ጠቁመው በቀን ከ 80 ሊትር ያላነሰ ወተት እንደሚያገኙና በዚህም ሂውታቸውን በተሻለ መልኩ እየመሩ እንደሆነ ገልፃዋል፡፡ግለሰቧ አክለውም ከቦታ ጋር ተያይዞ ያሉባቸው ችግሮች በመንግስት በኩል ቢፈቱ ከዚህ የተሻለ ስራ በመስራት ራሳቸውን እና ህብረተሰቡን መጥቀም እንደሚችሉ ገልፀዋል፡፡ እኛም ከቦታው ተገኝተን ያየነው ስራ የሚያበረታታ በመሆኑ የአካባቢው አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ  እንዲደረግላቸው መልክታቸውን እናስተላልፋለን፡፡

ዜና

በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተሰማሩ ወጣቶች የስራ እንቅስቃሲ

የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የእንስሳትን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ትኩረት ሰንቶ ከሚሰራቸው ስራዎች አንዱ የተሻለ የእንቁላል ምርትና ስጋ መስጠት የሚችሉ የውጭ ደም ያላቸው የዶሮ ዝርያዎች ከ 1 ቀን ጫጩት አቅራቢ ካምፓኒዎች አሳዳጊዎች እየወሰዱ እንሚያሳደጉ አስፈላጊ ሙያዊ እገዛዎችን በቅድመ ዝግጅትና በተግባር ምዕራፍ እያደረገ ይገኛል፡፡ ኤጀንሲው በ2012 በጀት አመት በ 1 ቀን ጫጩት ማሳደግ ስራ በሰራ ላይ ሆነው ድጋፍ የተደረገላቸው በኢንተርኘራይዝ የተደራጅ አሳዳጊዎች ቁጥር 2250 ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 754 ሴቶች ናቸው፡፡ ወጣት ብስራት እንዳላማው እና መዝገቡ የተባሉ የ1 ቀን ጫጩት አሳዳጊዎች ነዋሪነታቸው በደቡብ ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ከተማ ሲሆኑ ወደ ስራ የገቡት በ 2012 ዓም እና በ2010 ዓ.ም 500 እና 300 ጫጩቶችን በመያዝ ነው፡፡ አሳዳጊዎቹ አሁን ላይ በቅደም ተከተል 1500 እና 3000 ጫጩቶችን ይዘው በማሳደግ ላይ ያሉ ሲሆን የስራውን አዋጭነት በተመለከተ በሰጡት አስተያየት ከዚያ በፊት ምንም አይነት ስራ እንዳልነበራቸው እና ወደዚህ ስራ ከገቡ ጊዜ ጀምሮ የተሻለ ተጠቃሚ መሆናቸውን እና ወደ ፊትም ስራውን ይበልጥ ለማስፋፋት እቅድ እንዳላቸው ገልፀውልናል፡፡ የእነዚህን ወጣቶች አርአያነት በመውድ ሌሎች ወደ ስራ ያልገቡ ወጣቶች በዚህ ዘርፍ ወደ ስራ ቢገቡ ይበልጥ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ እንጠቁማለን፡፡

ዜና

እናትና ልጅ የወተት ላም እርባታ በ2ዐዐ2 ዓ/ምንደር ከተማ በ2 የወተት ላሞች የተጀመረ ሲሆን አሁን ላይ ከ2ዐ በላይ የወተት ላሞች እንዲሁም 37 የሚሆኑ ጊደሮችን በመያዝ በስፋት ወደ ስራ ገብተዋል፡፡

በክልላችን ከሚገኙ ዘመናዊ የወተት ላም እርባታ አንዱ እናትና ልጅ የወተተ ላም እርባታ ነው የወተት ላም እርባታ በ2ዐዐ2 ዓ/ም በንደር ከተማ በ2 የወተት ላሞች የተጀመረ ሲሆን አሁን ላይ ከ2ዐ በላይ የወተት ላሞች እንዲሁም 37 የሚሆኑ ጊደሮችን በመያዝ በስፋት ወደ ስራ ገብተዋል፡፡ የማህበሩ ሊቀመንበር ወ/ሮ ብርሃኔ ተዋበ እንደለፁልን ማህበሩ በቀን ከ15ዐ በላይ ወተት ለተጠቃሚ እንደሚያርቡ ጠቁመው ወተት የሚያቀርቡበት የራሱ የወተት መሸጫ ጣቢያ እንዳለው ገልፀዋል፡፡ ወ/ሮ ብርሃኔ ተዋበ አክለውም ከወተት ሽያጭ በተገኘ ገቢ ዘመናዊ ፎቅ እየገነቡ መሆኑን ጠቅሰው ወደፊት ስራውን የበለጠ ለማስፋት ሃሣብ እንዳላቸው ገልፀል፡፡

 

 

 

ዜና

በእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ኘሮጀክት በዓሣ ሃብት ልማት የተደራጁ ወጣቶች ና በአርሶ አደሮች የዓሳ ኩሪ ጫጩት የመጨመር ስራ ተሰራ

የአማራ ክልል እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ በክልሉ የዓሣ ሃብት ልማትን ለማሣደግ እና ህብረተሰቡን ከዘርፉ ተጠቃሚ ለማድረግ ከባ/ዳር የዓሣ ምርምር ማዕከል የዓሣ ጫጩት በማራባት በእንስሳትና ዓሣ ሃብት ልማት ኘሮጀክት በዓሣ ሃብት ልማት የተደራጁ ወጣቶች ና በአርሶ አደሮች የዓሳ ኩሪ ጫጩት የመጨመር ስራ ተሰራ

 

 

 

 

ክልላዊ የዓሣ ሃብት ልማት መረጃ

 

ክልሉ ለዓሳ ሃብት ልማት አመች የሆነ የአየር ንብረት ያለዉ ሲሆን በዓመት ከ30 ሽህ እሰከ 40 ሽህ ቶን የዓሳ ምርት ለሚረት እንደሚችል መርጃዎች ያሳያሉ ፡፡ በዚህም መሰረት በGTP-1 2007 ዓ/ም መጨረሻ ከነበረበት 18,400 ቶን የዓሳ ምርት በየዓመቱ 15 በመቶ በማሳደግ በGTP-2 መጨረሻ በ2012 ዓ/ም ወደ 37,008 ቶን የዓሳ ምርት ለማድረስ ታቅዶ ወደ ተግባር በመግባት በዘረፉ የነበሩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች አንደሚከተለዉ ቀርበዋል

 

 • የተከዜ የዓሳ ሃብት ልማት ጥቅም ላይ ለማዋል በርካታ ድጋፎች ተደርገዋል ፡፡
  • በክልሉ የዓሳ ጫጩት አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት አንድ የዓሣ ጫጩት ማስፈልፈያና ማበዣ ማዕከል ማቋቋም መቻሉ
  • የዓሳ ማስገር ዝግ ወቅትን ሙሉ ለሙሉ ማስቆም ባይቻልም በየዓመቱ የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች መኖራቸዉ በዚህም በሰዉ ሰራሽ ግድቦች ላይ ማስቆም የተቻለበት ሁኔታ መኖሩ
  • በአዲስ የተገነቡ ሰዉ ሰራሽ ግድቦች ላይ በመለየት በማጥናት እና የዓሳ ጫጩት በመጨመር የዓሣ ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ በተጨማሪ ለበርካታ ወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠር መቻሉ /ርብ ግድብ ፣ቆጋ ግድብ እንዲሁም ገርይ ግድብ …/
  • የዓሳ ግብርናን ከማስፋፋት አኳያ አ/አደሮች ዓሳን ከደሮ እርባታ ፣ከመስኖ ልማትና ከአትክልትና ፍራፍሬ ጋር በማቀናጀት ማልማት መቻላቸዉ/አዊ ፣ምስራቅ ጎጃም ፣ምዕራብ ጎጃምና ሰ/ሸዋ ዞኖች /
  • የደጋ ዓሳ ጫጩት አቅርቦት ችግር ቢኖርም ከአጎራባች ክልል /ከኦሮሚያ/ ጋር በመነጋገር ከ85 ሽህ በላይ የደጋ ዓሣ ጫጩቶች ወደ አ/አደር ኩሬች መሰራጨት መቻላቸዉ/ሰሜን ሸዋ ዞን /
  • LFSDP ፕሮጀክት አማካኝነት የአ/አደር CIGዎችን በማደራጀት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኩሬ ተቆፍሮ የጫጩት ስርጭት ለማከናወን በዝግጅ ላይ መሆናችን
  • በተለያዩ ጊዜያት ከሚመለከታቸዉ የንግድ ፣ህብረት ስራ ማህበራት ፣የፖሊስና የምርምር ተቋማት ጋር በመዉጣት በመስክ በመዉጣት ከወጣውየዓሣማስገርናአዋጅ፣ደንብናመመሪያአኳያ፣የማስገርፈቃድናየብቃትማረጋገጫበመያዝየንግድፈቃድአውጥቶከመስራት እና ከዓሣምርትግብይትናግብዓትጋርበተያያዘያሉበት ደረጃ ፣ከአስጋሪአደረጃጀትአንጻርበግልበኢንተርፕራየዝእናህብረትስራ/ እናነጋዴ/የተደራጁአካላትያሉበትሁኔታናከዚህጋርተያይዞችግሮች በመለየት በርካታ ስረዎች መሰራታቸዉ

 

ሀ.ስልጠና - ለተሳትፎዊ የዓሳ አስተዳደር ኮሚቴዎች ፣ለዓሳ አስጋሪዎች ፣ለመምህራና ተማሪዎች እንዲሁም ለምግብ ቤት ሰራተኞች ለቤተ ክህነት አከላትና ለወረዳ ዓሳ ባለሙያዎች በዓሳ ድህር ምርት አያያዝና አጠቃቃም ፣በዓሳ ምግብ ጠቃሜታና ስልጠና ተሰጥቷል ፡፡

 

ለ. የማስገሪያ መሳሪያ ግብዓት አቅርቦት- 16 የዓሳ ማቀዝቀዣዲፕ ፍሪጅ ፣ጀልባ 28፣ላይፍ ጃኬት 20፣የዓሳ መያዣ ሳጥን 140፣የዉሃ ባልዲዎች 140 ፣የዓሳ ማጠቢያ ሳህን 40 ፣የዓሳ መበለቻ ቢለዋ 140 ፣የመረብ መስሪያ ክር ፣የመረብ መስሪያ መርፊ፣የተለያየ መጠን ያላቸዉ መንጠቆዎች ፣የዓሳ መበለች ጠረጴዛ ፣የዓሳ መመዘኛ ሚዛን እንዲሁም የዓሳ ማጓጓዣ የሞተር ጀልባ ደጋፍ ተደርጓል፡፡

 

. የዓሣ መበለቻና መገበያያ ሸድ ግንባታ /ዝቋላ፣ ሳህላ ሰየምት ፣አበርገሌ/እንዲሁም የሪስቶራንተ ህንፃ ግንባታ/ሰቆጣ ከተማና አበርገሌ /ወረዳዎች ላይ መገንባቱ

 

ሠ. የዓሳ ምርት ገቢያ በተመለከተየተከዜን የዓሣ ምርት ወደ ገበያ ለማድረስ 4 ፍሪጅ የተገጠመላቸው መኪኖች እንዲገዙ በማድረግ ለ4 ወረዳወች ማዳረስ መቻሉ

 

በድክመት

 

 • የወጡ የዓሣ ሀብት ልማና ጥበቃ ሕጎችና ደንቦች ተግባራዊ በማድረግ በኩል በሃይቆች ላይ ዉስንነት መኖር በተለይም የዓሳ ማስገር ፍቃድ አሠጣጥ መመሪያ ተግባራዊ አለመሆን
 • የዓሣ ተረፈ ምርትን ጥቅም ላይ ለማዋል ከዶሮ ሀብት ልማት ኢንተርፕራይዞች /ባለሀብቶች ጋር ተቀናጅቶ አለመስራት
 • ተሳትፎዊ የዓሳ አስተዳደር ኮሚቴዎች በማጠናከር በሙሉ አቅማቸዉ ወደ ስራ እንዲገቡ አለመደረጉ /በተለይም በሃይቆች የኮሚቴዎች መፍረስ መኖር /
 • በክልሉ በአዲስ የተገነቡ ሰዉ ሰራሽ ግድቦች ላይ በመሉ በማጥናት ተስማሚ የዓሳ ዝርያዎችን በመጨመር ለወጣቶች የስራ ዕድል መፍጠሪያ አለማድረግ
 • ሞኖፊላመንት መረብ በስፋት ከዉጭ በመተማ በኩል በህገ ወጥ መንገድ በመግባት በገቢያ ላይ የሚሽጥበት ሁኔታ በመኖሩ አብዛኛዉ አስጋሪ በዚህ መረብ መጠቀሙ እና በዓሳ ሃብት ልማቱ ሰፊ ጉዳት እያደረሰ ቢሆንም ማስቆም አለመቻሉ
 • በወንዞች ፔን ካልቸር እንዲሁም በግድቦች የኬጅ ካልቸር ቴክኖሎጅን ማስፋፋት አለመቻሉ እንዲሁም ግድቦች በሚገነቡበት ወቅት ለዓሳ ሃብት ልማት እንዲዉሉ ከሚመለከታቸዉ የምህንድስና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት አለመስራት
 • ሁሉም የመስኖተጠቃሚአርሶአደሮችባሉበትአካበቢዎችከሌሎቸየግብርናልማትእንቅስቃሴዎችጋርበማቀናጀትበአ/አደርደረጃ ኩሬ በማዘጋጀት በዓሳ ግብርና እንዲሳተፉ በማድረግ በኩል የተሰራዉ ስራ አናሳ መሆን
 • የዓሳ ግብርናን ከሩዝ ግብርና ጋር በማቀናጀት /አምባዛ /(የቀይ ዓሳ ዝርያዎችን) በሩዝ ማሳዎች ጫጩት በመጨመር አ/አደሮች የዓሳ ምርት ከማምረታቸዉ ባሻገር ከዓሳዉ የሚወጣዉ ፅዳጅ ለሩዙ ምርት መጨመር አሰተዋፅኦ ቢኖረዉም ወደ ስራ አለመገባቱ

 

 

 

ዜና

በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 04 በወተት ሃብት ልማት ስራ ጥሩ እንቅስቃሲ እያደረጉ ያሉ ግለሰብ

አቶ እንድሪስ አደም ነዋሪነታቸው በኮምቦልቻ ከተማ ቀበሌ 04 ነዋሪ ሲሆኑ ግለሰቡ ከዚሀ በፊት የመንግስት ሰራተኛ የነበሩ ሲሆን ግለሰቡ ከ 2010 ዓ.ም ጀምሮ 5 የወተት ላሞችን በመያዝ ወደ ስራ የገቡ ሲሆን አሁን ላይ ጊደሮች እና ጥጃዎችን ጨምሮ ከ 30 ያላነሱ የተሻሻሉ ዝርያ ያላቸውን እንስሳት ይዘዋል፡፡ ግለሰቡ ለላሞቻቸው ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል እውቀትና እና የስራ ተነሳሽነት ያላቸው ሲሆን በባለሙያዎች ዘንድ የሚደረግላቸውን ድጋፍም በአግባቡ እንደሚተገብሩ የወተት ላም እርባታ ጣቢያቸውን በጐበኝንበት ወቅት ማረጋገጥ ችለናል፡፡አቶ እንድሪስ በቀን ከ 200 ሊትር ወተት ያላነሰ የሚያገኝ መሆኑን ገልፀው ወተቱን የሚሸጡበትም ጦይባ የወተትና የወተት ተዋጽኦ መሸጫ የሚባል ድርጅት እንዳላቸው አክለዉ ገልፀውልናል፡፡

በአጠቃላይ የግለሰቡ የስራ እንቅስቃሴ ለሌሎት የህ/ሰብ ክፍሎች አርያነት ያለው በመሆኑ ከእሳቸው ተሞክሮ ተምረን የበለጠ ውጤታማ እንድንሆን እንትጋ መልዕከታቸን ነው፡፡

ዜና

ደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ሀርቡ 02 ቀበሌ  በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት የኘሮጀክት ድጋፍ በዶሮ ሃብት ልማት ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች 

 1. አቶ ጀማል አወል ነዋሪነታቸው በቃሉ ወረዳ ሀርቡ ቀበሌ ሲሆን ግለሰቡ በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት 30 የእንቁላል ዶሮዎች፣ የመመገቢያና የመጠጫ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጎላቸው በዶሮ እርባታ ወደ ስራ የገቡ ግለሰብ ሲሆኑ ግለሰቡ ለዶሮዎች ተገቢውን እንክብካቤ ማድረግ በመቻላቸው በቀን 27 እንቁላል ያገኛሉ፡፡
 2. አቶ ጀማል የሱፍ ነዋሪነታቸው በቃሉ ወረዳ ሀርቡ ቀበሌ ሲሆን ግለሰቡ በእንስሳትና ዓሣ ሀብት ሴክተር ልማት ኘሮጀክት 30 የእንቁላል ዶሮዎች፣ የመመገቢያና የመጠጫ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጎላቸው በዶሮ እርባታ ወደ ስራ የገቡ ግለሰብ ሲሆኑ ግለሰቡ ለዶሮዎች ተገቢውን እንክብካቤ ባለማድረጋቸው በቀን ከ 17-20 እንቁላሎችን በአማካኝ ያገኛሉ፡፡

ዜና

የአብክመ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ icipe Moyeshe ፕሮጀክትጋር በመተባበር ከታህሳስ 3__4/2013 በባህርዳር ከተማ የማር ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱ አካሄደ፡፡

 

የአማራ ክልል ባለው የአየር ፀባይ እና የመሬት አቀማመጥ ለተለያዩ የቀሰም እፅዋቶች እንዲኖሩ ምቹ አከባቢ በመሆኑ 

ለንብ ሃብት ልማት ተግባር ተስማሚ ነው ክልላችን 1,349,320 ህብረ ንብ እንዳለውና ከሃገር አቀፍ ጥቅል የህብረ 

ንብ ብዛት ደግሞ 20% ድርሻ እንዳለው 2012 የማዕከላዊ ስታትስቲክስ /CSA/ መረጃ ያሳያል፡፡

ክልሉ ካለው አጠቃላይ አግሮ ኢኮሎጂ አንፃር የቆላ እና ወይና ደጋ የመሬት ሽፋን 72.8% መሆኑ ለንብ ሃብት ልማት 

ስራ የበለጠ ተስማሚያደርገዋል፡፡ ክልሉ በማርና ሰም  ልማት ከጥንት ጀምሮ ሲሰራበት የቆየ የካበተ ልምድ ቢኖረውም 

ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም እና አሰራሩን ወደ ዘመናዊ የማነብ ዘዴ በማሸጋገር ከዘርፉ መገኜት ያለበትን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ በአግባቡ እንዳያገኝ አድርጎታል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በንብ ሃብት ልማት ስራዎች መሬት አልባ ስራ አጥ 

ወጣቶችን በቡድን እና በኢንተርፕራይዝ በማደራጀት፣ የተሻለ የመልማት አቅም ያላቸውን የተከዜ ተፋሰስ እና የአባይ ሸለቆ አካባቢዎችን የንብ ሃብት ልማት ኮሞዲቲ ተቀርፆ ተግባራዊ እንዲደረግ በማመቻቸት እና ወጣቶች የተሻሻሉ የቴክኖሎጅ ውጤቶችንና ግብዓቶችን በመጠቀም በአካባቢያቸው ለሚገኙ አናቢ አርሶ አደሮች የቴክኒኖሎጅ ሽግግር ለማምጣት የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከዓለም አቀፉ የስነ ነፍሳት እና ስነ ምህዳር የምርምር ተቋም /icipe/ ከሚያስተባብራቸው የተለያዩ ፕሮጀክቶች ጋር 

በጋራ በመሆን ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡

ክልላችን ካለው እምቅ የንብ ሃብት አቅም አኳያ የአብክመ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከዓለም አቀፉ የስነ ነፍሳት እና ስነ ምህዳር የምርምር ተቋም /icipe/ ጋር በጋራ በመሆን ከ4 ዞኖችና 13 ወረዳዎች 

የተውጣጡ ማርና ሰም አምራች ኢንተርፕራይዞች፣ ማህበራት፣ ቡድኖች እና ግለሰቦችን ጨምሮ ሌሎች ተሳታፊ እንግዶች

በተገኙበት ከታህሳስ 03-04/2013 . በባህር ዳር ከተማ የፓናል ውይይትና ኤግዚቢሽኑን ተካሂዷል፡፡ ይህም ለገበያ ትስስር፣ 

ባለሃብቶችን ለመሳብ፣ ክልል አቀፍ ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥና ለማስፋት፣ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ግብዓቶችን ለማስተዋወቅ እንዲሁም ለዘርፉ መነቃቃት ታላቅ አስተዋፅዖ ይኖረዋል፡፡

 

ዓላማ

የንብ ውጤቶች ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንሱ የሚከተሉት ዋና ዋና ዓላማዎች ይኖሩታል፡-

Ø የአማራ ክልልን የማርና ሰም ምርት ለማስተዋወቅ

Ø  የማርና ሰም የግብይት ስረዓትን በማዘመን አምራቹ ምርቱን ቀድሞ የመሸጥምምነት እንዲጀመር ለማድረግ

Ø  ከፍተኛ የመግዛት አቅም ያላቸው ነጋዴዎች ወደ ክልሉ እንዲመጡ ለማድረግ እና በአምራችና በገዥ መካከል ያለውን የገበያ ትስስር ለማጠናከርና ጤናማ የገበያ ውድድር ስረዓትን ለመዘርጋት

Ø የቀፎ ውጤቶችን ለዓለማቀፍ ገበያ ለማቅረብ እንዲቻል የተሻለ ልምድ ለመውሰድ እና ምርቶቻችንን ወደ ውጭ በመላክ ዘርፉ ለአናቢዎች እና ለሃገር ኢኮኖሚ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ለማድረግ

Ø የማርና ሰም ምርትን እሴት በመጨመር የራሱ ብራንድ ያለው ምርት ለገበያ ለማቅረብ የሚያስሉ ተሞክሮዎችና ልምዶችን ለመውሰድ

Ø ዘመናዊ የምርትና ግብይት ሥረዓትን ለመዘርጋት የሚመለከታቸውን ባለ ድርሻ አካላት ያሳተፈ ኮንፈረንስ በማድረግ ችግሮቻችንን በጋራ በመለየት ለቀጣይ ስራዎቻችን ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር

 

 

ግብ

Ø በክልሉ ውስጥ በማርና ሰም ምርትና ግብይት ስራዎች ላይ የሚሳተፉ ተዋናዮችና ባለ ድርሻ አካላት በጋራ በመሆን የንብ ውጤቶች ኤግዚቢሽንና ኮንፈረንስ በክልል ደረጃ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት በብቃት መፈፀም፡፡

 

የኤግዚቢሽንና  ኮንፈረንሱ አስፈላጊነት

Ø የማር አምራቹን ተጠቃሚነት ማረጋገጥና የሃገር አቀፍ ገበያን ለማመቻቸት፣

Ø  ከገበያ ትስሰር ጋር በተያያዘ የምርትና ግብይት ተዋንያንን አቅም ለመገንባት፣

Ø በሚቀርቡ ጥናታዊ ፅሑፎች በቂ ክህሎት እና ልምድ ለማግኘት፣

Ø የክልሉን የማርና ሰም ምርት ለማስተዋወቅ፤

Ø  በማር ምርት ጥራትና አስተሻሸግ ዙሪያ ልምድ ለማግኘት፤

Ø  በዘርፉ ስራዎች ዙሪያ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት፣

 

ከየኤግዚቢሽንና  ኮንፈረንሱ የሚጠበቅ ዉጤት

Ø የግብይት ተዋንያኖች ስፊ የግብይት ልምድ ያገኛሉ፣

Ø  የክልላችን የንብ ሃብት አቅም ማስተዋወቅና ባለሃብቶችን መሳብ ያስችላል

Ø  የንብ ሃብት ልማት የስራ እንቅስቃሴ የበለጠ መነቃቃት ይችላል 

Ø  በማር፣ ሰምና ሌሎች የቀፎ ውጤቶች ዘላቂ የገበያ ትስስር ይፈጠራል፣

Ø  ባለሙያዎች ከኮንፈረንሱ በቂ ልምድና ክህሎት ያገኛሉ፣

Ø ከተለያዩ ተሞክሮዎች የተሻሉ ልምዶችን ማግኜት ይቻላል

 

በኤግዚቢሽንና  ኮንፈረንሱ የተሳተፉ አካላት

በክልል ደረጃ በተካሄካሄደው የንብ ውጤቶች ኮንፈረንስና ኤግዚቢሽን የክልሉ ርዕሰ መስተረዳድር አማካሪ አቶ ዓለሙ ጀምበርን ጨምሮ የቢሮ ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣የicipe አመራሮች እና ባለሙያዎች፣ ዞኖች እና 13 ወረዳዎች ዋና አስተዳዳሪዎችን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የማርና ሰም አምራቾች፣ በዘርፉ ወደ ስራ የገቡ ቡድኖች፣ ኢንተርፕራይዞች፣ ማህበራት፣ነጋዴዎች፣ ዩኒኖች፣ የማርና ሰም ግብዓት 

አቅራቢዎች፣አቀነባባሪዎች፣ ዘርፉን የሚደግፉ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማቶች፣ አገልግሎት ሰጭ የመንግስት መስሪ ቤቶች፣

የምርምር ተቋማት  እና የመሳሰሉት ተሳትፈዋል፡፡

የፓናል ውይይቱ በዩኒሰን ሆቴል ለ2 ቀናት የተካሄደ ሲሆን የአራቱም ዞኖች ሪፖርት ከቀረበ በኋላ የተገኙ ውጤቶችን በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል እና የዘርፉ ዋና ዋና ችግሮች ናቸው ተብለው የቀረቡትን የብድር አቅርቦት ችግር፣ የገበያ ትስስር ማነስ፣ ህገ ወጥ የኬሚካል ርጭት እና የመሳሰሉት ሃሳቦች ላይ ምክክር በማድረግ በቀጣይ ችግሮቹን ለመቅረፍ በሚያስችሉ መፍትሄዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል፡፡

የንብ ውጤቶች ኤግዚቢሽን በባህር ዳር ዓለማቀፍ ስታዲየም ለተመሳሳይ 2 ቀናት የተካሄደ ሲሆን ከ4 ዞኖች የተመረጡ ከ13 ወረዳዎች የተገኙ ማር አምራች ወጣቶች ጥራቱን የጠበቀ ማር፣ ሰም እና ፕሮፖሊስ በማቀነባበር እና በማሸግ ለኤግዚቢሽን በማቅረብ ለከተማው ህብረተሰብ በማስተዋወቅ ግብይ ተካሂዷል፡፡

 

በመጨረሻም YESH ፕሮጀክት ከሚሰራባቸው 13 ወረዳዎች በስራ አፈፃፀም 1ኛ ደሃና ወረዳ፣ 2ኛ አዋበል ወረዳ፣ 3ኛ ጓንጓ ወረዳ በደረጃ ተለይተው ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

 

 

 

ዜና

የደቡብ ጎንደር ዞን እንስሳት ሃብት ልማት ተ/ጽ/ቤት የ2012 በጀት ዓመት የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2013 እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ

 

የደቡብ ጎንደር ዞን እንስሳት ሃብት ልማት ተ/ጽ/ቤት የዞኑ ክፍተኛ አመራሮች፤ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የድርጀት ጽ/ቤት ሃላፊዎች፤ በዞኑ እንስሳት ሃብት ልማት ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና የወረዳ ተ/ጽ/ቤት ሃላፊዎችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የአዳቃይ ቴክኒሻን በተገኙበት በቀን 10/02/2013ዓ.ም በአዲስ ዘመን ከተማ የ2012 በጀት ዓመት የዋና ዋና ስራዎች እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2013 እቅድ ትውውቅ መድረክ አካሄደ መድረኩ በዞኑ ክፍተኛ አመራሮች የተመራ ሲሆን በመድረኩ የተሻሉ አፈፃፀም ላላቸው መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፤ ወረዳዎች እና አዳቃይ ቴክኒሻያኖች እውቅና እና የማበረታቻ የምስክር ወረቀት ተሠጥቷል ፡ ፡

ዜና

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2013 እቅድ የስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡

 

የእንስሳትና ዓሣ ሀብት ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2012 በጀት አመት የዋና ዋና ስራዎችን እቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2013 ዓም እቅድ ትውውቅየስትሪንግ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በቀን 22/01/2013 ዓ.ም በደብረ ታቦር ከተማ አካሄደ፡፡

ኘሮጀክቱ በ2012 በጀት አመት በወተት ሃብት ልማት፣ በቀይ ስጋ፣ በዶሮ ሀብት ልማት እና በሣ ሃብት ልማት በአርሶ አደር እና በተደራጁ ወጣቶች ዙሪያ የተሰሩ የፊዚካል ስራዎችን ከፋይናንስ አፈፃፀሙ ጋር በዝርዝር በሪፖርት ያቀረበ ሲሆን የስትሪንግ ኮሚቴ አባላትም በቀረበው ሪፖርት በስፋት ከተወያዩ በኃላ የሚከተሉትን ዋና ዋና ገንቢ አስተያየቶች አስቀምጠዋል፡፡ 

• ኘሮጀክቱ ከኮቪድ ጋር ያለውን ወቅታዊ ችግር ተቋቁሞ የ2012 በጀት አመት እቅድን 94% መፈፀም መቻሉ ጥሩ መሆኑንና በቀጣይ ከዚህ በበለጠ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት

• ኘሮጀክቱ ዘርፍን ለማዘመን ለወጣቶችና ሴቶችን የስራ ዕድል ለመፍጠር ፋይዳው ትልቅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በተጀመረዉ አግባብ ይበልጥ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት

• በየደረጃው ያለው ስትሪንግ እና ቴክኒክ ኮሚቴ በመደበኛ ጊዜ ተግባሩን እየገመገመ ከመሄደ አንፃር ያለው ሁኔታ ጥሩ ነው፡፡ በቀጣይም ቢጠናከር

• የሪፖርት አቀራረብ ጥሩ ነው በቀጣይ በአፈፃፀም የተሻሉና ችግር ያለባቸውንም ለይቶ ቢያቀርብ የበለጠ ለግምገማ አመች እንደሚሆን፡፡

• በአንድ የፍላጎት ቡድን የሚመደበው በጀት አናሳ ነው በቀጣይ ቢታይ የሚሉ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በዚህ ዙርያ የሚመለከታቸዉ የስራ ሀላፊዎች በቂ ማብራሪያ በመስጠት የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሯል፡፡ በእለቱም የ2013 እቅድ ቀርቦ ዉይይት ከተደረገበት በኋላ እቅዱ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡

 ዜና

የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት ለ15 ወረዳዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ካሄደ፡፡ 

የአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የእንስሳት አያያዝ ትግበራ ለመመዘን የሚያገለግል መመሪያ ዙሪያ በፕሮጀክቱ በታቀፉ 15 ወረዳዎች ለሚገኙ የዘርፉ ሃላፊዎች ፤ሙያተኞች እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች ከ14-18/01/2013 ዓ.ም በፍኖተ ሰላም ከተማ የአሰልጣኞች ስልጠና ካሄደ፡፡ ስልጠናው በቀጣይ ፕሮጀክቱ በሚሰራባቸው ወረዳዎች ለሚገኙ የቀበሌ ሙያተኞች እንደሚደርስ ተጠቁሟል፡፡

ዜና

የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2012 እቅድ አፈፃፀም እና የ2013 የእቅድ በቴክኒክ ኮሚቴ ተገመገመ፡፡

የእንስሳትና ዓሣ ዘርፍ ልማት ኘሮጀክት የ2012 በጀት አመት የዋና ዋና ስራዎች አፈፃፀም ግምገማ እና የ2013 በጀት አመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ የቴክኒክ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት በ 3/01/2013 ዓ.ም በእንጀባራ ከተማ አካሄደ፡፡ ፕሮጀክቱ በበጀት አመቱ ያከናወናቸዉን ዋና ዋና ስራዎች ያቀረበ ሲሆን

ከወጣቶች አንጻር የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች በተመለከተ

በደሮ ለ2460 ወጣቶች(ሴ 1007) ለ1 ወጣት ባአማካኛ 25 ደሮዎችን እና የደሮ መጠላይ ግንባታ፣መኖ፣ መመገቢያና መጠጫ ቁሳቁስ የማሟላት

በቀይ ስጋ ለ1405 ወጣቶች (ሴ 348) በአማካኝ ለ15 ወጣቶች 30 በግ፣የበግ መጠለያ ፣መኖ፣መመገቢያና መጠጫ ቁሳቁስ የማሟላት

በአሳ ለ170 ወጣቶች(ሴ 25) የሸድ ግንባታ፣የመበለቻ ቁሳቁስ፣ዲፕ ፍሪጅ ፣ጄኔረተር እና የማጓጓዣ ቁሳቁሶችን የማሟላት ስራ መከናወኑ ተጠቅስዋል፡፡

በወተት ለ6023 አርሶ አደሮች (ሴ2081) የወተት ላሞችን ቤት በአዲስ የመገንባትና የማሻሻል፣ መኖ የማቅረብ እንዲሁም መመገቢያና የመጠጫ ገንዳ የማዘጋጀት ስራ የማሟላት

በደሮ ለ5341 አርሶ አደሮች (ሴ 3257) ለ 1 አርሶ አደር ባአማካኝ 25 የእንቁላል ጣይ ደሮዎችን ገዝቶ የማቅረብ፣ሸድ የመገንባት ፣መኖ የማቅረብ እና መመገቢያና የመጠጫ ቁሳቁሶችን አሟልቶ የማቅረብ

በቀይ ስጋ ለ4658 አርሶ አደሮች (ሴ1548) የበግ ጋጣ የማሻሻል፣መኖ ማቅረብ እንዲሁም መመገቢያና መጠጫ የማሟላት

በአሳ ለ 85 አርሶ አደሮች (ሴ9) የአሳ ኩሬ የማዘጋጀት፣መበለቻ ሸድ የመገንባት፣የአሳ ጫጩት ኩሬ ላይ የመጨመር፣ዲፕ ፍሪጅና ጀኔረተሮችን ገዝቶ የማቅረብ እንዲሁም የማስገሪያ ፣የመበለቻ እና የማጓጓዣ ቁሳቁሶችን ገዝቶ የማሟላት ስራ መከናወኑና ከላይ ለተጠቀሱ አጠቃላይ ተግባሮች 127,321,160 ብር ስራ ላይ መዋሉ በሪፖርቱ ተመላክትዋል፡፡

ከአርሶ አደሮች አንጻር የተከናወኑ ዋና ዋና ስራዎች በተመለከተ

ፕሮጀክቱ በወጣቶችና በአርሶ አደር ደረጃ ካሉ ተጠቃሚዎች ከሚሰራዉ ስራ በተጨማሪ በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ የሚሰሩ ተቋማትን በግብአትና በመሳሰሉ ጉዳዮች የማጠናከር ስራ እንደሚሰራ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በዚህ ዙርያ በበጀት አመቱ

 • ለአርሶ አደር ሰርቶ ማሳያዎች ሞዴል መገንባትና ቁሳቁስ ማሟላት
 • ለወረዳ እና ለቀበሌ የእንስሳት ጤና ክሊኒኮች የህክምና ቁሳቁሶችን የማሟላት
 • ለአርሶ አደር ሰርቶ ማሳያዎች የመኖ ዘር እና ቴክኖሎጂ አቅርቦት
 • ለ 2 ላብራቶሪ ቁሳቁስ ግዥ
 • ለ 15 ወረዳዎች 15 መኪናዎች እና ለ 2 ላቦራቶሪዎች ለእያንዳንዳቸዉ 5 መኪናዎች
 • ለ15 ወረዳዎች 37 ሞተር ባይስክል ግዥ
 • ለባህር ዳር አሣ ምርምር ማዕከል ለአሣ ጫጩት ማምርቻ የሚያገለግል ቁሳቁስ የማሟላት
 • ለPPR መከላከልና ቁጥጥር

ድምር 28,935,170 ብር ስራ ላይ መዋሉ ተመላክትዋል፡፡

በአጠቃላይ ከላይ በዝርዝር የተከናወኑ ስራዎች ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱም ኘሮጀክቱ ያቀዳቸውን ስራዎች በአብዛኛው{94%} ከማሳካት አንፃር የሄደበት ርቀት የተሻለ መሆኑ መድረኩን በመሩት የኤጀንሲዉ ም/ስራ አስኪያጅና የቴክኒካል ኮሚቴዉ ሰብሳቢ በሆኑት በአቶ ፈንቴ ቢሻዉ እና በተወያዮቹ ተገልፃል፡፡ በአፈፃፀም ረገድ የታዮ ውስንነቶች ላይም በቀጣይ መሻሻል እንዳለባቸዉ ሰብሳቢዉ አሳስበዋል፡፡ በቀጣም የተሻለ ስራ ለመስራት ቅንጀቲዊ አሰራሮች ከላይ እስከ ታች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት በመድረኩ የጋራ ግንዛቤ ተይዟል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኘሮጀክቱ የ2013 እቅድ ቀርቦ ውይይት ከተደረገበት በኃላ እቅዱን የሚያዳብሩ ሀሳቦች ከተወያዮቹ ቀርቦ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

ዜና

የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከ26—27/12/2012 በባህርዳር ከተማ የ2012 በጀት አመት የዋና ዋና ስራዎች የእቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2013 እቅድ ትዉዉቅ አካሄደ፡፡ 

የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከ26—27/12/2012 በባህርዳር ከተማ የዞን ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች ፣የማአከላት ሀላፊዎች፣የ 3ቱ ከተማ አስተዳደርና ሀላፊዎችና ቡድን መሪዎች እንዲሁም የኤጀንሲዉ ስራ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት የ2012 በጀት አመት የዋና ዋና ስራዎች የእቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2013 እቅድ ትዉዉቅ አካሄደ፡፡በመድረኩ የዋና ዋና ስራዎች አፈጻጸም ማለትም፡- የእንስሳት ዝርያ ማሻሻል፣ የእንስሳት መኖ ልማት፣የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ስራዎች እንዲሁም በንብ ሀብት ልማትና በአሳ ሀብት ልማት ስራዎቻችን ዙርያ በአፈጻጸም ረገድ የነበሩ ጥንካሬዎችና እጥረቶች ተለይተዉ በዝርዝር የተገመገሙ እና በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት በሚቻልበት ሁኔታ የጋራ ግንዛቤ የተየዘ ሲሆን፡፡ በመጨረሻም የ2013 በጀት አመት እቅድ ቀርቦ ሰፊ ዉይይት ከተደረገበት በኋላ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተሰጥተዉ ዉይይቱ ተጠናቆዋል፡፡

 

ዜና

የንብ ሃብት ልማትን ለማዘመን እየተሰሩ ያሉ ስራዎች እና በተሰሩ ስራዎች የህ/ሰቡ ተጠቃሚነት በተለይ ዘርፉ ለወጣቶችና ሴቶች የስራ እድል ከመፍጠር አንፃር ያለው ፋይዳ

በኢትዮጰያ 6,523,969 የሚጠጋ የንብ መንጋ ብዛት እንዳለ የCSA-2010 መረጃ ያሳያል ከዚህም ውስጥ በአማራ ክልል 1,154,094 የንብ መንጋ ብዛት እንዳለ ያሳያል ይህም ከሃገሪቱ የንብ ሃብት ብዛት 17.7% ድርሻ ይኖረዋል ማለት ነው እንዲሁም በ2010 CSA መረጃ መሰረት በአማራ ክልል 1,115,835 ባህላዊ ቀፎ እንዲሁም 5,986 የሽግግር ቀፎ እና 32,273 ዘመናዊ ቀፎ ይኖራል ተብሎ ይገመታል፡፡ የንብ ሀብት ተግባር ከተለያዩ አቅጣጫወች ሲታይ ሁለገብና አስተማማኝ ዘላቂ የሆነ ጥቅም የሚያስገኝ ስራ ነው፡፡ ከጤና አንጻር በመዳህኒትነት የሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮችን የያዘና በምግብነትም ከፍተኛ የሆነ የሀይል ምንጭ ሲሆን ፣ ከኢኮኖሚ ጠቀሜታ አንጻር ሲታይ በቀጥታ የንብ ውጤቶችን ማለት ማር ሰም   ዞፍ (የንብ ሙጫ) ድኝ መርዝ ለገበያ በማቅረብ ገቢ የሚያስገኝ ዘርፍ ነዉ፡፡የንብ እርባታ ስራ በአነስተኛ የመነሻ ካፒታልና በውስን የመሬት ይዞታ ወደ ልማቱ በማስገባት የምግብ ዋስትናን ያረጋግጣል፡፡ ዘርፉ በርካታ ስራ አጥ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን በአጭር ጊዜ ስልጠና ሰጥቶ ወደ ልማቱ በማስገባት የስራ እድል ሊፈጥር የሚችል የስራ መስክ ነው፡፡ ንቦች እንደ ሌሎች ተመሳሳይ በራሪ ነፍሳት በማንኛውም የእነባ ዘዴ፡- የእጽዋትን ሽፋን በመጨመር ፣የአፈር መሸርሸርን በመከላከልና የውሀ ስርገትን መጨመር ጎርፍን በመቀነስ የበለጠ ምቹና አስተማማኝ አካባቢን ይፈጥራሉ:: እንዲሁም ውብና ጽዱ አካባቢን ለመፍጠር የንብ ሀብት ተግባራት ከማርና ሰም ምርት ያለፈ ወሳኝ ተግባር ያላቸው መሆኑን በተለያዩ ጊዜያት የወጡ መረጃወች ይጠቁማሉ፡፡ በሌላ በኩል ሲታይ የንብ ማነብ ስራ የሰብል ምርትን በመጨመር የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አንጻር አይነተኛ አማራጭ ነው፡፡ ንቦች እጽዋትን በማራከብ ከ20-140% የእጽዋትን ምርት እንደሚያሳድጉ ልዩልዩ መረጃወች ይጠቁማሉ፡፡ ከ300 የገበያ ሰብሎች /commercial crops/ ውስጥ 84% ያህሉ በነፍሳት የሚዳቀሉ ናቸው፡፡ አማራ ክልል የንብ ሃብት ልማት ምቹ ሁኔታዎችና ተግዳሮቶች ስንመለከት ፡-ክልሉ ለንብ እርባታ ስራ ተስማሚ ስነ ምህዳር ያለዉ ክልል ነዉ ፡፡በክልሉ ከ800 በላይ የማር የቀሰም እፅዋቶች ይገኛሉ፡፡በአማራ ክልል የንብ ማነብ ስራ ለረጅም ዘመናት ሲከናወን የነበረ ተግባር በመሆኑ የአናቢዎች ከባቢያዊ እውቀት እና ልምድ የተሻለ መሆኑ ለንብ ማነብ ስራዉ ምቹ ያደርገዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫ መሆኑና የንብ ሃብት ፖሊሲና ስትራቴጂ መቀረፁ ፣ የንብ ሃብት ልማትን የሚደግፉ አዋጆች፣ደንቦችና መመሪያዎች መዘጋጀታቸው ፣ለገጠር ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ካለው ድርሻ አንፃር የመንግስት ዋነኛ አጀንዳ መሆኑ የማር ምርትና ምርታማነት በመጨመሩ ወደ ገበያ የሚወጣው የማር ምርት ከዕለት ወደ ዕለት እያደገ መሄዱና አማራጭ የገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱ ፣ እንዲሁም የተመረተውን የማር ምርት የገበያ ችግር ለመቅረፍና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ የሚያስችሉ 5 የማር ምርት ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች መኖራቸው እና ዘርፉን በምርምር፣በአቅም ግንባታ፣ በግብዓትና ቴክኖሎጂ ስራዎች የሚደግፉ አካላት /ተቋማት መኖራቸው ፣ እና በዘርፉ በርካት መንግስታዊ ልሆኑ ድርጅቶች የዘርፉን ልማት ለማገዝ እያሳዩት ያለዉጥረት አበረታች መሆኑና በለሙ ተፋሰሶች ላይ ከኬሚካል ርጭት ነፃ የሆነ የንብ እርባታ ስራ ለመስራት አመቺ መሆኑ ሀብቱን ለማልማት በምቹነት የሚጠቀሱ ጉዳዮች ናቸዉ፡፡ በተቃራኒዉ የንብ ሃብት ልማትና ግብይት ዋና ዋና ችግሮች ተብለዉ ከተለዩት ዉስጥ ፡-የባለሙያዎችና አናቢዎች የክህሎት ከፍተት መኖር፣ የማነቢያ ቁሳቁሶች በበቂ ሁኔታ አለመሟላትና ፡- የዋጋ ውድነት፣ የአቅርቦት ማነስ፣ የጥራት ችግሮች መኖር፣ህገ ወጥ የፀረ ተባይና ፀረ አረም ኬሚካል አጠቃቀም ፣ የማር ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ አለመግባት ፣ በማር እና ሰም ምርት የተደራጁ የንብ ውጤቶች ልማትና ግብይት ኅ/ሥራ ማህበራቶች የተጠናከሩ አለመሆን እና ዘላቂነት ያለው የገበያ ትስስር አለመኖር፣ የዘርፉን ልማት ለማዘመን በመሰረታዊነት ሚጠቀሱ ተግዳሮቶች ናቸዉ፡፡ ንብ አናቢዉ የህብረተሰብ ክፍል ዘመናዊ አሰራሮችን ተከትሎ እንዲያንብና የማር ምርትን በብዛትና በጥራት አምርቶ ራሱንና ሀገሩን የበለጠ ተጠቃሚ እንዲያደርግ የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ችግሮችን ለመፍታት ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት እየሰራ ይገኛል፡፡ ወደፊትም ይበልጥ አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

 

ዜና

በቡሬ አግሮ ኢንዱስትሪ አቅራቢያ ለሚገኙ የወተት ህብረት ስራ ማህበራት ድጋፍ ተደረገ ::

በክልሉ የወተት ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ያሉንን ዝርያዎች የውጭ ደም ካላቸውና በወተት ምርታቸው ከታወቁ እንስሳት ጋር በማዳቀል ዝርያቸውን የማሻሻል፤ የእንስሳት ጤና አጠባበቅ ተደራሽትንና ጥራትን የማሳደግ እንዲሁም የተሻሻለ መኖ ልማትን ማስፋፋት ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ይገኛል፡፡ እነዚህ ተግባራት ተሟልተው በተከናወኑባቸው በርካታ አካባቢዎች የወተት ምርት እድገት በማሳየቱ ወደ ገበያ የሚቀርበው ወተት እየጨመረ መጥቷል፡፡ በመሆኑም በክልላችን 119 የወተት ልማትና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው ወደ ተግባር በመግባታቸው የግብይት ስራውን በማሳለጥ በኩል የድርሻውን እየተወጡ ይገኛሉ፡፡ በተለይም 74 የሚሆኑንት ማህበራት ከ280 እስክ 3,800 ሊትር ወተት በቀን በማሰባሰብ የተሻለ ስራ በመስራት ላይ ናቸው፡፡ ኤጀንሲዉ የእነዚህን የወተት ህብረት ስራ ማህበራት አቅም ለማጠናከር በግብአት አቅርቦትና በድጋፍና ክትትል በርካታ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል∶∶ ከእነዚህ ስራዎችም ለቡሬ አግሮ ኢንደስትሪ ፓርክ ግብአት ያቀርባሉ ተብለዉ ከተለዩ የወተት ተፋሰስ ወረዳዎች በአንድ ማአከል ሆኖ ወተትን በተፋሰሱ ወረዳዎች በሚገኙ የወተት ህብረት ስራ ማህበራት እየሰበሰበ ለገበያ ማቅረብ የሚችል 10,000 (አስር ሽህ) ሊትር የመያዝ አቅም ያለዉ ኩለር የተገጠመለት ተሸከርካሪ እና 4 ሽህ ሊትር መያዝ የሚችል ችለር (ማቀዝቀዣ) ኤጀንሲዉ ሀምሌ 20 / 2012 የክልሉ ከፍተኛ ስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን በዳንግላ ወረዳ ለሚገኘዉ ሂወት የወተት ህብረተስ ስራ ማህበር አስረክቧል∶∶ በርክክብ ስነ-ስርአቱም የኤጀንሲዉ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ደበበ አድማሱ ተሸከርካሪዉ በአግሮ ኢንደስትሪዉ አቅራቢያ በሚገኙ ወረዳዎች ወተት ከወተት ህብረት ስራ ማህበራት እየሰበሰበ ለገበያ የሚያቀርብ መሆኑን ገልጸዉ ሂወት የወተት ስራ ማህበር ይህን ታሳቢ በማድረግ በተቀመጠዉ የአሰራር ሞዳሊቲ መሰረት ተግባራዊ እንዲያደርግ አጽእኖት ሰጥተዉ አሳስበዋል∶∶ የማህበሩ ሊቀመንበርም በተደረገላቸዉ ድጋፍ ከፍተኛ ደስታ የተሰማቸዉ መሆኑን ገልጸዉ ተሸከርካሪዉን በተቀመጠዉ የአሰራር ሞዳሊቲ መሰረት ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል ∶∶

 

ዜና

በአማራ ክልል እንስሳት እና ዓሳ ሀብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት የተሰሩ ስራዎች በግብርና ሚኒስትር ድኤታው ተጎበኙ::

የእንስሳት እና ኣሳ ሀብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በአማራ ክልል ወደ ስራ የገባዉ በ2011 በጀት አመት ነዉ፡፡ ፕሮጀክቱ የዘርፉን ልማት ለማዘመን ትልቅ አቅም ያለዉ ፕሮጀክት ሲሆን በክልሉ በ 15 ወረዳዎች በ 199 ቀበሌዎች 4110 ወጣቶችንና 16302 አርሶ አደሮችን በቀይ ስጋ ማድለብ፣ በወተት ፣በደሮ እና በዓሳ ሀብት ልማት አደራጅቶ ወደ ስራ አስገብቷል፡፡ፕሮጀክቱ በበጀት አመቱ ከላይ ለተጠቀሱ የህብረተሰብ ክፍሎች ለግብአት መግዣ፣ ለእንስሳት ቤት ግንባታና ማሻሻያ፣ እንዲሁም ለቁሳቁስ መግዣ በድምሩ 135 ሚሊዮን ብር በቀጥታ ለተጠቃሚዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቱ ለወጣቶች እና አርሶ አደሮች ከሚያደርገዉ ድጋፍ በተጨማሪ በፕሮጀክቱ ለታቀፉ የወረዳና የቀበሌ ሙያተኞች በስልጠና እና በቁሳቁስ አቅማቸዉን የማጠናከር እንዲሁም ለእንስሳት ጤና ክሊኒኮችን የህክምና ቁሳቁሶችን የማሟላት እንዲሁም በአርሶ አደር ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ለማስተማርያነት የሚሆኑ ግንባታዎችን በመገንባት አቅማቸዉን የማሳደግ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለ15 ወረዳዎች እና ለ2 ላቦራቶሪዎች ለእያንዳንዳቸዉ 1 ደብል ካፕ ቶዮታ መኪና እና 45 የሞተር ብስክሌቶችን ድጋፍ አድርጓል፡፡ ፕሮጀክቶ በ20/10/2012 በተመረጡ 2 ወረዳዎች በሜጫና በባህር ዳር ዙርያ ወረዳዎች በመስክ የተሰሩ ስራዎችን የፌደራል ግብርና ሚኒስትር ድኤታና የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ሀላፊዎች እንዲሁም የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች በተገኙበት የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡ በምልከታዉ በቀይ ስጋ ማድለብ ፣ በዓሳ ሀብት ልማት እና በወተት ሀብት ልማት ወደ ስራ የገቡ የህብረተሰብ ክፍሎች የስራ እንቅስቃሴ ተጎብኝትዋል፡፡ በጉብኝቱም በታዩ ጥንካሬዎች እና እጥረቶች ዙርያ አጭር ዉይይት ተደርጎ የቀጣይ አቅጣጫዎች ተቀምጠዉ የጉብኝት መርሀ ግብሩ ተጠናቋል፡፡

 

ዜና

የተከዜ ዓሳ ሀብትን ወደ ማዕከላዊ ገበያ የሚያደርሱ ተሽከርካሪዎች ለአራት ወረዳዎች ተሰጡ።

car07ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 29/2012 ዓ.ም የተከዜ ዓሳን ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስ እየተሠራ ነው። በ16 ሚሊዮን ብር ወጭ የተከዜን ዓሳ ሀብት ሳይበላሽ ወደ ማዕከላዊ ገበያ የሚያደርሱ ተሽከርካሪዎች ለአራት ወረዳዎች ተሰጥዋል።በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር እና በሰሜን ጎንደር ዞን ለሚገኙ አራት ወረዳዎች ማለትም ስሃላ ሰየምት፣ ዝቋላ፣ አበርገሌ እና ጠለምት ወረዳዎች ለአካባቢዎቹ ተስማሚ የሆኑና ማቀዝቀዥ ያላቸው አራት ተሽከርካሪዎች ዛሬ ሚያዝያ 29/2012 ዓ.ም ተሰጥቷቸዋል።ተሽከርካሪዎችን ያስረከቡት የአማራ ክልል እንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ሥራ አስኪያጅ ደበበ ዓድማሱ ተሽከርካሪዎቹ ወደ ሥራ መግባታቸው በስፋት ይነሳ የነበረውን የዓሳ ሀብት የገበያ ትስስር ችግር እንደሚቀርፉ ተናግረዋል።ተሽከርካሪዎቹ እያንዳንዳቸው በአንድ ጊዜ 60 ኩንታል ወደ ማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ የሚችሉ ናቸውም ብለዋል።ከተሸከርካሪዎቹ በተጨማሪም በሰቆጣና ነይረአቚ ከተሞች ላይ የተገነቡትን የዓሳ መሸጫና ማከፋፈያ ሼዶች ሥራ ለማስጀመር ርክክብ እየፈፀሙ መሆናቸውን ተናግረዋል።የአበርገሌና የጠለምት የዓሳ መበለቻ ሼዶችም ጀነሬተርና ውኃ ማጠራቀሚያ በርሚሎች በመገጠማቸው ሥራ መጀመር እንደሚችሉ ተመላክቷል፤ የዝቋላው ግን ለዓሳው ቅርበት ያለው ቦታ ላይ ያልተሠራ እና የመንገድ ቅየሳ ችግርም ያለበት መሆኑ ነው የተገለጸው።የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ በሪሁን ኪዳነማሪያም ተሽከርካሪዎችን በመረከባቸው ወደ ገበያ ለማቅረብ ይፈጠር የነበረውን የትራንስፖርት ችግር በመቅረፍ ዓሳን በጥራትና በትኩስነቱ ወደ ማዕከላዊ ገበያ ለማድረስ እንደሚያስችል ተናግረዋል።ተሽከርካሪዎቹ በሚሠሩባቸው ቦታዎች ያሉ የመንገድ ችግሮችን የክልሉ መንግሥት እንዲፈታ ማሳወቃቸውንም ገልጸዋል።የክልሉ ርእሰ መሥተዳደር ተመሥገን ጥሩነህ ከቅዳሚት እስከ ተከዜ ያለውን መንገድ በ2013 ዓ.ም የክልሉ መንግሥት ቅድሚያ ትኩረት ሰጥቶ ከሚሠራቸው ፕሮጀክትቶች አንዱ መሆኑን ቀደም ብለው ለአብመድ መናገራቸው ይታወሳል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወርቁ ለምለሙ ደግሞ ለጠለምት ወረዳ የተደረገው ድጋፍ ሰፊ የገበያ ዕድልን የሚፈጥር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ወረዳው ዝናብ አጠር በመሆኑ የዓሳ ዘርፉ ለአካባቢው ዓይነተኛ የኢኮኖሚ ምንጭ ይሆናልም ብለዋል።

ዜና

ሞየሽ (MOYESH) የተባለ ፕሮጀክት በ10/05/2012ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ የዉይይት መድረክ አካሄደ፡፡

(MOYESH)02ሞየሽ (MOYESH) የተባለ ፕሮጀክት በ10/05/2012ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ከፌደራል እስከ ወረዳ የሚመለከታቻቸዉ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ፕሮጀክቱ በሚሰራቸዉ ስራዎችና በቀጣይም በየደረጃዉ ካለዉ መንግስት አካላት ጋር ፕሮጀክቱን ዉጤታማ ለማድረግ በቅንጅት መሰራት ባለባቸዉ ጉዳዮች ዙርያ የዉይይት መድረክ አካሄደ፡፡ በመድረኩም በቀጣይ በፕሮጀክቱ ሊሰሩ የታሰቡ ስራዎች ቀርበዉ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ዉይይቱንም የፌደራል ግብርና ሚኒሰቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶክተር ገብረ እግዚአብሄር የአማራ ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሀላፊ አቶ ሻንበል እንዲሁም የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ አቶ ደበበ አድማሱ መርተዉታል፡፡ መንግስት በሀገሪቱ ውስጥ የወጣቶችን ሥራ አጥነት ለመቀነስ የሚያደርገውን ጥረት ለማገዝ የዓለም አቀፍ ሥነ-ነፍሳት ሳይንስ ሥነ-ምህዳር ማዕከል (International center of Insect physiology and Ecology) icipe ከማስተር ካርድ ፋውንዴሽንና ከኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለወጣቶች በሐርና ማር ልማት የላቀ ሥራ እድል ፈጠራ (MOYESH) የተሰኝ ኘሮግራም ቀርጾ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ የኘሮግራሙ ዋና አላማ ለወጣቶች ተገቢ እውቀትና ክህሎቶችን በመስጠት እና የንብና ልማት ኢንተርኘራይዞች እንዲመሰረቱ በማድረግና በእነዚህ የተደራጁ ማህበራት አማካኝነት 100.000 ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች (60% ሴትች) የሥራ ዕድልን በመፍጠር አስተማማኝ ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲያገኙ ማስቻል ነው፡፡ በተጨማሪም ኘሮግራሙ በተዛማች ውጤቶች አማካይነት በማር እና የሐር እሴት ሰንሰለት ላይ በሚገኙ 14.6 ሚሊዮን ሰዎች በጎ ተጽዕኖ ይኖረዋል፡፡ ሞየሺ (MOYESH) በአራት የኢትዮጵያ አካባቢዎች/ በአማራ፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች እና በትግራይ / በዓለም አቀፍ ሥነ-ነፍሳት ሳይንስ ሥነ-ምህዳር ማዕከል / icipe/ ከመንግስትና የግሉ ዘርፍ አካላት ጋር በመተባበር የሚተገበር የአምስት ዓመት ኘሮግራም /እ.ኤ.አ ከጥቅምት 2019 - ጥቅምት 2024/ ነው፡፡ የኘሮግራሙ መርህ በሀገሪቱ ውስጥ በግሉ ዘርፍ እና በገቢያ የሚመሩ የወጣቶችን የሥራ ዕድል መፍጠር ነው፡፡ የሚከተሉትን ክፍሎች አሉት፡፡

1. በንብ ሐር ልማት ለወጣቶች የሥራ እና የትምህርት ዕድሎችን መለየትና በእነዚህ ዘርፎች የተሰማሩ ኢንተርኘራይዞችን ማቋቋምና አጋርነቶችን ማሳደግ
2. ዘመናዊ የዲጂታል አማካኝነት ወጣት ወንዶችንና ሴቶችን ከገንዘብ አገልግሎት አቅራቢዎች ጋር ማገናኘት እንዲሁም የንግድ-ለንግድ ትስስር መፍጠር
3. የገቢያ ትስስሮችን ማጎልበት እና በወጣቶች የሚተዳደሩ ትርፋማ የንብ ማነብ፣ የሐር ልማት እና እንደ ጓሮ አትክልት ልማት ያሉ ተጓዳኝ ተግባሮችን ማጎልበት
4. በንብ ማነብና ሐር ልማት ሥራ ላይ ስኬታማ እና በዘላቂነት የሚሳተፉ ኢንተርኘራይዞችን እንዲሁም ተጓዳኝ እንቅስቃሴዎችን ለማካሄድ እና ለማስተዳደር የወጣቶችንና አጋሮችን ሙያዊ አቅም እና ችሎታ ማዳበር
5. ውሳኔ አሰጣጥንና ትምህርትን ለማቅለል በሥርዓተ ጾታ ትኩረት ያደረገ ቁጥጥር፣ ግምገማና ትምህርት ሥርዓትን ማዳበር እና መተግበር
6. ለኘሮጀክቱ ውጤታማ ትግበራ፣ ስኬታማ አስተዳደር፣ አደረጃጀት፣ አጋርነት እና የግንኙነት ስትራቴጁዎችን ማቋቋም

 

የኘሮግራሙ ቁልፍ ተግባር
❖ ለ100.000 ሥራ አጥ ወጣቶች (60% ሴትች) የቴክኒክ፣ ሥራ ፈጣሪነት እና የገንዘብ አያያዝና አስተዳደር ሙያዊና ክህሎት ማጎልበቻ ስልጠናዎችን መስጠት
❖ 4.850 የወጣት ቡድኖችን/ የህብረት ሥራ ማህበር እና 17.300 የግል የንብ ማነብ እና የሐር ልማት ኢንተርኘራይዞችን ማቋቋም
❖ 420 ግብዓት አቅርቦት ላይ የሚሰሩ የወጣቶች ኢንተርኘራይዞችን ማቋቋም
❖ 100.000 ወጣቶችን በተናጠል ወይም በቡድን ግብዓትና ምርት ገቢያ ጋር ማገናኘት እንዲሁም 80.000 ወጣቶችን ከፋይናንስ ቴክኖሎጂ አገልግሎት ጋር ማገናኘት
❖ ዲጂታል መድረክን ማዘጋጀት 80.000 ወጣቶች እና አጋሮች በዚህ ዲጂታል መድረክ በኩል የቴክኒክ ድጋፍ እና የገቢያ መረጃን ያገኛሉ
❖ ወጣቶችን የሚያገለግሉና የሚያግዙ 1800 የመንግስት የግል ተቋማት ሰራተኞችን ችሎታዎች እና አቅምን ማጎልበት 
❖ በኘሮግራሙ በተፈጠሩ የገቢያ ትስስሮች አማካኝነት 14.000 ቶን ጥራት ያለው ማር እና 1.400 ቶን ሰም በማጣራት፣ በማቀነባበርና በመሸግ ለሽያጭ እንዲቀርብ ማስቻል ነዉ፡፡

ዜና

የከልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከ EIF ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በ09/05/2012 ዓ.ም በምእራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ የንብ ዉጤቶች ፌስቲቫል እና የፓናል ዉይይት አካሄደ፡፡

EIF ፕሮጀክት03የከልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከ EIF ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በ09/05/2012 ዓ.ም በምእራብ ጎጃም ዞን ሰከላ ወረዳ የንብ ዉጤቶች ፌስቲቫል እና የፓናል ዉይይት አካሄደ፡፡ በ ፌስቲቫሉ ቁጥራቸዉ ከ 20 የማያንሱ የ4 ወረዳ አናቢ ማህበራት የማርና ሰም ምርታቸዉን ለእይታና ለገብያ አቅርበዋል፡፡ በእለቱም ተጣርቶ የታሸገ 1 ኪሎግራም ማር በ250 ብር ተሸጥዋል፡፡ ከፌስቲቫሉ በተጨማሪ የአናቢ ማህበራትን የስራ እንቅስቃሴ በመስክ ምልከታ በማድረግ ፕሮጀክቱ በዞኑ ከንብ ሀብት ልማት አንጻር ያከናወናቸዉን ስራዎች እና የወጣቶችን ተጠቃሚነት እንዲሁም በስራ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን አስመልክቶ በዞኑ እንስሳት ሀብት ልማት ተጠሪ ጽ/ቤት በኩል የመወያያ ጽሁፍ ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡ ዉይይቱን የመሩት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ስሜነህ እና ክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ደበበ አድማሱ ሲሆኑ ፕሮጀክቱ ከንብ ሀብት ልማት አንጻር በዞኑ በ 5 ወረዳዎች የሰራቸዉን ስራዎች አፈጻጸማቸዉ ከወረዳ ወረዳ ቢለያይም በጣም ጥሩ መሆኑን ጠቁመዉ በቀጣይ በእነዚህ ወረዳዎች የተሰሩ ምርጥ ስራዎች በዞኑ ባሉ ሁሉም ወረዳዎችና ቀበሌዎች መስፋት እንዳለባቸዉ ለዚህም በየደረጃዉ ያለዉ አመራርና ሙያተኛ የበኩሉን ሀላፊነት መወጣት እንዳለበት አጽእኖት በመስጠት በዉይይቱ ማጠቃለያ አሳስበዋል፡፡

ዜና

የእንስሳትና አሳ ሀብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክቱ የዘርፉን ልማት ለማዘመን አጋዥ የሆኑ 17 ተሸከርካሪዎችን ለ15 ወረዳዎች እና ለ2 የእንስሳት ጤና ላቦራቶሪዎች የቁልፍ ርክክብ ተደር፡፡

የእንስሳትና አሳ ሀብት ዘርፍ ልማት ፕሮጀክት በክልላችን በ15 ወረዳዎች በ2011 በጀት አመት ስራ የጀመረ ሲሆን ፕሮጀክቱ በስጋ ፣በወተት፣በደሮ እና በአሳ ሀብት ልማት የተሰማሩ የህብረተሰብ ከፍሎችን እና በዘርፉ የተሰማሩ ማህበራትን በስልጠና እና በግብአት በመደገፍ ዉጤታማ ና ተጠቃሚ ለማድረግ የሚሰራ ፕሮጀክት ከመሆኑ በተጨማሪ ፕሮጀክቱ በዘርፉ የሚሰሩ ተቋማትን በስልጠና እና በግብአት ማጠናከርን አላማ አድርጎ ወደ ስራ የገባ ፕሮጀክት ነዉ፡፡ ፕሮጀክቱ የዘርፉን ልማት ለማዘመን አጋዥ የሆኑ 17 ተሸከርካሪዎችን ለ15 ወረዳዎች እና ለ2 የእንስሳት ጤና ላቦራቶሪዎችበቀን 04/05/2012 ዓ.ም የ15 ወረዳዎች እና የባህርዳርና ኮምቦልቻ እንስሳት ጤና ላቦራቶሪ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት በክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ስራ አስኪያጅ አማካኝነት የቁልፍ ርክክብ ተደርጓል፡፡ በቁልፍ ርክክቡ ወቅትም በፕሮጀክቱ የታቀፉ ወረዳዎች የተመደበላቸዉን ተሸከርካሪዎች ለዘርፉና ለዘርፉ ስራዎች ብቻ ማዋል እንዳለባቸዉ ሀላፊዉ አጽእኖት ሰጥተዉ አሳስበዋል፡፡ በፕሮጀክቱ የታቀፉ የወረዳ ሀላፊዎችም የተሰጠዉን አቅጣጫ ተቀብለዉ ተሸከርካሪዎችን ለታለመላቸዉ አላማ ለማዋልና ፕሮጀክቱ ያስቀመጠዉን ግብ ለመፈጸም ጠንክረዉ እንደሚሰሩ ቃል በመግባት የርክክብ ስነስርአቱ ተጠናቋል፡፡

ዜና

የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከ scaling up of honey production and fair trade in Ethiopia ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በ17/04/2012 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ የንብ ሀብት ልማት ኢግዚቪሽንና ፓናል አካሄደ፡፡

sculingup honey01የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከ scaling up of honey production and fair trade in Ethiopia ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በ17/04/2012 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ የንብ ሀብት ልማት ኢግዚቪሽንና ፓናል አካሄደ፡፡ በኢግዚቪሽኑ ቁጥራቸዉ ከ15 ያላነሱ የንብ አናቢ ማህበራት የማርና ሰም ምርታቸዉን ለእይታ አቅርበዋል፡፡ በኢግዚቪሽኑም ጥሪ የተደረገላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች በመገኘት በአናቢ ማህበራት የቀረቡ ምርቶችን እንዲቀምሱ ተደርጓል፡፡ ግብይትም ተፈጽሟል፡፡ በፓናል ዉይይቱም ቁጥራቸዉ ከ100 ያላነሱ ተሳታፊዎች ተሳትፈዋል፡፡በዉይይቱም በየሽ ፕሮጀክት ከንብ ሀብት ልማት አንጻር በአዊ ብ/አስ ዞን በ3 ወረዳዎች የተሰሩ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ከቀረበዉ ሪፖርትም ለመረዳት እንደተቻለዉ ፕሮጀክቱ በዞኑ በሚገኙ 3 ወረዳዎች ቁጥራቸዉ ከ2000 በላይ የሆኑ ወጣቶችን የስልጠና እና የግብአት አቅርቦት ድጋፎችን በማድረግ ወደ ስራ ማስገባቱ ተገልጻል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ የ scaling up of honey production and fair trade in Ethiopia ፕሮጀክት ከግብይት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ስራዎችን እየሰራ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል፡፡ የፓናል ዉይይቱን የመሩት የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ደበበ አድማሱ እንደገለጹት የአማራ ክልል ለንብ ሀብት ልማት አመች የአየር ንብረት ያለዉ መሆኑን በመጥቀስ በዚህ ዘርፍ ወጣቶች በስፋ ተደራጅተዉ ወደ ስራ ቢገቡ ራሳቸዉንም ሆነ ሀገርን ተጠቃሚ የሚያደርጉበት እድል እንዳለ ጠቁመዉ በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ ለሚሰማሩ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይም ለወጣቶች የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ አስፈላጊዉን ሙያዊ እገዛ የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል ፡፡ ሃላፊዉ አክለዉም የእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍን ለማዘመን የሚሰሩ ስራዎች በዋነኛነት የመንግስትና የህዝብ ስራዎች መሆኑን ጠቅሰዉ የሽ ፕሮጀክት በአዊ ብ/እስ/ዞን ባሉ 3 ወረዳዎች በንብ ሀብት ልማት ዙርያ እየሰራዉ ያለዉን ስራ አመስግነዉ በተለይ እንዲህ አይነት መድረኮች መዘጋጀታቸዉ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ተወያቶ ለመፍታት ያለዉ ፋዳ ከፍተኛ በመሆኑ በቀጣይም ፕሮጀክቱ እሰራዉ ባለዉ አግባብ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠቁመዋል፡፡ የእለቱ ፕሮግራምም በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡

ዜና

የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ዘርፍ ለክልሎች የ122 ተሸከርካሪዎች ድጋፍ አደረገ::

lfsdp car01በግብርና ሚኒስቴር የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ዘርፉን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግና መንግስት በእንስሳት ልማትና ሽግግር ረገድ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለመደገፍ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ከእነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ ግንባር ቀደም የሆነው የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ሴክተር ፕሮጀክት የፕሮጀክቱን ዓላማ ለማሳካት የሚረዳ ተሸከርካሪዎችን ፕሮጀክቱ ለሚሰራባቸው ክልሎች አበርክቷል፡፡በ106 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ከአለም ባንክ በተገኝ የገንዘብ ድጋፍ 122 ተሸከርካሪዎች ለርክክብ ዝግጁ መደረጋቸውን ነው የግብርና ሚኒስቴር የገለፀው፡፡የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ዑመር ሁሴን እንደተናገሩት የፕሮጀክቱን አላማ በታቀደለት ጊዜ ከግብ በማድረስ የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ዘርፉን ምርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ሚኒስትሩ አክለውም የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ሴክተር ፕሮጀክት ለክልሎች ለማሰራጨት የተገዙትን ተሽከርካሪዎች ከሚፈለገው አላማ ውጭ ለጥቅም እንዳይውሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች የተገጠመላቸው መሆኑን በመናገር ፤የገንዘብ ድጋፍ ያደረገውንም የዓለም ባንክን በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ስም አመስግነዋል፡፡የእንስሳትና ዓሣ ሃብት ሴክተር ፕሮጀክት ብሔራዊ አስተባባሪ ዶ/ር ቶማስ ቸርነት በበኩላቸው ፤ ፕሮጀክቱ በዋናነት በወተት፣ በዶሮ፣ በዓሣ እንዲሁም በስጋ ላይ ትኩረት አድርጎ በ6 ክልሎች፣ 58 ወረዳዎችና በ 1 ሺህ 775 ቀበሌዎች ላይ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ሁሉም ተሸከርካሪዎች ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ፕሮጀክቱ በሚሰራባቸው ክልሎች እንደሚደርሱ በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ ተመላክቷል፡፡

ዜና

እድገት ለህብረት የንብ አናቢዎች ማህበር የሚገኘው በዋግ/ብ/አስ ዞን ሰቆጣ ወረዳ 03/ሃሙሲት ቀበሌ ሲሆን ማህበሩ ኡሁን ላይ ወንድ 7 ሴት 3 በድምሩ 10 አባላትን በመያዝ በ23 ዘመናዊ ቀፎዎች የንብ ማነብ ስራ እየሰሩ ይገኛል::

 

ATA hony06የአማራ ክልል ለንብ ሃብት ልማት ምቹ ሰነ-ምህዳር ያለው ክልል ነው ፡፡ እንደ ማዕከላዊ ስታስቲክስ 2017/2018 መረጃ መሰረት በክልሉ 1.15ሚሊዮን ያክል የንብ መንጋ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳ በክልላችን ሰፊ የሆነ የንብ ሃብት ልማት ቢኖርም ንብ አናቢው የህብረተሰብ ክፍል አሁንም ድረስ በሚከተለው ኋላቀር የንብ ማነብ ዘዴ ህብረተሰብ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ሳያገኝ ቆይቶል ፡፡ የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ንብ አናቢው የህብረተሰብ ክፍል ሳይንሳዊ ዘዴ ተጠቅሞ የንብ ማነብ ስራ እንዲሰራ በስልጠና ፤ በግብዓት አቅርቦትና በድጋፍና ክትትል በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛል ፡፡እድገት ለህብረት የንብ አናቢዎች ማህበር የሚገኘው በዋግ/ብ/አስ ዞን ሰቆጣ ወረዳ 03/ሃሙሲት ቀበሌ ሲሆን ማህበሩ ኡሁን ላይ ወንድ 7 ሴት 3 በድምሩ 10 አባላትን በመያዝ በ23 ዘመናዊ ቀፎዎች የንብ ማነብ ስራ እየሰራ እንደሆነ የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ መንግስቴ አብርሃ ገልፀዋል ፡፡አቶ መንግስቴ አብርሃ አክለውም በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ በኩል የተደረገላቸው 23 የንብ መንጋ ድጋፍ፤35 ዘመናዊ ቀፎ፤15 የሽግግር ቀፎ ፤ የሸድ ግንባታ ፤የማነብያ ቁሳቁሶችና የተሰጣቸው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ለስኬታማነታቸው ትልቅ ድርሻ ያለው መሆኑን ገልጸዋል ወደፊት ከዚህ በተሻለ መልኩ ስራቸውን አስፍተው መስራት እንደሚፈልጉም ገልጸዋል፡፡የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ከፍተኛ የእንስሳት ባለሙያ የሆኑት አቶ በለጠ አንተነህ እንደገለጹት ክልሉ ሰፊ የሆነ የንብ ሃብት ክምችት ያለው ቢሆንም አናቢው ህብረተሰብ አሁንም ድረስ በሚከተለ ኋላቀር የንብ ማነብ ዘዴ የተነሳ ህብረተሰቡም ሆነ አገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንዳታገኘ አድርጎታል ብለዋል ፡፡ ባለሙያዉ አክለዉም የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ንብ አናቢው የህብርተሰብ ክፍል ሳይንሳዊ የሆነ የማነብ ዘዴን ተከትሎ እንዲሰራ ኤጀንሲው ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዉ ወደፊትም በንብ ማነብ ስራ ፖቴንሻል በሆኑ አካባቢዎች ተደራጅተዉ ወደ ስራ ለሚገቡ አናቢዎች በግብርና ትራንስፎርሜሽን በኩል የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል ፡፡

ዜና

ጥምቀተ ባህር የንብ አናቢዎች ማህበር የሚገኘው በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ሹምሻ ቀበሌ ሲሆን ማህበሩ ኡሁን ላይ 8 አባላትን በመያዝ በ37 ዘመናዊ ቀፎዎች የንብ ማነብ ስራ እየሰሩ ይገኛል::

ATA hony02

የአማራ ክልል ለንብ ሃብት ልማት ምቹ ሰነ-ምህዳር ያለው ክልል ነው ፡፡ እንደ ማዕከላዊ ስታስቲክስ 2017/2018 መረጃ መሰረት በክልሉ 1.15ሚሊዮን ያክል የንብ መንጋ ይገኛል፡፡ ምንም እንኳ በክልላችን ሰፊ የሆነ የንብ ሃብት ልማት ቢኖርም ንብ አናቢው የህብረተሰብ ክፍል አሁንም ድረስ በሚከተለው ኃላ ቀር የንብ ማነብ ዘዴ ህብረተሰብ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባውን ጥቅም ሳያገኝ ቆይቶል ፡፡ የክልሉ እንስሳት ሃብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ንብ አናቢው የህብረተሰብ ክፍል ሳይንሳዊ ዘዴ ተጠቅሞ የንብ ማነብ ስራ እንዲሰራ በስልጠና ፤ በግብዓት አቅርቦትና በድጋፍና ክትትል በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛል ፡፡ጥምቀተ ባህር የንብ አናቢዎች ማህበር የሚገኘው በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ሹምሻ ቀበሌ ሲሆን ማህበሩ ኡሁን ላይ 8 አባላትን በመያዝ በ37 ዘመናዊ ቀፎዎች የንብ ማነብ ስራ እየሰራ እንደሆነ የማህበሩ ገንዘብ ያዥ አቶ ሙላት መልሴ ገልፀዋል ፡፡አቶ ሙላት መልሴ አክለውም በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ በኩል የተደረገላቸው 37 የንብ መንጋ ድጋፍ፤35 ዘመናዊ ቀፎ፤15 የሽግግር ቀፎ ፤የሸድ ግንባታ ፤የማነብያ ቁሳቁሶችና የተሰጣቸው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ለስኬታማነታቸው ትልቅ ድርሻ ያለው መሆኑን ገልጸዋል ወደፊት ከዚህ በተሻለ መልኩ ስራቸውን አስፍተው መስራት እንደሚፈልጉም ገልጸዋል፡፡የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ከፍተኛ የእንስሳት ባለሙያ የሆኑት አቶ በለጠ አንተነህ እንደገለጹት ክልሉ ሰፊ የሆነ የንብ ሃብት ክምችት ያለው ቢሆንም አናቢው ህብረተሰብ አሁንም ድረስ በሚከተለው ሃላቀር የንብ ማነብ ዘዴ የተነሳ ህብረተሰቡም ሆነ አገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንዳታገኘ አድርጎታል ብለዋል ፡፡ ባለሙያዉ አክለዉም የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኤጀንሲ ንብ አናቢው የህብርተሰብ ክፍል ሳይንሳዊ የሆነ የማነብ ዘዴን ተከትሎ እንዲሰራ ኤጀንሲው ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ጠቁመዉ ወደፊትም በንብ ማነብ ስራ ፖቴንሻል በሆኑ አካባቢዎች ተደራጅተዉ ወደ ስራ ለሚገቡ አናቢዎች በግብርና ትራንስፎርሜሽን በኩል የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል ፡፡

 

ዜና

የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከሴፍ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በቀን 11/02/2012 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ የወተት ቀን አከበረ፡፡

milkday01የክልሉ እንስሳት ሀብት ልማት ማስፋፊያ ኤጀንሲ ከሴፍ ፕሮጀክት ጋር በመተባበር በቀን 11/02/2012 ዓ.ም በዳንግላ ከተማ የወተት ቀን አከበረ፡፡ በበአሉ ጥሪ የተደረገላቸዉ የክልል፣የዞን እና የወረዳ ተሳቴፊዎች እና የዳንግላ ከተማ 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡ በአሉን አስመልክቶ የፕሮጀክቱ ሀላፊ አቶ ደስታ ዳመና እንደገለጹት ሴፍ ፕሮጀክት በአማራ ክልል በ2 ዞኖች በምእራብ ጎጃምና በአዊ ብ/አ/ዞን በሚገኙ 4 ወረዳዎች የወተት ምርትና ምርታማነትን የማሳደግ እና ገቢን በመጨመር በሴቶችና ወንዶች ፍትሀዊ ሀብት ተጠቃሚነት ላይ አልሞ የሚሰራ ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም የወተት ቀን በአልን በተማሪዎች ምገባ መልክ ማካሄድ ያስፈለገበትን ሁኔታ በዝርዝር ለታዳሚዎች አስረድተዋል፡፡ በመቀጠልም ለበአሉ ተሳታፊዎች እና ለተማሪዎች የወተት ምገባ ስነስርአት ከተካሄደ በኋላ በወተት ሀብት ልማት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን አስመልክቶ በኤጀንሲዉ በኩሉ አጭር መነሻ ጽሁፍ ቀርቦ ዉይይት በማድረግ የእለቱ ፕሮግራም ተጠናቋል፡፡

LOADING
Photo Title 1Photo Title 2Photo Title 3Photo Title 4Photo Title 5

download

 

 

Copyright©2022-ANRS Livestock Resources Development & Promotion Agency. All rights reserved! |